በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በስተ ግራ፦ እህት ታትያና ጋልኬቪች፤ በስተ ቀኝ፦ እህት ቫለንቲና ቭላዲሚሮቫ

ጥር 24, 2022 | የታደሰው፦ የካቲት 16, 2024
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ጥፋተኛ ተባሉ | ከባድ የጤና እክል ያለባቸው ሁለት እህቶች ለስድስት ወር ማረፊያ ቤት ቢቆዩም በይሖዋ እርዳታ መጽናት ችለዋል

ወቅታዊ መረጃ—ጥፋተኛ ተባሉ | ከባድ የጤና እክል ያለባቸው ሁለት እህቶች ለስድስት ወር ማረፊያ ቤት ቢቆዩም በይሖዋ እርዳታ መጽናት ችለዋል

የካቲት 14, 2024 በስሞለንስክ የሚገኘው የፕሮሚሽሌኒ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ እህት ታትያና ጋልኬቪች እና እህት ቫለንቲና ቭላዲሚሮቫ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ውሳኔ አስተላልፏል። በሁለቱም ላይ የሁለት ዓመት የገደብ እስራት በይኗል። የአሁኑ ብይን ወህኒ እንዲገቡ የሚጠይቅ አይደለም።

የክሱ ሂደት

  1. ግንቦት 14, 2019

    ባለሥልጣናት በታትያና እና በቫለንቲና ላይ የወንጀል ምርመራ አስጀመሩ። ፖሊሶች የሁለቱንም እህቶች አፓርታማዎች በረበሩ፤ እንዲሁም ከ48 ሰዓት በላይ የወንጀል ምርመራ አካሄዱባቸው። ሁለቱም ከባድ የጤና እክል ቢኖርባቸውም ወደ ማረፊያ ቤት ተላኩ

  2. ኅዳር 22, 2019

    ታትያና እና ቫለንቲና ከስድስት ወር በላይ ማረፊያ ቤት ከቆዩ በኋላ ተለቀው በቁም እስር እንዲቆዩ ተደረጉ

  3. ታኅሣሥ 31, 2019

    ቫለንቲና ጤንነቷ በማሽቆልቆሉ ወደ ሆስፒታል ተወሰደች

  4. ነሐሴ 6, 2020

    ከስምንት ወራት ገደማ በኋላ ታትያና ከቁም እስር ተለቀቀች፤ ሆኖም ከምትኖርበት ከተማ እንዳትወጣ ታዘዘች። ቫለንቲና ግን በቁም እስር ቀጠለች፤ መነጋገር የሚፈቀድላት ከአንድ የቅርብ ዘመዷ እና ከጠበቃዋ ጋር ብቻ ነበር

  5. ጥቅምት 2, 2020

    ባለሥልጣናቱ ታትያናን እና ቫለንቲናን ለመክሰስ የ400 ገጽ ሰነድ አስገቡ። ሰነዱ እህቶች “የጽንፈኛ ድርጅትን እንቅስቃሴ ለመደበቅ” እንዳሴሩ ይገልጻል

  6. ጥቅምት 14, 2020

    ጉዳያቸው በፍርድ ቤት በተሰማበት ወቅት ዳኛው ማስረጃው ለፍርድ ቤት የማይበቃ በመሆኑ ምክንያት ጉዳያቸው ለተጨማሪ ምርመራ ወደ አቃቤ ሕግ ቢሮ እንዲመለስ አዘዙ። ቫለንቲና በጤንነቷ ምክንያት ፍርድ ቤት ውስጥ መቆም ባትችልም እንኳ ፍርድ ቤቱ ከቁም እስር እንድትለቀቅ አልፈቀደም

  7. የካቲት 25, 2021

    ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ፣ ጉዳያቸው ወደ አቃቤ ሕግ ቢሮ እንዲመለስ የተደረገውን ውሳኔ ቀለበሰ፤ በመሆኑም ጉዳያቸው በፍርድ ቤት መታየቱን ቀጠለ

አጭር መግለጫ

ይሖዋ ለቫለንቲና፣ ለታትያና እንዲሁም በሩሲያና በክራይሚያ ስደት እየደረሰባቸው ላሉት ወንድሞችና እህቶች በሙሉ ‘ብርታትና ጋሻ’ መሆኑን እንዲቀጥል ጸሎታችን ነው።—መዝሙር 28:7