በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

ከዚህ ሥዕል ውስጥ የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው?

2 ነገሥት 4:8-10⁠ን አንብብ። ከዚያም ሥዕሉን ተመልከት። በጥቅሱ ውስጥ ከተገለጹት መካከል የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው? መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ። እንዲሁም ሥዕሉ የተሟላ እንዲሆን ነጥቦቹን በመስመር ካገናኘህ በኋላ ተስማሚ የሆነውን ቀለም ቀባ።

1.․․․․

2.․․․․․

3.․․․․․

[ሥዕል]

(ጽሑፉን ተመልከት)

ለውይይት፦

ይህች ሴት ምን የደግነት ተግባር ፈጽማለች? የእሱን ነቢይ በመርዳቷ ይሖዋ የባረካት እንዴት ነው?

ፍንጭ፦ 2 ነገሥት 4:32-37⁠ን አንብብ።

አንተስ በዛሬው ጊዜ ለሚገኙ የይሖዋ አገልጋዮች ደግነት ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?

ፍንጭ፦ ሮም 12:13⁠ን እና ገላትያ 6:10⁠ን አንብብ።

ቤተሰብን የሚያሳትፍ፦

አንድ የቤተሰባችሁ አባል ከላይ በተጠቀሰው የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ ካሉት ሰዎች መካከል አንዱ ያደረገውን ሁኔታ ምንም ድምፅ ሳይሰማ በእንቅስቃሴ ያሳይ። የቀሩት የቤተሰብ አባላት ደግሞ ማንን እያስመሰለ እንደሆነ ለማወቅ ጥረት ያድርጉ።

ካርድ በመሰብሰብ መማር

ቆርጠህ አውጣውና ለሁለት አጥፈህ አስቀምጠው

የመጽሐፍ ቅዱስ ካርድ 2

ጥያቄ

ሀ. ዳንኤል ወደ አንበሶች ጉድጓድ የተጣለው ለምንድን ነው?

ለ. ሦስቱ የዳንኤል ጓደኞች የዕብራይስጥ ስማቸው ማን ይባላል?

ሐ. ዳንኤል በየትኞቹ ሁለት የውጪ መንግሥታት ሥር አገልግሏል?

[ሠንጠረዠ]

4026 ዓ.ዓ. አዳም ተፈጠረ

ዳንኤል የኖረበት ዘመን 600ዎቹ ዓ.ዓ. ገደማ

1 ዓ.ም.

98 ዓ.ም. የመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተጻፈ

[ካርታ]

ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ተወስዷል

ኢየሩሳሌም

ባቢሎን

ዳንኤል

አጭር የሕይወት ታሪክ

ከይሁዳ ነገድ የተወለደ የንጉሣዊ ቤተሰብ ልጅ ሳይሆን አይቀርም። በስሙ የሚጠራውን በመንፈስ መሪነት የተጻፈ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የጻፈ ታማኝ ነቢይ ነበር። ናቡከደናፆር እሱንና ሌሎች የንጉሣዊ ቤተሰብ አባላትን በምርኮ ወደ ባቢሎን ሲወስዳቸው ዳንኤል በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ሳይሆን አይቀርም።

መልስ

ሀ. መጸለይን የሚከለክል ሕግ ቢወጣም እንኳ ወደ ይሖዋ በመጸለዩ።—ዳንኤል 6:6-17

ለ. አናንያ፣ ሚሳኤልና አዛርያ።—ዳንኤል 1:6, 7

ሐ. ባቢሎንና ሜዶ ፋርስ።—ዳንኤል 5:30፤ 6:8

ሕዝቦችና አገሮች

4. ስማችን ሆርሂ፣ ኒኮላስ እና ፕሪሲልያን ይባላል። የምንኖረው በማዕከላዊ አሜሪካ በምትገኘው በቤሊዝ ነው። በቤሊዝ ምን ያህል የይሖዋ ምሥክሮች ያሉ ይመስልሃል? 600፣ 2,000 ወይስ 3,500?

5. የምንኖርበትን አገር የሚጠቁመው ፊደል የትኛው ነው? ይህን ፊደል አክብብ፤ ከዚያም አንተ በምትኖርበት አገር ላይ ምልክት አድርግ፤ የምትኖርበት አገር ከቤሊዝ ምን ያህል እንደሚርቅ ለመገመት ሞክር።

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

● በገጽ 30 እና 31 ላይ የሚገኙት ጥያቄዎች መልስ በገጽ 28 ላይ ይገኛል

በገጽ 30 እና 31 ላይ የሚገኙት ጥያቄዎች መልስ

1. አልጋ።

2. ጠረጴዛ።

3. ወንበር።

4. 2,000

5. ሀ።