በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ታኅሣሥ 24, 2021
ካናዳ

በካናዳ የጉልበት ሥራ ካምፖች ወንድሞቻችን ያሳዩት አስደናቂ እምነት

በካናዳ የጉልበት ሥራ ካምፖች ወንድሞቻችን ያሳዩት አስደናቂ እምነት

በ1946 የበጋ ወቅት የካናዳ ባለሥልጣኖች በካናዳ ርቀው በሚገኙ የተለያዩ የጉልበት ሥራ ካምፖች ውስጥ የነበሩ ወጣት የይሖዋ ምሥክሮችን ነፃ ለቀቁ። ወደ 300 የሚጠጉ ወጣት የይሖዋ ምሥክሮች በሕሊናቸው ምክንያት ወታደራዊ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የጉልበት ሥራ እንዲሠሩ ተገደው ነበር። ወንድሞቻችን፣ ያጋጠማቸውን ከባድ ሁኔታ በድፍረት የተቋቋሙ ሲሆን ከካምፖቹ ሲወጡ መንፈሳዊነታቸው ከቀድሞው ይበልጥ ተጠናክሮ ነበር። ውድ ወንድሞቻችን ከካምፖቹ ከተለቀቁ ዘንድሮ 75ኛ ዓመታቸው ነው። አሁንም ድረስ በሕይወት ካሉት ጥቂት ወንድሞች መካከል አንዱ የሆኑት ዶን ማክሊን ያኔ የነበረውን ሁኔታ ሲያስታውሱ እንዲህ ብለዋል፦ “በጥቅሉ ሲታይ በጦርነቱ ወቅት ያጋጠሙኝ ነገሮች በጣም አጠንክረውኛል። ስለዚያ ጊዜ ሳስታውስ ሁሌም ይሖዋን አመሰግናለሁ።”