በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ይበልጥ አስፈላጊ ለሆነ ነገር ጊዜ ማግኘት

ይበልጥ አስፈላጊ ለሆነ ነገር ጊዜ ማግኘት

ይበልጥ አስፈላጊ ለሆነ ነገር ጊዜ ማግኘት

‘የቀረው ጊዜ አጭር ነው።’—1 ቆሮንቶስ 7:29

“ውኃ ውስጥ ገብተህ ስለተንቦራጨቅክ ብቻ እየዋኘህ ነው ማለት አይቻልም” በማለት ዎርኪንግ ስማርት በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ ማይክል ለቦፍ ጽፈዋል።

በሌላ አነጋገር አንድን ሥራ ለማከናወን በመጣርና ውጤታማ ሥራ በማከናወን መካከል ልዩነት ሊኖር ይችላል። እስቲ ስላለፈው ሳምንት ቆም ብለህ ለማሰብ ሞክር። ጊዜህ ያለፈው በምን ነበር? ብዙ ጊዜህን ያሳለፍከው ምን በመሥራት ነው? ይበልጥ አስፈላጊ ናቸው ለምትላቸው ነገሮች ተጨማሪ ጊዜ መመደብ እንዳለብህ ይሰማሃል?

ኢየሱስ በጥድፊያ የተሞላውን ዘመናችንን አስመልክቶ ምን እንደተናገረ ተመልከት። ኢየሱስ የዚህ ሥርዓት ፍጻሜ ሲደርስና ጽድቅ የሚሰፍንበት የአምላክ አዲስ ዓለም ሲቃረብ ደቀ መዛሙርቱ በሥራ እንደሚጠመዱ ተናግሯል። በየትኛው ሥራ? ‘የአምላክን መንግሥት ምሥራች’ በመስበኩ ሥራ ነው። በተጨማሪም ኢየሱስ አብዛኞቹ ሰዎች ለማዳመጥ እስከማይችሉ ድረስ በሥራ የተጠመዱ እንደሚሆኑ ተናግሯል። እነዚህ ሰዎች የተጠላለፉት በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ነው። እንዲሁም ኢየሱስ የመንግሥቱን መልእክት ማስተዋል እስከማይችሉ ድረስ በሥራ የሚጠመዱ ሰዎች ጥፋት እንደሚደርስባቸው ተናግሯል።—ማቴዎስ 24:14, 37-39፤ ሉቃስ 17:28-30

በዛሬው ጊዜ የይሖዋ ምሥክሮች የአምላክን መንግሥት ምሥራች ከ230 በላይ በሆኑ አገሮች እየሰበኩ ነው። ኢየሱስ በትንቢት እንደተናገረው ብዙ ሰዎች “በጣም ሥራ እንደሚበዛባቸው” በመናገር የይሖዋ ምሥክሮችን ማዳመጥ አይፈልጉም። ይሁንና ሥራ ቢበዛብህም ጊዜህን አመቻችተህ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አምላክ መንግሥት ምን እንደሚያስተምር እንድትመረምር እንጋብዝሃለን። አምላክ ለሰው ዘር የሚያመጣውን በረከት ስታውቅ የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት መስማትና ተግባራዊ ማድረግ በእርግጥም ይበልጥ አስፈላጊ ማለትም ጊዜ ሊመደብለት የሚገባ ነገር እንደሆነ ትስማማለህ ብለን ተስፋ እናደርጋለን። *

[የግርጌ ማስታወሻ]

^ አን.6 ተጨማሪ እውቀት ለማግኘት በአካባቢህ ያሉትን የይሖዋ ምሥክሮች እንድታነጋግር ወይም በገጽ 5 ላይ ካሉት አድራሻዎች ውስጥ አመቺ ወደሆነው እንድትጽፍ አሊያም www.watchtower.org የተባለውን ድረ ገጻችንን እንድትጎበኝ እናበረታታሃለን።