በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የይሖዋ ምሥክሮች ኢኳዶር ውስጥ በተደረገ ስፖርታዊ ውድድር ላይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎችን ሲያበረክቱ

ታኅሣሥ 26, 2022
ኢኳዶር

ኢኳዶር ውስጥ የአደባባይ ምሥክርነት ሺዎችን ተደራሽ አደረገ

ኢኳዶር ውስጥ የአደባባይ ምሥክርነት ሺዎችን ተደራሽ አደረገ

ጥቅምት 29, 2022 የኢኳዶሯ ጓያኪል ከተማ፣ የደቡብ አሜሪካ የእግር ኳስ ክለቦች ውድድር (ኮፓ ሊበርታዶሬስ) የፍጻሜ ጨዋታ አስተናግዳ ነበር። ይህን ትልቅ ክንውን ምክንያት በማድረግ ከጨዋታው በፊትና በኋላ ባሉት ቀናት 1,500 ገደማ የይሖዋ ምሥክሮች በጋሪ ምሥራቹን ሰብከዋል።

ወንድሞች እግረኛ በሚበዛባቸው 45 ቦታዎች ላይ 135 ምሥክርነት መስጫ ጋሪዎችን አቁመው ነበር። ብዙዎች በዚህ ልዩ የምሥክርነት ዘመቻ ላይ ለመሳተፍ ሲሉ ፕሮግራማቸውን አስተካክለዋል። ጨዋታውን ለመታደም ከብራዚል የመጡ ብዙ ጎብኚዎች ነበሩ፤ በመሆኑም አንዳንድ ወንድሞችና እህቶች ጎብኚዎቹን ለማናገር ሲሉ የተወሰኑ የፖርቱጋልኛ ቃላትን ተምረዋል።

የምሥክርነት ዘመቻው የተሳካ ነበር። ለምሳሌ፣ በአንድ ቀን ብቻ አስፋፊዎች 796 ጽሑፎችን አበርክተዋል። በጥቅሉ ደግሞ ኅዳር 2 በተጠናቀቀው የአሥር ቀናት ዘመቻ 5,139 ጽሑፎች ተሰራጭተዋል።

ዘመቻውን በማስተባበር ያገዘው ወንድም ዳቪዴ ዴል ሞንቴ እንዲህ ብሏል፦ “ቱሪስቶች በወንድሞችና እህቶች ፈገግታና ደግነት ስለተማረኩ ፎቶ እናንሳችሁ ይሏቸው ነበር። በአለባበሳቸውና የተደራጁ በመሆናቸው አድናቆታቸውን የሚገልጹም ነበሩ፤ አንዳንዶች ደግሞ ጽሑፎቹ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆኑ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።”

አንዲት ሴት ወደ ጋሪው ቀርባ እንዲህ ብላለች፦ “ገና ከሩቅ ነው ያወቅኳችሁ። ያለቃል ብዙ ትመሥክራላችሁ። የምትጠቀሙበት ዘዴ ልዩ ነው።”

ይህ የምሥክርነት ዘመቻ ለይሖዋ ውዳሴ እንዳመጣ ምንም ጥርጥር የለውም፤ ምክንያቱም “በአደባባይ ላይ ያለማቋረጥ ድምፅዋን [የምታሰማው]” እንዲሁም “ሰው በሚበዛባቸው ጎዳናዎች ማዕዘን ላይ ሆና [የምትጣራው]” ጥበብ ከእሱ የተገኘች ነች።—ምሳሌ 1:20, 21