በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የዘላለም ደስታ

የዘላለም ደስታ

(መዝሙር 16:11)

አውርድ፦

  1. 1. ሰማያትን የዘረጋህ

    ታላቁ ጌታ፣

    ውብ አድርገህ ሠራሃቸው

    ፀሐይ፣ ጨረቃን።

    ምድርን ሠርተህ አሳምረህ፣

    ስታበቃ ሁሉን ፈጥረህ፣

    ደስ አለው ልብህ።

    (አዝማች)

    ደስ አለን በ’ጆችህ ሥራ፣

    በምናውጀው ምሥራች፣

    ለኛ ባሰብከው ተስፋ።

    ከዚህ ሁሉ ግን ’ሚበልጠው

    በፍቅርህ መኖራችን ነው።

    አንተ ነህ የኛ ደስታ፣

    የዘላለም ደስታ።

  2. 2. ሁሉን ነገር ሰጥተኸናል

    ለጋሱ ጌታ፤

    ልባችን ሐሴት ያደርጋል

    ባንተ ስጦታ።

    ፈጥረኸናል በአምሳልህ

    ግሩም አድርገህ በፍቅርህ፤

    ድንቅ ነው ሥራህ።

    (አዝማች)

    ደስ አለን በ’ጆችህ ሥራ፣

    በምናውጀው ምሥራች፣

    ለኛ ባሰብከው ተስፋ።

    ከዚህ ሁሉ ግን ’ሚበልጠው

    በፍቅርህ መኖራችን ነው።

    አንተ ነህ የኛ ደስታ፣

    የዘላለም ደስታ።

    (መሸጋገሪያ)

    ልጅህ ሞቶልን ነው

    ከፍለህልን ውድ ዋጋ፤

    የታደልነው ለዚህ ደስታ

    ባንተ ነው፣ ባንተ ውለታ።

    (አዝማች)

    ደስ አለን በ’ጆችህ ሥራ፣

    በምናውጀው ምሥራች፣

    ለኛ ባሰብከው ተስፋ።

    ከዚህ ሁሉ ግን ’ሚበልጠው

    በፍቅርህ መኖራችን ነው።

    አንተ ነህ የኛ ደስታ፣

    የዘላለም ደስታ።

    (አዝማች)

    ደስ አለን በ’ጆችህ ሥራ፣

    በምናውጀው ምሥራች፣

    ለኛ ባሰብከው ተስፋ።

    ከዚህ ሁሉ ግን ’ሚበልጠው

    በፍቅርህ መኖራችን ነው።

    አንተ ነህ የኛ ደስታ፣

    የዘላለም ደስታ።

(በተጨማሪም መዝ. 37:4⁠ን እና 1 ቆሮ. 15:28⁠ን ተመልከት።)