በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

እርግጠኛ ሁን

እርግጠኛ ሁን

አውርድ፦

  1. 1. ታማኝነትህ፣

    አገልግሎትህ፣

    ከንቱ አይቀርም ይህ ጽናትህ።

    ሰው ባያውቅልህም ያሳለፍከውን

    ይሖዋ አይቶልሃል ሁሉን።

    (ቅድመ አዝማች)

    በገዢዎች፣ በዳኞች ፊት ሲያቆሙህ

    አለን ከጎንህ።

    ባቋምህ፣ በ’ምነትህ ኮርተናል፤

    ይሖዋም አይቷል።

    (አዝማች)

    ‘እርግጠኛ ነኝ፤

    ሞትም ሆነ ኃያል መንግሥት አይለየንም ከፍቅሩ።’

    ‘እርግጠኛ ነኝ፤

    ማንኛውም ፍጥረት ቢሆን አይለየንም ከፍቅሩ።’

    እርግጠኛ ሁን፤

    አይቀንስም ፍቅሩ።

  2. 2. አልተረታህም፤

    እጅ አልሰጠህም።

    ያን ሁሉ ፈተና

    ታምነህ ጸናህ።

    ብቻህን እንዳልሆንክ እርግጠኛ ሁን፤

    ከኛ ጋር ያሉት ይበልጣሉ።

    (ቅድመ አዝማች)

    በገዢዎች፣ በዳኞች ፊት ሲያቆሙህ

    አለን ከጎንህ።

    ባቋምህ፣ በ’ምነትህ ኮርተናል፤

    ይሖዋም አይቷል።

    (አዝማች)

    ‘እርግጠኛ ነኝ፤

    ሞትም ሆነ ኃያል መንግሥት አይለየንም ከፍቅሩ።’

    ‘እርግጠኛ ነኝ፤

    ማንኛውም ፍጥረት ቢሆን አይለየንም ከፍቅሩ።’

    እርግጠኛ ሁን፤

    አይቀንስም ፍቅሩ።

    አዎ፣ ፍቅሩ።

    (መሸጋገሪያ)

    ምን ይገርማል ብንሰደድ ለታላቅ ስሙ!

    ኦ፣ ይላል ቃሉም።

    ‘በወደደን በሱ ድል አድራጊዎች እንሆናለን፤’

    ’ናሸንፋለን።

    (አዝማች)

    ‘አዎ አምናለሁ፤

    ሞትም ሆነ ኃያል መንግሥት አይለየንም ከፍቅሩ።’

    ‘እርግጠኛ ነኝ፤

    ማንኛውም ፍጥረት ቢሆን አይለየንም ከፍቅሩ።’

    ‘አዎ አምናለሁ፤

    ሞትም ሆነ ኃያል መንግሥት አይለየንም ከፍቅሩ።’

    ‘እርግጠኛ ነኝ፤

    ማንኛውም ፍጥረት ቢሆን አይለየንም ከፍቅሩ።’

    እርግጠኛ ሁን፤

    አይቀንስም ፍቅሩ።