በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አይተወኝም ለብቻዬ

አይተወኝም ለብቻዬ

አውርድ፦

  1. 1. ብቻዬን ተተውኩኝ፤

    ጣሉኝ፣ ሁሉም ከዱኝ።

    ውስጤ ተስፋ ቆረጠ፤

    ልቤም በሐዘን ተዋጠ።

    ለማን አቤት ልበል?

    ማንስ ያዝንልኛል?

    አይዞህ ባይ የለኝ ቅርቤ፤

    ብጮኽ ማን ይደርስልኛል?

    (አዝማች)

    ከላይ አለ

    ጠበቃዬ፤

    አይተወኝም

    ለብቻዬ።

    አይቶልኛል

    መገፋቴን፤

    ጆሮው ሰምቷል

    መቃተቴን።

    አጥቼው አላውቅም

    አንዴም ከጎኔ።

  2. 2. ሁሉን ነገር ባጣ፣

    አንተን በመያዜ፤

    ማንም በቃሉ ባይገኝ፣

    አንተ ታማኝ ነህ ሁልጊዜ።

    ስምህን ጠርቼ

    አታሳፍረኝም፤

    እምነቴና ተስፋዬ

    አውቃለሁ፣ ከንቱ አይቀርም።

    (አዝማች)

    ከላይ አለ

    ጠበቃዬ፤

    አይተወኝም

    ለብቻዬ።

    አይቶልኛል

    መገፋቴን፤

    ጆሮው ሰምቷል

    መቃተቴን።

    አጥቼው አላውቅም

    አንዴም ከጎኔ።

    ጠበቃዬ፤

    አይተወኝም

    ለብቻዬ።

    አይቶልኛል

    መገፋቴን፤

    ጆሮው ሰምቷል

    መቃተቴን።

    አጥቼው አላውቅም

    አንዴም ከጎኔ።