በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“ለሰዎች ጥልቅ ፍቅር ስላላችሁ ልናመሰግናችሁ እንወዳለን”

“ለሰዎች ጥልቅ ፍቅር ስላላችሁ ልናመሰግናችሁ እንወዳለን”

“ለሰዎች ጥልቅ ፍቅር ስላላችሁ ልናመሰግናችሁ እንወዳለን”

ሩሲያ የሚገኘው የንቁ! ዘጋቢ እንደጻፈው

በሳይቤሪያ ምሥራቃዊ ክፍል በምትገኘው በቺታ የሚኖሩ የይሖዋ ምሥክሮች አዲስ ወደሠሩት የመንግሥት አዳራሽ ከመዛወራቸው በፊት ክርስቲያናዊ ስብሰባዎችን ያደርጉ የነበረው በአንድ ትምህርት ቤት የመማሪያ ክፍል ውስጥ ነበር። የይሖዋ ምሥክሮች፣ የሚሰበሰቡበትን ክፍል በንጽሕና በመያዛቸውና ጥገናዎችን በማድረጋቸው እንዲሁም ደግና ሰው አክባሪዎች በመሆናቸው የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህራን ለጉባኤው የምስጋና ደብዳቤ ጽፈዋል።

ደብዳቤው በከፊል እንዲህ ይላል:- “ለሰዎች ጥልቅ ፍቅር ስላላችሁ ልናመሰግናችሁ እንወዳለን። ሁሉም ሰው ይህንን በቀላሉ መረዳት ይችላል። የሚስዮናዊነት ሥራችሁንም ሆነ ኅብረተሰቡን ለመጥቀም ስትሉ የምታከናውኗቸውን የበጎ አድራጎት ተግባራት እናደንቃለን። አብረን በሠራንባቸው በእነዚህ ዓመታት ከእናንተ የተማርናቸውን ነገሮች ፈጽሞ አንረሳቸውም። በአምላክ የሚያምኑ ሰዎች ጨዋዎች፣ ትጉዎችና ደጎች ከመሆናቸውም በላይ እምነት ያላቸው፣ ሕይወታቸውን በዓላማ የሚመሩ ብሎም በግብ የሚንቀሳቀሱ መሆን እንዳለባቸው ተገንዝበናል።” የይሖዋ ምሥክሮችም ለተሰጣቸው አድናቆት አመስጋኞች ናቸው።

በሩሲያ የሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ ተወካይ፣ ከቺታ በስተ ምዕራብ 5,500 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ የምትገኘው የሴይንት ፒተርስበርግ አውራጃ አስተዳደር ባዘጋጀው አንድ ልዩ ሥነ ሥርዓት ላይ እንዲገኝ ተጋብዞ ነበር። ቅርንጫፍ ቢሮው የተጋበዘው ለምን ነበር? በአካባቢው ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች በየዓመቱ በረዶ ከቀለጠ በኋላ አስፋልቱ ላይ የሚከማቸውን ቆሻሻ ለማጽዳት በሚደረገው እንቅስቃሴ ስለሚካፈሉ ነው። እነዚህ የይሖዋ ምሥክሮች ከቅርንጫፍ ቢሮው አቅራቢያ የሚገኘውን 60 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው አስፋልት ያጸዳሉ። በመሆኑም ባለሥልጣናቱ የይሖዋ ምሥክሮች ለኅብረተሰቡ ባከናወኑት ጠቃሚ ተግባር የተነሳ ለቅርንጫፍ ቢሮው ተወካይ የመልካም ምግባር የምሥክር ወረቀት ሰጥተውታል። በዚህ ወቅት ተሰብሳቢዎቹ ሞቅ ያለ ጭብጨባ አሰምተዋል። የሚገርመው ስብሰባውን የሚመራው ሰው ይሖዋ የሚለውን መለኮታዊ ስም በተሳሳተ መንገድ ሲጠራ የይሖዋ ምሥክር ያልሆኑ በርካታ ተሰብሳቢዎች ወዲያውኑ አርመውታል። ይህም ተሰብሳቢዎቹ የአምላክን ስምም ሆነ ይህን ስም የተሸከሙትን ሕዝቦቹን በደንብ እንደሚያውቋቸው ያሳያል።

እነዚህ ሰዎች ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ሊያውቁ የቻሉት፣ በሩሲያ የሚገኙት 150,000 የሚያህሉ የይሖዋ ምሥክሮች በሚያደርጉት የስብከት እንቅስቃሴ አማካኝነት ነው። የይሖዋ ምሥክሮች፣ መስማት ለሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ የመጽሐፍ ቅዱስን አጽናኝ መልእክት በመናገር “ለሰዎች ጥልቅ ፍቅር” ማሳየታቸውን ይቀጥላሉ።—ማቴዎስ 22:39

[በገጽ 29 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የሩሲያ ቅርንጫፍ ቢሮ የመልካም ምግባር የምሥክር ወረቀት ተቀብሏል