በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መልስህ ምንድን ነው?

መልስህ ምንድን ነው?

መልስህ ምንድን ነው?

ይህ የሆነው የት ነበር?

1. ሙሴ ለእስራኤላውያን ውኃ ለማውጣት የመታው አለት የሚገኘው የት ነበር?

ፍንጭ፦ ዘኍልቍ 20:1-8ን አንብብ።

መልስህን በካርታው ላይ አክብብ።

ቃዴስ

ራፊዲም

ሲና (ኮሬብ) ተራራ

▪ በዚህ ጊዜ ሙሴና አሮን የሠሩት ስህተት ምን ነበር? የተቀጡትስ ምን ነበር?

․․․․․

ፍንጭ፦ ዘኍልቍ 20:9-13ን እና መዝሙር 106:32, 33ን አንብብ።

ለውይይት፦

ሙሴ በእስራኤላውያን ላይ የተናደደው ለምን ይመስልሃል? ቁጣህን መቆጣጠርህ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ከዚህ እትም

የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ፤ እንዲሁም የጎደለውን ቁጥር አሟላ።

ገጽ 7 መጥፎ ጓደኝነት ምን ጉዳት ያስከትላል? 1 ቆሮንቶስ 15:․․․

ገጽ 8 ምን መሆናቸውን የሚያውቁ ሰዎች ደስተኞች ናቸው? ማቴዎስ 5:․․․

ገጽ 13 አኗኗራችን ከምን ነጻ መሆን አለበት? ዕብራውያን 13:․․․

ገጽ 18 ፍቅር ምን አያደርግም? 1 ቆሮንቶስ 13:․․․

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

ስለ ነቢያት ምን የምታውቀው ነገር አለ?

አሞጽ 7:10-17ን አንብብና የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ።

2. ․․․․․

ካህኑ አሜስያስ አሞጽን ምን ብሎ ወነጀለው?

3. ․․․․․

አሞጽ፣ አሜስያስ በፌዝ ለሰነዘረበት ክስ መልስ ሲሰጥ ያሳያቸው ሁለት ባሕርያት ምንድን ናቸው?

ለውይይት፦

አንዳንድ ሰዎች ስላሾፉብህ ብቻ ስለ ይሖዋ መመሥከርህን ማቆም ይኖርብሃል? ለምን?

▪ መልሱ በገጽ 11 ላይ ይገኛል

በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች

1.  ቃዴስ።

ሙሴ ሳያስብ የተናገረ ሲሆን እሱም ሆነ አሮን ይሖዋን ቅዱስ አድርገው አላከበሩም። በመሆኑም ወደ ተስፋይቱ ምድር እንዲገቡ አልተፈቀደላቸውም።

2. በንጉሡ ላይ አሲሯል።

3. ትሕትናና ድፍረት።

[በገጽ 31 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

ካርታ፦ Based on maps copyrighted by Pictorial Archive (Near Eastern History) Est. and Survey of Israel