በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ቪዲዮዎች—መሠረታዊ ትምህርቶች
እነዚህ አጫጭር ቪዲዮዎች መሠረታዊ ለሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣሉ፤ ለምሳሌ ያህል፣ አምላክ ምድርን የፈጠረው ለምንድን ነው? የሞቱ ሰዎች በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ? አምላክ መከራ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው?
ጽንፈ ዓለም የተገኘው በፍጥረት ነው?
ብዙዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን የፍጥረት ዘገባ በተሳሳተ መንገድ ይረዱታል። ታዲያ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ነገር ምክንያታዊ ነው?
በእርግጥ አምላክ አለ?
አምላክ አለ ብሎ ማመን ምክንያታዊ ነው፤ ማስረጃውን ለምን አትመረምርም?
አምላክ ስም አለው?
አምላክ ብዙ የማዕረግ ስሞች አሉት፤ ከእነዚህ ስሞች መካከል ሁሉን ቻይ፣ ፈጣሪ እና ጌታ የሚሉት ይገኙበታል። ይሁንና የአምላክ የግል ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ወደ 7,000 ጊዜ ይገኛል።
የአምላክ ወዳጅ መሆን ይቻላል?
ለበርካታ ዘመናት ሰዎች ስለ ፈጣሪያቸው ለማወቅ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ወዳጅ እንድንሆን ይረዳናል። ይህ ወዳጅነት የሚጀምረው የአምላክን ስም በማወቅ ነው።
የመጽሐፍ ቅዱስ ባለቤት ማን ነው?
መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት ሰዎች ከሆኑ የአምላክ ቃል ሊባል ይችላል? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው የማን ሐሳብ ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ ከአምላክ የመጣ ነው?
መጽሐፍ ቅዱስን ያስጻፈው አምላክ ከሆነ እስከ ዛሬ ከተጻፉት መጻሕፍት ሁሉ የላቀ መሆን አለበት።
አምላክ ምድርን የፈጠረው ለምንድን ነው?
ምድራችን በሚያስደምሙ ውብ ነገሮች የተሞላች ናት። ከፀሐይ ያላት ርቀት፣ ያጋደለችበት መጠን እንዲሁም በዛቢያዋ ላይ የምትሽከረከርበት ፍጥነት የተስተካከለ ነው። ለመሆኑ አምላክ ይህን ያህል ተጠቦ ምድራችንን የፈጠረበት ዓላማ ምንድን ነው?
የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው?
እውነተኛ ደስታ ለማግኘትና ትርጉም ያለው ሕይወት ለመምራት ቁልፉ ምንድን ነው?
ለጥያቄዎችህ መልስ ማግኘት የምትችለው ከየት ነው?
ሕይወትን፣ ሞትን ወይም የወደፊቱን ጊዜ በተመለከተ ጥያቄ ይፈጠርብሃል? ለእነዚህም ሆነ ለሌሎቹ ጥያቄዎችህ መልስ ማግኘት ትችላለህ! ግን ከየት?
ስንሞት ምን እንሆናለን?
መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ሰዎች እንደ አልዓዛር ትንሣኤ የሚያገኙበት ጊዜ እንደሚመጣ ይናገራል።
ሲኦል ኃጢአተኞች የሚሠቃዩበት ቦታ ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ ‘አምላክ ፍቅር እንደሆነ’ ይናገራል፤ ፍቅር የሆነ አምላክ ደግሞ ቀደም ሲል ለሠራነው ኃጢአት ለዘላለም አያሠቃየንም።
ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነው?
ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉን ቻይ አምላክ ነው? ወይስ ሁሉን ቻይ ከሆነው አምላክ የተለየ አካል ነው?
ኢየሱስ የሞተው ለምንድን ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስ ሞት ለሰው ልጆች ከፍተኛ ጥቅም እንዳስገኘ ይናገራል። ለመሆኑ የኢየሱስ ሞት ምን ጥቅም አስገኝቷል?
የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
ኢየሱስ ምድር ላይ በነበረበት ወቅት ከየትኛውም ርዕሰ ጉዳይ ይበልጥ ያስተማረው ስለ አምላክ መንግሥት ነው። ለበርካታ መቶ ዘመናት፣ የኢየሱስ ተከታዮች ይህ መንግሥት እንዲመጣ ሲጸልዩ ኖረዋል።
የአምላክ መንግሥት በ1914 መግዛት ጀምሯል
ከ2,600 ዓመታት በፊት አምላክ፣ ለአንድ ኃያል ንጉሥ ትንቢታዊ ይዘት ያለው ሕልም ገልጦለት ነበር፤ ይህ ትንቢት በአሁኑ ጊዜ ፍጻሜውን እያገኘ ነው።
ከ1914 ወዲህ የዓለም ሁኔታ ተቀይሯል
ከ1914 ወዲህ በዓለም ላይ እየተፈጸሙ ያሉት ክንውኖች እንዲሁም የሰዎች ባሕርይ ስለ “መጨረሻዎቹ ቀናት” የሚናገሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች እየተፈጸሙ እንደሆነ ያሳያሉ።
የተፈጥሮ አደጋዎች የአምላክ ቅጣት ናቸው?
በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ሲማሩ ምን ተረዱ? እስቲ ከራሳቸው አንደበት እንስማ።
አምላክ መከራ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው?
ብዙ ሰዎች ዓለማችን በጥላቻና በመከራ የተሞላ የሆነው ለምን እንደሆነ ይጠይቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ አጥጋቢ መልስ ይሰጣል።
አምላክ ሁሉንም ሃይማኖቶች ይቀበላል?
ብዙ ሰዎች የየትኛውም ሃይማኖት ተከታይ ብትሆን ለውጥ እንደሌለው ይናገራሉ።
አምላክ ምስሎችን ተጠቅመን የምናቀርበውን አምልኮ ይቀበላል?
ምስሎችን ተጠቅመን ማምለካችን ወደማይታየው አምላክ ለመቅረብ ይረዳናል?
አምላክ ማንኛውንም ዓይነት ጸሎት ይሰማል?
አንድ ሰው በራስ ወዳድነት ፍላጎት ተነሳስቶ ቢጸልይ አምላክ ይሰማዋል? ሚስቱን የሚበድል ባል የአምላክን በረከት ለማግኘት ቢለምን ጸሎቱ ተቀባይነት ይኖረዋል?
አምላክ ለትዳር ያለው አመለካከት ምንድን ነው?
አምላክ በትዳርህ እንዲሳካልህ ይፈልጋል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ግሩም ምክር የብዙ ባለትዳሮችን ሕይወት አቅንቷል።
ፖርኖግራፊ ኃጢአት ነው?
“ፖርኖግራፊ” የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛል? አምላክ ስለ ፖርኖግራፊ ምን አመለካከት እንዳለው እንዴት ማወቅ እንችላለን?