የሞቱ ሰዎች እንደገና በሕይወት መኖር ይችላሉ?
መልስህ ምንድን ነው?
ይችላሉ?
አይችሉም?
ወይስ ምናልባት?
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
ሰዎች ከሞት ይነሳሉ።’—የሐዋርያት ሥራ 24:15 አዲስ ዓለም ትርጉም
ይህን ማወቅህ ለአንተ ምን ጥቅም አለው?
የምትወዳቸው ሰዎች ሲሞቱ ማጽናኛ ታገኛለህ።—2 ቆሮንቶስ 1:3, 4
ስሞት ምን እሆናለሁ ከሚለው ፍርሃት ነፃ ትወጣለህ።—ዕብራውያን 2:15
ከምትወዳቸው ሰዎች ጋር እንደገና የመገናኘት ተስፋ ይኖርሃል። —ዮሐንስ 5:28, 29
መጽሐፍ ቅዱስ በሚናገረው ነገር ላይ እምነት መጣል እንችላለን?
አዎ፣ ቢያንስ ሦስት ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል፦
የሕይወት ምንጭ አምላክ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ “የሕይወት ምንጭ” ይሖዋ አምላክ እንደሆነ ይናገራል። (መዝሙር 36:9 አዲሱ መደበኛ ትርጉም፤ የሐዋርያት ሥራ 17:24, 25) ሕያዋን ፍጥረታትን ወደ ሕልውና ያመጣው አምላክ የሞተን ሰው ወደ ሕይወት መመለስ እንደሚችል ግልጽ ነው።
አምላክ ከዚህ በፊት ሰዎችን ከሞት አስነስቷል። መጽሐፍ ቅዱስ የተለያየ ፆታና ዕድሜ ያላቸው ስምንት ሰዎች (ልጆች፣ አዋቂዎች እንዲሁም ወንዶችና ሴቶች ይገኙበታል) በዚሁ ምድር ላይ ከሞት እንደተነሱ ይናገራል። ብዙዎቹ የተነሱት ከሞቱ ብዙም ሳይቆዩ ሲሆን አንዱ ግን የተነሳው መቃብር ውስጥ አራት ቀን ከቆየ በኋላ ነው!—ዮሐንስ 11:39-44
አምላክ ወደፊትም ሙታንን ለማስነሳት ይጓጓል። ይሖዋ ሞትን የሚመለከተው እንደ ጠላት ነው። (1 ቆሮንቶስ 15:26) ይህን ጠላት በትንሣኤ አማካኝነት ድል ለማድረግ ‘ይጓጓል።’ ይሖዋ የሚወዳቸውን ሰዎች ከሞት ለማስነሣትና በምድር ላይ እንዲኖሩ ለማድረግ ይናፍቃል።—ኢዮብ 14:14, 15