በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በውጥረት የተዋጡ ተማሪዎች

በውጥረት የተዋጡ ተማሪዎች

በውጥረት የተዋጡ ተማሪዎች

የአሥራ ሰባት ዓመቷ ጄኒፈር በክፍሏ ውስጥ ከፍተኛ ውጤት ከሚያመጡ ተማሪዎች መካከል አንዷ ነች። ጄኒፈር ከመደበኛ ትምህርት ሰዓት ውጪ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ትሳተፍ የነበረ ሲሆን አስተማሪዎቿና አማካሪዎቿም በአክብሮት ያዩዋታል። ይሁንና በመመረቂያዋ ዓመት ላይ ኃይለኛ ራስ ምታትና በተደጋጋሚ የሚከሰት የማቅለሽለሽ ስሜት ያጋጥማት ጀመር። የቤት ሥራዋን በምትሠራበት ጊዜ በአንድ ነገር ላይ ትኩረት አድርጋ ረጅም ሰዓት መቆየቷና በቂ እንቅልፍ አለማግኘቷ ለሕመም እንደዳረጋት ይሰማታል።

ይሁንና እንዲህ ዓይነት ችግር የገጠማት ጄኒፈር ብቻ አይደለችም። በትምህርት ቤት ከፍተኛ ውጥረት የሚያጋጥማቸው ተማሪዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ይመስላል፤ እንዲያውም አንዳንዶች የሥነ ልቦና ሐኪም እርዳታ አስፈልጓቸዋል። ከዚህም የተነሳ በአሜሪካ የሚገኝ አንድ የትምህርት ባለሙያዎች ቡድን በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚታየውን ከፍተኛ ውጥረት ለመቀነስ የሚረዳ ፕሮግራም ቀርጿል።

አንተም ተማሪ ከሆንክ ልክ እንደ ጄኒፈር የሚደርስብህን ውጥረት ለመቋቋም እየታገልክ ይሆናል። ወላጅ ከሆንክ ደግሞ ልጅህ በትምህርት ቤት ስኬታማ ለመሆን ሲል ማቆሚያ የሌለው ጫና እንደሚያጋጥመው አስተውለህ ይሆናል። ተማሪዎችም ሆኑ ወላጆቻቸው በዚህ ረገድ ሊረዳቸው የሚችል ጠቃሚ መመሪያ ከየት ማግኘት ይችላሉ?