በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ነሐሴ 5, 2022
ፊሊፒንስ

ከባድ የምድር መንቀጥቀጥ ሰሜናዊ ፊሊፒንስን አናወጠ

ከባድ የምድር መንቀጥቀጥ ሰሜናዊ ፊሊፒንስን አናወጠ

ሐምሌ 27, 2022 ሉዞን የተባለችው የፊሊፒንስ ደሴት በምድር መናወጥ መለኪያ 7.0 በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመታች። በአደጋው ከባድ ጉዳት የደረሰበት የአብራ ግዛት ነው። የመሬት መናወጡ 400 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቆ እስከሚገኘው እስከ ማኒላ ድረስ ተሰምቷል። ዋናውን የመሬት መናወጥ ተከትሎ ከ2,000 በላይ ትናንሽ የመሬት መናወጦች ተመዝግበዋል።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል ሕይወቱን ያጣ የለም

  • 4 አስፋፊዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 42 ቤተሰቦች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

  • 63 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 1 ቤት ከባድ ጉዳት ደርሶበታል

  • 13 የመሰብሰቢያ አዳራሾች ጉዳት ደርሶባቸዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • 1 የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ የእርዳታ ሥራውን እንዲያስተባብር ተደርጓል

  • በአካባቢው ያሉ የጉባኤ ሽማግሌዎች ጉዳት ለደረሰባቸው ክርስቲያኖች እረኝነት እያደረጉ ነው

  • ሁሉም የእርዳታ እንቅስቃሴ የሚካሄደው ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው

ቅርንጫፍ ቢሮው አደጋ በደረሰበት አካባቢ ለሚኖሩ ወንድሞችና እህቶች ወዲያውኑ የእርዳታ ቁሳቁሶች ልኳል፤ ጊዜያዊ መጠለያ እንዲያገኙም ዝግጅት አድርጓል። አደጋ የደረሰባቸው ወንድሞችና እህቶችም እርስ በርስ ሲረዳዱ ነበር።

በዚህ ‘የጭንቅ ቀን’ ይሖዋ ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን እንደሚታደጋቸው እርግጠኞች ነን።—መዝሙር 50:15