በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ውኃ የማያስገባው የሎተስ ቅጠል

ውኃ የማያስገባው የሎተስ ቅጠል

ንድፍ አውጪ አለው?

ውኃ የማያስገባው የሎተስ ቅጠል

ራሳቸውን በራሳቸው የሚያጸዱ የፕላስቲክ ኩባያዎች፣ ዝናብ ቢዘንብባቸውም የማይረጥቡ መስኮቶች፣ እርስ በርስ ሳይፋተጉ የሚሠሩ ጥቃቅን ማሽኖች። የሎተስ ቅጠልን ሚስጥር ማወቅ ብንችል ኖሮ ከምናገኛቸው ጥቅሞች መካከል ከላይ የተጠቀሱት ጥቂቶቹ ብቻ እንደሆኑ የሳይንስ ሊቃውንት ይናገራሉ።

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ የሎተስ ቅጠል የላይኛው ክፍል በዓይን ሊታዩ በማይችሉ ጉብታዎች የተሞላ ሲሆን እነዚህ ጉብታዎች ደግሞ ቅባትነት ባለው ነገር የተሸፈኑ ናቸው። እንደ ውኃ መከላከያ ሆነው የሚያገለግሉት እነዚህ ጉብታዎች በቅጠሉ ላይ የሚያርፉትን የውኃ ጠብታዎች ወደ ውስጥ ሰርገው እንዳይገቡ ያግዷቸዋል። ቅጠሉ ጋደል ያለ መሆኑ ውኃው የቅጠሉን ገላ ሳይነካ ኮለል ብሎ እንዲወርድ ያደርገዋል። ከዚህ የተነሳ የሎተስ ቅጠል ምንጊዜም የማይረጥብ ሲሆን በላዩ ላይ ያሉት ቆሻሻዎችና አቧራ በውኃ ነጠብጣቦቹ ታጥበው ስለሚወሰዱ ቅጠሉ ሁልጊዜ ንጹሕ ነው።

የሳይንስ ሊቃውንት እንደ ሎተስ ቅጠል ሁሉ ውኃ ወደ ውስጥ እንዳይሰርግ የማገድ ባሕርይ ያላቸው ነገሮች ለመሥራት ይፈልጋሉ። በውኃ ምክንያት ሊበላሹ የሚችሉ ጥቃቅን የሆኑ ማሽኖችም እንኳ ሳይቀር የሎተስን ቅጠል የሚመስል አሠራር ቢኖራቸው ጠቃሚ ነበር። “[የሎተስን ቅጠል አፈጣጠር በመኮረጅ] ሊገኙ የሚችሉት ጥቅሞች ቁጥር ሥፍር የላቸውም” በማለት ሳይንስ ዴይሊ ዘግቧል።

ምን ይመስልሃል? የሎተስ ቅጠል በአጋጣሚ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?