በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ይሖዋን ይዤ

ይሖዋን ይዤ

አውርድ፦

  1. 1. ዛሬስ የት ይወስደኝ ይሆን ውሎዬ?

    ወጣሁ ከቤት አምላኬን ተማጽኜ።

    አትስበክ ይላሉ የማይሆን ነገር!

    አልውልም ስሙን ሳልናገር።

    (አዝማች)

    አይረበሽም ልቤ፤ ጭንቄን፣ ሐሳቤን ለሱ ጥዬ።

    ደግሞስ ምን ያስፈራኛል ይሖዋን ይዤ?

    እኔስ ሰውን አልፈራም አምላኬን ይዤ።

  2. 2. ላዝግም ወደ ቤቴ ተመስገን ብዬ፤

    ቅን ሰው አግኝቼ ሰምሯል ውሎዬ።

    ልቡ ቢጽናና እውነትን ተምሮ፤

    ዳግም ላገኘው ይዣለሁ ቀጠሮ።

    (አዝማች)

    አይረበሽም ልቤ፤ ጭንቄን፣ ሐሳቤን ለሱ ጥዬ።

    ደግሞስ ምን ያስፈራኛል ይሖዋን ይዤ?

    እኔስ ሰውን አልፈራም አምላኬን ይዤ።

    (መሸጋገሪያ)

    የሚፋጅ እሳት ሆኖብኝ ቃሉ፣

    በል በል ይለኛል አውጅ ስሙን።

    ያወድሰዋል አንደበቴ፤

    ዝም አይልም ፍጹም እስካለ ሕይወቴ።

    አላፍርም በቃሉ ዓለም ይስማ፤

    ማፈግፈግ የለም ከንግዲማ!

    ያመንኩት ጌታ መች ይተወኛል?

    አውቀዋለሁ እሱን ይክሰኛል።

  3. 3. እስቲ ልተኛ፣ ይረፍ ጎኔ፤

    ሰላም ያዋለኝን አመስግኜ።

    ስጋት አይገባኝም ነገስ ብዬ፤

    አይለይም ከኔ፣ ጠባቂዬ።

    (አዝማች)

    አይረበሽም ልቤ፤ ጭንቄን፣ ሐሳቤን ለሱ ጥዬ።

    ደግሞስ ምን ያስፈራኛል ይሖዋን ይዤ?

    እኔስ ሰውን አልፈራም አምላኬን ይዤ።