ስለ ሕይወት አመጣጥ የተሰጡ አስተያየቶች

የተለያዩ ሰዎች በፈጣሪ መኖር እንዲያምኑ ስላደረጋቸው ነገር የሰጡት አስተያየት።

ሞኒካ ሪቻርድሰን፦ አንዲት የሕክምና ባለሙያ ስለምታምንበት ነገር ምን ትላለች?

‘ልጅ በሚወለድበት ወቅት የሚታየው አስገራሚ ክንውን እንዲሁ በአጋጣሚ የተገኘ ነው ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?’ የሚል ጥያቄ ነበራት። በሕክምና ሙያዋ ያገኘችው ተሞክሮ ምን መደምደሚያ ላይ እንድትደርስ አደረጋት?

ማሲሞ ቲስታሬሊ፦ አንድ የሮቦት መሐንዲስ ስለሚያምንበት ነገር ምን ይላል?

ለሳይንስ የሚሰጠው ትልቅ ቦታ ስለ ዝግመተ ለውጥ በተማረው ነገር ላይ ጥያቄ እንዲያነሳ አድርጎታል።

ፒተር መዝኒ፦ አንድ የሕግ ፕሮፌሰር ስለሚያምንበት ነገር ምን ይላል?

የተወለደው በኮሚኒስት አገዛዝ ሥር ነው። በፈጣሪ መኖር ማመን እንደ ሞኝነት ይቆጠር ነበር። አመለካከቱን እንዲቀይር ያደረገው ምን ይሆን?

ኢሬን ሆፍ ሎራንሶ፦ አንዲት የአጥንት ቀዶ ሕክምና ባለሙያ ስለምታምንበት ነገር ምን ትላለች?

ከአጥንት ቀዶ ሕክምና ጋር የተያያዘው ሙያዋ ታምንበት በነበረው የዝግመተ ለውጥ ጽንሰ ሐሳብ ላይ ጥያቄ እንድታነሳ አድርጓታል።

እነዚህንስ አይተሃቸዋል?

ሳይንስ እና መጽሐፍ ቅዱስ

ስለ ሕይወት አመጣጥ የተሰጡ አስተያየቶች

የሥነ ሕይወት ተመራማሪዎች፣ ባዮኬሚስቶች፣ ሐኪሞች፣ የቀዶ ጥገና ባለሙያዎችና ሌሎች ሰዎች በሙያቸው ያገኙትን እውቀት መጽሐፍ ቅዱስ ከሚናገረው ነገር ጋር ካወዳደሩ በኋላ የሕይወት አመጣጥን በተመለከተ የደረሱበትን መደምደሚያ ይናገራሉ።