በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በእቅፉ

በእቅፉ

አውርድ፦

  1. 1. ነፍሴ ተቅበዝብዛ፣

    አንዴ እዚህ፣ አንዴ ’ዛ፤

    ሕይወት ሆኖ ሥቃይ፣

    ጋርዶኝ ነበር አሻግሬ ’ንዳላይ።

    ግን ቆምኩ፣ ዳግም ብዬ ቀና፤

    እረኛዬ አይተኛምና።

    (አዝማች)

    ፈልጎ፣ አገኘኝ ፈላልጎ፤

    ተሸከመኝ በጉያው ሸሽጎ።

    ስንከራተት ባዝኜ፣ ዘመናቴም ቢያልፉ፣

    ያዘኝ እንደገና በ’ቅፉ።

  2. 2. ከንዳድ ሐሩሩ፣

    መከለያ ከቁሩ፤

    ይህ አይደለም ወይ ቦታው፣

    ሰላም ’ረፍት የሚሰጠው፣ ለቀመሰው?

    ና ቤትህ ’ባክህ ሳትሳቀቅ፤

    ናፍቋል ይሖዋ ሊያይህ ስትስቅ።

    (አዝማች)

    ፈልጎ፣ ጠራህ ወደ ቤቱ፤

    አልረሳም ፍቅርህን፣ ያን የጥንቱን።

    መቼም ዓለም፣ ዓለም ነው፤ እንባ ’ኮ ነው ትርፉ!

    ’ሚገኘው እፎይታ፣ በ’ቅፉ።

    (አዝማች)

    ብለናል እልል፣

    እንኳን በቃህ ለቤትህ!

    ደርሷል ምኞትህ።

    ኑር እዚህ ሳይነካህ ክፉ፤

    በ’ቅፉ።

    በ’ቅፉ።

    (አዝማች)

    ፈልጎ፣ አግኝቶሃል ፈላልጎ፤

    ተሸከመህ በጉያው ሸሽጎ።

    የት አለ የተሻለ፣

    ከዚህ ቦታ የላቀ፣

    ከ’ቅፉ።