ሰቆቃወ ኤርምያስ 5:1-22
5 ይሖዋ ሆይ፣ የደረሰብንን ነገር አስታውስ።
ውርደታችንን እይ፤ ደግሞም ተመልከት።+
2 ርስታችን ለእንግዶች፣ ቤቶቻችን ለባዕድ አገር ሰዎች ተሰጡ።+
3 አባት እንደሌላቸው ወላጅ አልባ ልጆች ሆንን፤ እናቶቻችን እንደ መበለቶች ሆኑ።+
4 የገዛ ራሳችንን ውኃ ለመጠጣት መክፈል ነበረብን፤+ የገዛ እንጨታችንን የምናገኘውም በግዢ ነበር።
5 አሳዳጆቻችን አንገታችንን ሊይዙ ተቃረቡ፤ዝለናል፤ እረፍት የሚባል ነገርም አላገኘንም።+
6 በቂ ምግብ ለማግኘት ወደ ግብፅና ወደ አሦር እጃችንን ዘረጋን።+
7 ኃጢአት የሠሩት አባቶቻችን አሁን በሕይወት የሉም፤ እኛ ግን የእነሱን በደል ለመሸከም ተገደድን።
8 አሁን አገልጋዮች ይገዙናል፤ ከእጃቸው የሚያስጥለን ማንም የለም።
9 በምድረ በዳ ካለው ሰይፍ የተነሳ ምግባችንን የምናመጣው በሕይወታችን* ቆርጠን ነው።+
10 ከከባድ ረሃብ የተነሳ ቆዳችን እንደ ምድጃ ጋለ።+
11 በጽዮን ያሉ ሚስቶችና በይሁዳ ከተሞች ያሉ ደናግል ተዋረዱ።*+
12 መኳንንቱ በእጃቸው ተንጠለጠሉ፤+ ሽማግሌዎችም አልተከበሩም።+
13 ወጣቶች ወፍጮውን ይሸከማሉ፤ ልጆችም ከባድ እንጨት ሲሸከሙ ይደናቀፋሉ።
14 ሽማግሌዎች ከከተማዋ በር ሄደዋል፤+ ወጣቶችም ሙዚቃቸውን መጫወት አቁመዋል።+
15 ደስታ ከልባችን ራቀ፤ ጭፈራችን በሐዘን ተተካ።+
16 ራሳችን ላይ ያለው አክሊል ወድቋል። ኃጢአት ስለሠራን ወዮልን!
17 ከዚህ የተነሳ ልባችን ታመመ፤+ከእነዚህም ነገሮች የተነሳ ዓይኖቻችን ፈዘዙ፤+
18 ባድማ የሆነችው የጽዮን ተራራ+ አሁን የቀበሮዎች መፈንጫ ሆናለችና።
19 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን ለዘላለም በዙፋንህ ላይ ትቀመጣለህ።
ዙፋንህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።+
20 ለዘላለም የረሳኸንና ለረጅም ዘመን የተውከን ለምንድን ነው?+
21 ይሖዋ ሆይ፣ ወደ አንተ መልሰን፤ እኛም በፈቃደኝነት እንመለሳለን።+
ዘመናችንን እንደቀድሞው አድስልን።+
22 አንተ ግን ፈጽሞ ጥለኸናል።
አሁንም በእኛ ላይ እጅግ እንደተቆጣህ ነህ።+