መጠበቂያ ግንብ ጥቅምት 2013 | መጽሐፍ ቅዱስ የያዘው መልእክት ምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ፣ ወደ ሕልውና የመጣነው እንዴት እንደሆነ እንዲሁም አምላክ በመሲሑ አማካኝነት የሰውን ዘር ለማዳን ምን ዝግጅት እንዳደረገ ይነግረናል።

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

መጽሐፍ ቅዱስን ማወቅ የሚያስፈልግህ ለምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ፣ ስለ አምላክ የሚናገር ከመሆኑም ሌላ አምላክ ያስጻፈው መጽሐፍ ነው። ይህን መጽሐፍ በማንበብ ምን ትምህርት ማግኘት ትችላለህ?

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

ወደ ሕልውና የመጣነው እንዴት ነው?

የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የሆነው የዘፍጥረት መጽሐፍ፣ አጽናፈ ዓለም ከየት እንደመጣ በአጭሩ ይገልጻል። ከዘፍጥረት መጽሐፍ ሌላ ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን?

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

አምላክ የሰውን ዘር ለማዳን ዝግጅት አደረገ

አምላክ ለአብርሃም የገባለት ቃል ከመሲሑ ጋር የሚያያዘው እንዴት ነው? አምላክ፣ የሰው ልጆችን ከበሽታ፣ ከመከራና ከሞት የሚገላግላቸው እንዴት እንደሆነ እንድታነብብ እንጋብዝሃለን።

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

“መሲሑን አገኘነው”!

ብዙዎች፣ አስቀድሞ የተነገረለት መሲሕ ኢየሱስ እንደሆነ ያምናሉ። ሌሎች ግን ይህን አያምኑም። መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ ምን እንደሚል መርምር።

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

ለሁሉም ሰው የሚሆን ምሥራች

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው አምላክ ለሰው ዘር የላከው መልእክት ዛሬም ሆነ ወደፊት ሊጠቅምህ የሚችለው እንዴት ነው?

ፍቺ የሚያስከትለውን ጫና መቋቋም

አብዛኞቹ ፍቺ የፈጸሙ ሰዎች ሕይወታቸው ከጠበቁት በላይ አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው ጠቃሚ ምክር ይህንን ሁኔታ ለመቋቋም ይረዳል።

ወደ አምላክ ቅረብ

‘ይሖዋ በነፃ ይቅር ብሏችኋል’

አምላክ ንስሐ የሚገቡ ኃጢአተኞችን በፈቃደኝነት ይቅር ይላል። ታዲያ እኛ ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት ምን ማድረግ ይኖርብናል? ሌሎች ይቅር ማለታችን በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ሕይወት ይለውጣል

“ብዙ ሰዎች ይጠሉኝ ነበር”

ግልፍተኛ የነበረ አንድ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናቱ ሰላማዊ እንዲሆን የረዳው እንዴት እንደሆነ አንብብ።

ቀለማት ተጽዕኖ የሚያሳድሩብህ እንዴት ነው?

ቀለማት በሰዎች ስሜት ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ። እስቲ ሦስት ቀለማትን እንውሰድና በስሜትህ ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ እንመልከት።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የሞቱ ሰዎች ምን ተስፋ አላቸው? ከሞት ተነስተው እንደገና በሕይወት ይኖራሉ?

በተጨማሪም . . .

የይሖዋ ምሥክሮች ከቤት ወደ ቤት የሚሄዱት ለምንድን ነው?

ኢየሱስ ለጥንቶቹ ደቀ መዛሙርት ምን መመሪያ እንደሰጣቸው እንድታውቅ እንጋብዝሃለን።