በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መስማት ለተሳናቸው ይጠቅማል”

“የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መስማት ለተሳናቸው ይጠቅማል”

“የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መስማት ለተሳናቸው ይጠቅማል”

በቼክ ሪፑብሊክ ውስጥ መስማት ለተሳናቸው ሰዎች የሚዘጋጅ አንድ መጽሔት ይህን ርዕስ ይዞ ወጥቶ ነበር። ይህን ርዕስ የጻፉት ዝዴኔክ ስትራካ የይሖዋ ምሥክሮች መስማት የተሳናቸውን ሰዎች ለመርዳት ሲሉ የምልክት ቋንቋ በመማራቸው አመስግነዋቸዋል።

ሚስተር ስትራካ ይህን ርዕስ እንዲጽፉ ያነሳሳቸው ምን ነበር? እኚህ ሰው በ2006 በፕራግ በተደረገው የይሖዋ ምሥክሮች የአውራጃ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ነበር፤ በስብሰባው ላይ የነበሩትን 70 መስማት የተሳናቸው ሰዎች ለመርዳት ሲባል ፕሮግራሙ በምልክት ቋንቋ ሲተረጎም ተመልክተዋል። የይሖዋ ምሥክሮች በየዓመቱ በዓለም ዙሪያ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትን ለመማርና እርስ በርስ ለመበረታታት ትልልቅ ስብሰባዎችን ያደርጋሉ። በእነዚህ ስብሰባዎች ላይ መስማት የተሳናቸው ሰዎችም ይገኛሉ። በቅርብ ባለፈ አንድ ዓመት ውስጥ በዓለም ዙሪያ ከተደረጉት ትልልቅ ስብሰባዎች መካከል 96ቱ በምልክት ቋንቋ ብቻ የቀረቡ ሲሆን በሌሎች 95 ቦታዎች ደግሞ ፕሮግራሙ ወደ ምልክት ቋንቋ ተተርጉሟል።

በፕራግ የአውራጃ ስብሰባ በተደረገበት ወቅት በዚያች ከተማ ያለው በምልክት ቋንቋ የሚካሄድ ጉባኤ አባላት 30 የሚያህሉ መስማት የተሳናቸው ግለሰቦችን መጽሐፍ ቅዱስ ያስጠኑ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስን የሚያጠኑት ሰዎች የሚማሩት ነገር እየጠቀማቸው እንደሆነ ከሚከተለው ተሞክሮ መመልከት ይቻላል።

ማርኬታ፣ ከሞንጎሊያ የመጣችን አንዲት መስማት የተሳናት ሴት መጽሐፍ ቅዱስን ለማስተማር በየሳምንቱ ከ100 ኪሎ ሜትር በላይ ትጓዛለች። የቼክና የሞንጎሊያ የምልክት ቋንቋዎች በጣም ስለሚለያዩ ማርኬታ ትምህርቱ ለተማሪዋ እንዲገባት ለማድረግ ዘዴ መፍጠር አስፈልጓታል። ይሁንና የማርኬታ ልፋት ከንቱ አልሆነም። ሁለተኛ ልጇን አርግዛ የነበረችው የማርኬታ ጥናት ለማስወረድ አስባ የነበረ ቢሆንም አመለካከቷ ተቀየረ። ማርኬታ እንዲህ ትላለች፦ “ስለ ጉዳዩ ስጠይቃት በምልክት ‘ይሖዋ ማስወረድን አይፈቅድም’ በማለት መለሰችልኝ። አምላክ ስለ ሕይወት ያለውን አመለካከት እንደተረዳች ስገነዘብ በጣም ደስ አለኝ!” *

በዓለም ዙሪያ መስማት የተሳናቸው ብዙ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አማካኝነት ስለ አምላክ ትክክለኛ እውቀት እያገኙ ነው። እነዚህ ሰዎች ወደ አምላካቸው ይበልጥ እየቀረቡና ደስታቸውም እየጨመረ በመሄዱ ሕይወታቸው እየተሻሻለ ነው።—ኢሳይያስ 48:17, 18

[የግርጌ ማስታወሻ]

^ አን.5 መጽሐፍ ቅዱስ ፅንስ ማስወረድን በተመለከተ ምን እንደሚል ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የሰኔ 2009 ንቁ! ከገጽ 3-9 ተመልከት።

[በገጽ 26 እና 27 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

ይህን ያውቁ ኖሯል?

የይሖዋ ምሥክሮች በ43 የምልክት ቋንቋዎች የተዘጋጁ የዲቪዲ ፕሮግራሞችን አውጥተዋል። መስማት የተሳናቸው ሰዎች ዳውንሎድ ሊያደርጓቸው የሚችሉ ሌሎች የማስተማሪያ መሣሪያዎችን www.pr418.com በሚለው ድረ ገጽ ላይ ማግኘት ይችላሉ።

የይሖዋ ምሥክሮች፣ መስማት የተሳናቸው ሰዎች ተጨማሪ ጽሑፎችን ማግኘት እንዲችሉ በዓለም ዙሪያ ወደ 59 የምልክት ቋንቋዎች የሚተረጉሙ የትርጉም ቡድኖችን አደራጅተዋል።

በዓለም ዙሪያ በምልክት ቋንቋ የሚካሄዱ ከ1,200 የሚበልጡ የይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤዎች አሉ።

[በገጽ 26 ላይ የሚገኝ ሥዕላዊ መግለጫ]

(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)

www.pr418.com