በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከዓለም አካባቢ

ከዓለም አካባቢ

ከዓለም አካባቢ

“አንድ የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች ቡድን [ሃዋይ ውስጥ በሚገኝ] ማውና ኬአ በሚባል ቦታ ላይ ያሉትን ሱባሩ እና ኬክ የሚባሉ ቴሌስኮፖች በመጠቀም ከዳር እስከ ዳር ለማቋረጥ 200 ሚሊዮን የብርሃን ዓመታት በሚፈጅ ጠፈር ላይ የተንጣለሉ ሰፋፊ የከዋክብት ረጨቶችን አግኝቷል።” እነዚህ ረጨቶች አንድ ላይ ተዳምረው፣ እስከ ዛሬ ከተገኙት ሁሉ በስፋቱ ተወዳዳሪ የሌለውን የጠፈር ላይ አካል አስገኝተዋል።—ሱባሩ ቴሌስኮፕ ዌብ ሳይት፣ ጃፓን

የዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ ስታቲስቲክስ ቢሮ ያወጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው ከሆነ “[በእንግሊዝና በዌልስ] በ2006 የተፈጸሙት የጋብቻ ሥነ ሥርዓቶች ቁጥር ከዚያ በፊት በነበሩት 110 ዓመታት ውስጥ ከተፈጸሙት ሁሉ በጣም ዝቅተኛው ነበር። ሳይጋቡ አብረው የሚኖሩ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል።”—ዘ ጋርዲያን ዊክሊ፣ ብሪታንያ

የሃይማኖታዊና የሕዝባዊ ኑሮ ፎረም የተባለ ድርጅት በገለጸው መሠረት “44 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ወይ ሃይማኖታቸውን ቀይረዋል አሊያም ሃይማኖት የለሽ መሆናቸውን አቁመው አንድ ዓይነት እምነት መከተል ጀምረዋል፤ ወይም ደግሞ እስከነጭራሹ ማንኛውንም ሃይማኖታዊ ልማድ መከተል ትተዋል።”—ዩናይትድ ስቴትስ

ከተቃራኒ ፆታ ጋር “መውጣት” በኮሌጆች ውስጥ

የካቶሊክ ሃይማኖታዊ ምሑርና ረዳት የዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ዳና ፍራተስ በአሜሪካ ኮሌጆች ውስጥ ከፆታና ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ ጥናት ካካሄዱ በኋላ እንዲህ በማለት ተናግረዋል፦ “ከአንዳንድ የኤቫንጀሊክ ኮሌጆች በስተቀር . . . በሕዝብም ሆነ በግል እንዲሁም በካቶሊክ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ከተቃራኒ ፆታ ጋር ‘መውጣታቸው’ ማለትም ከተለያዩ ሰዎች ጋር የፆታ ግንኙነት መፈጸማቸው በጣም የተለመደ ሆኗል።” ፍራተስ፣ ናሽናል ካቶሊክ ሪፖርተር በተባለ ጽሑፍ ላይ እንደተናገሩት ከሆነ ሃይማኖቶች ከፆታ ጋር በተያያዘ በሰዎች ላይ በጎ ተጽዕኖ ማሳደር አለመቻላቸው “በኮሌጆች ውስጥ ከተቃራኒ ፆታ ጋር መውጣት እየተስፋፋ እንዲመጣ” ከማድረጉም በላይ “ሃይማኖቶች እንዲህ ያለውን ሥነ ምግባር የጎደለው አካሄድ ለመከላከል ምንም አቅም እንደሌላቸው” ያሳያል።

ወላጆች ሴት ልጆቻቸውን እንዲያሳድጉ ገንዘብ ተሰጣቸው

የሕንድ መንግሥት ድሃ የሆኑ ወላጆች ሴት ልጆቻቸውን እንዲያሳድጉ በአሜሪካ ዶላር ሲሰላ ወደ 3,000 የሚጠጋ ገንዘብ እንደሚሰጣቸው የቢቢሲ የዜና ዘገባ ተናግሯል። አንዲት ልጅ ከተወለደችበት ጊዜ ጀምሮ 18 ዓመት እስኪሞላት ድረስ በተለያዩ ጊዜያት ቤተሰቦቿ ገንዘብ ይሰጣቸዋል። ምንም እንኳን ሰዎች፣ የማይፈልጉት ፆታ ያለውን ጽንስ እንዳያስወርዱ የሚከለክል ሕግ በ1994 የወጣ ቢሆንም እንዲህ ያለው ድርጊት በሰፊው መሠራጨቱን ቀጥሏል። እንዲያውም ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ 10 ሚሊዮን የሚሆኑ ሴት ሕፃናት በውርጃ ሕይወታቸውን እንዳጡና ይህም በአንዳንድ አካባቢዎች በወንዶችና በሴቶች ቁጥር መካከል ልዩነት እንዲኖር እንዳደረገ ተገምቷል። በ2001 በተደረገ የሕዝብ ቆጠራ መሠረት በመላው ሕንድ የሚገኙ ከስድስት ዓመት በታች የሆኑ ልጆችን አስመልክቶ የወጣው አኃዝ እንደሚያሳየው ሬሾው ለ1,000 ወንዶች 927 ሴቶች ሲሆን ልዩነቱም እየሰፋ የሚሄድ ነበር። በአገሪቱ ካሉት ግዛቶች መካከል በአንዱ ብቻ የሚወለዱት ሕፃናት ሬሾ ለ1,000 ወንዶች 793 ሴቶች ሆኖ ተገኝቷል።

ከፍተኛ መጠን ያለው ድምፅ በወፎች ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ

አንዳንድ ወፎች ድምፃቸው በተቻለ መጠን በከተማ ውስጥ ከሚፈጠረው ጫጫታ ከፍ ብሎ እንዲሰማ ለማድረግ ይጥራሉ። ኒው ሳይንቲስት የተባለ መጽሔት እንደገለጸው ከሆነ በከተማ ውስጥ የሚሰማው ጫጫታ ሰዎችን ሊረብሽ ቢችልም ወንዶች ወፎች “የተጓዳኛቸውን ትኩረት ለመሳብና ድንበራቸውን ለማስከበር” መዘመር ስለሚኖርባቸው ጫጫታው ለወፎች ሕይወታቸውን የሚነካ ከባድ ጉዳይ ሊሆን ይችላል። በከተማ ውስጥ የሚሰማው ጫጫታ ከፍተኛ ስለሚሆን አንዳንድ ወፎች ዝማሬያቸው ይበልጥ እንዲሰማ ሌሊት ላይ ይዘምራሉ አለዚያም ድምፃቸውን በጣም ከፍ ለማድረግ ይሞክራሉ። ይህ ድምፅን ከሁኔታዎች ጋር የማስማማት ችሎታ በከተማ አካባቢ በሚኖሩ ወፎች ዘንድ ብቻ የተለመደ እንዳልሆነ መጽሔቱ አክሎ ተናግሯል። “በፏፏቴዎችና በወራጅ ወንዞች” አካባቢ የሚኖሩ ወፎችም የሚዘምሩት ከፍ ባለ ድምፅ ነው።