በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም አሌክሳንደር ኒኮላዬቭ ከእስር ተፈትቶ ከሚስቱ ዬቭጌኒያ፣ ከአምስት ልጆቻቸውና ከዬቭጌኒያ እናት ጋር

መስከረም 21, 2023
ሩሲያ

ወንድም አሌክሳንደር ኒኮላዬቭ ከእስር ተፈታ

ወንድም አሌክሳንደር ኒኮላዬቭ ከእስር ተፈታ

መስከረም 19, 2023 ወንድም አሌክሳንደር ኒኮላዬቭ ከእስር ተፈታ። ወንድም አሌክሳንደር በሩሲያ እስር ቤት ወደ ሁለት ዓመት የሚጠጋ ጊዜ አሳልፏል። አሌክሳንደር ሲፈታ የእምነት አጋሮቹ አቀባበል ያደረጉለት ሲሆን ከሚስቱ ዬቭጌኒያ እና ከአምስት ልጆቹ ጋር በድጋሚ ተገናኝቷል።

በ2021 መባቻ ላይ የፌደራል የደህንነት አባላትና አድማ በታኝ ፖሊሶች የአሌክሳንደርን ቤት ፈተሹ። ፍተሻውን ተከትሎም አሌክሳንደር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐሳቦችን ከቤተሰቡና ከጓደኞቹ ጋር በመወያየት “ወንጀል” ተከሰሰ።

አሌክሳንደር በቁጥጥር ሥር ከመዋሉ በፊት፣ ታማኝ ሆኖ እንዲቀጥል የረዳው ምን እንደሆነ ሲናገር እንዲህ ብሏል፦ “የሰው ፍርሃትና ‘ምን ይመጣ ይሆን?’ የሚል ስጋት አጥርቶ ማሰብ እንዲያቅተኝ ሊያደርገኝ እንደሚችል ተገንዝቤአለሁ። ስለዚህ እንዲህ ባለው ፍርሃት ላለመሸነፍ ጥረት አደርጋለሁ። ይሖዋን በእሱ ላይ የበለጠ ለመተማመን እንዲረዳኝ በጸሎት ለምኜዋለሁ፤ እሱም ይህን ለማድረግ ብርታት ሰጥቶኛል።”

አሌክሳንደር ነፃ በመውጣቱና ከቤተሰቡ ጋር በመቀላቀሉ ተደስተናል። ይሖዋ የፍትሕ መጓደል ቢያጋጥማቸውም እምነትና ድፍረት በማሳየት በታማኝነት በሚያገለግሉት ሕዝቡ ‘ደስ እንደሚሰኝ’ ምንም ጥርጥር የለውም።—መዝሙር 149:4