በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለልብና ለጤንነት የሚበጅ ጥበብ

ለልብና ለጤንነት የሚበጅ ጥበብ

ለልብና ለጤንነት የሚበጅ ጥበብ

“ሰላም ያለው ልብ ለሰውነት ሕይወት ይሰጣል።”​—ምሳሌ 14:30

“ደስተኛ ልብ ጥሩ መድኀኒት ነው።”​—ምሳሌ 17:22

● እነዚህን ያልተወሳሰቡ እና ጥልቅ ትርጉም ያላቸው ሐሳቦች የተናገረው ከሦስት ሺህ ዓመታት በፊት የኖረው ሰለሞን የተባለ የእስራኤል ንጉሥ ነው። * ይሁንና እነዚህ ጥቅሶች የያዙት መልእክት እውነት ነው? ዘመናዊ ሕክምና ይህን በተመለከተ ምን ይላል?

ሰላም ያለው ልብ ያላቸውን ሰዎች እና ቁጣ የሚቀናቸውን ሰዎች በተመለከተ ጆርናል ኦቭ ዚ አሜሪካን ኮሌጅ ኦቭ ካርዲዮሎጂ እንዲህ ይላል፦ ‘በአሁኑ ጊዜ ያሉ የምርምር ውጤቶች እንደሚጠቁሙት ቁጣና ጥላቻ ለልብ ሕመም አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።’ በመሆኑም ይህ መጽሔት እንዲህ ብሏል፦ “የልብ ሕመምን በመከላከልና በማከም ረገድ ውጤታማ ለመሆን . . . ከተለመደው የፊዚዮቴራፒና በመድኃኒቶች አማካኝነት የሚደረግ ሕክምና በተጨማሪ ቁጣንና ጥላቻን በመቆጣጠር ላይ ያተኮረ ሥነ ልቦናዊ ሕክምና ሊያስፈልግ ይችላል።” በቀላል አነጋገር፣ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው ሰላም ያለው ልብ ለጥሩ ጤንነት አስተዋጽኦ ያበረክታል።

ደስተኛ ልብም እንዲሁ ለጤና ጠቃሚ ነው። ዶክተር ዴረክ ካክስ የሚባሉ በስኮትላንድ የጤና ባለሙያ ሆነው የሚሠሩ ሰው በቢቢሲ የዜና አገልግሎት ባቀረቡት ዘገባ ላይ “ደስተኛ ከሆንክ ወደፊት በአካላዊ ሕመም የመሠቃየት አጋጣሚህ ደስተኛ ካልሆኑ ሰዎች ያነሰ ነው” በማለት ተናግረዋል። ይኸው ዘገባ እንዲህ ብሏል፦ “ደስተኛ የሆኑ ሰዎች እንደ ልብ ሕመምና በጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ ባሉት የጤና እክሎች የመጠቃት አጋጣሚያቸው አነስተኛ ነው።”

ሌሎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች ያሰፈሩትን ሐሳብ ሳናነሳ ሰለሞን የጻፈውን ጥበብ ያዘለ ሐሳብ ብቻ እንኳ ብንወስድ ሰለሞን ከዘመኑ እጅግ የቀደመ ሐሳብ ሊጽፍ የቻለው እንዴት ነው? ብለን ለመጠየቅ እንነሳሳለን። መልሱ ቀላል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ “አምላክ ለሰሎሞን ጥበብንና እጅግ ታላቅ ማስተዋልን . . . ሰጠው” ይላል። (1 ነገሥት 4:29) ደግሞም ይህ ጥበብ ያዘለ ሐሳብ ሁሉም ሰው ሊጠቀምበት እንዲችል በቀላል ቋንቋ ተመዝግቦ ይገኛል። መልእክቱንም በነፃ ማግኘት ይቻላል!

ታዲያ መጽሐፍ ቅዱስን ለምን አዘውትረህ አታነብም? እንዲህ ብታደርግ “ጥበብ ልብህ ውስጥ [ትገባለች]፤ ዕውቀትም ነፍስህን ደስ ታሰኛለች፤ የመለየት ችሎታ ይጋርድሃል፤ ማስተዋልም ይጠብቅሃል።” በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ይህን በመገንዘባቸው ደስታ አግኝተዋል። (ምሳሌ 2:10, 11) ይህ በጣም የሚያበረታታ ሐሳብ አይደለም?

[የግርጌ ማስታወሻ]

^ አን.4 “ልብ” የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ የሚያመለክተው የአንድን ሰው ስሜት ጨምሮ ውስጣዊ ማንነቱን በአጠቃላይ ነው።