በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መልስህ ምንድን ነው?

መልስህ ምንድን ነው?

መልስህ ምንድን ነው?

ከዚህ ሥዕል ውስጥ የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው?

ኢያሱ 2:15-18፤ 6:15-21፤ 7:1, 20, 21ን አንብብ። ከዚያም ሥዕሉን ተመልከት። በጥቅሱ ውስጥ ከተገለጹት ነገሮች መካከል የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው? መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ።

1. ․․․․․

2. ․․․․․

3. ․․․․․

4. ․․․․․

ለውይይት፦

የሌሎችን ንብረት መውሰድ የሌለብን ለምንድን ነው?

ከዚህ እትም

የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ፤ እንዲሁም የጎደለውን ቁጥር አሟላ።

ገጽ 5 ዳንኤል የሚታወቀው በምን ነበር? ዳንኤል 6:․․․

ገጽ 6 በሁሉም ሰው ዘንድ ምን በመሆናችን ልንታወቅ ይገባል? ፊልጵስዩስ 4:․․․

ገጽ 28 ጋብቻ በሁሉም ዘንድ ምን መሆን አለበት? ዕብራውያን 13:․․․

ገጽ 28 ምኞት ከፀነሰች በኋላ ምንን ትወልዳለች? ያዕቆብ 1:․․․

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

ስለ ነቢያት ምን የምታውቀው ነገር አለ?

ሁለተኛ ዜና መዋዕል 18:1 እስከ 19:3 አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ።

5. ․․․․․

ንጉሥ አክዓብ ይጠላው የነበረው ነቢይ ስሙ ማን ነው?

6. ․․․․․

ንጉሥ አክዓብ ይህን ነቢይ ይጠላው የነበረው ለምንድን ነው?

7. ․․․․․

ነቢዩ ለአክዓብ ምን አለው? አክዓብስ ምን አደረገ?

ለውይይት፦

ነቢዩ የነበረውን ዓይነት ድፍረት ማሳየት ያለብህ መቼ ሊሆን ይችላል?

▪ መልሶቹ ገጽ 14 ላይ ይገኛሉ

በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች

1. የኢያሪኮ ቅጥር የወደቀው እስራኤላውያን ከተማዋ ላይ ጥቃት ከመሰንዘራቸው በፊት ነበር።

2. ረዓብ መስኮት ላይ ያንጠለጠለችው ፈትል ቀለሙ ቀይ እንጂ ሰማያዊ አልነበረም።

3. አካን የሰረቀው ካባ፣ የወርቅ ቡችላና የብር ሰቅል እንጂ ጣዖት አልነበረም።

4. ጥቃቱ የተፈጸመው በማታ አልነበረም።

5. ሚክያስ።

6. ይሖዋ አምላክ በአክዓብ ላይ ያስተላለፈውን የፍርድ መልእክት ነገረው።

7. አክዓብ በጦርነቱ እንደሚሞት ነገረው። ሚክያስን እስር ቤት አስገባው።