በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

በዚህ ሥዕል ላይ ምን ስህተቶች ይታዩሃል?

ዮሐንስ 2:13-17ን አንብብ። በዚህ ሥዕል ላይ ስህተት የሆኑት አራት ነገሮች ምንድን ናቸው? መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ። እንዲሁም ሥዕሉ የተሟላ እንዲሆን ተስማሚ የሆነውን ቀለም ቀባ።

1. ․․․․․

2. ․․․․․

3. ․․․․․

4. ․․․․․

ለውይይት፦

ኢየሱስ እነዚህን ሰዎች ከቤተ መቅደሱ ያባረራቸው ለምንድን ነው?

ፍንጭ፦ ማርቆስ 11:17⁠ን አንብብ።

እነዚህ ሰዎች ቤተ መቅደሱ ውስጥ መግዛታቸውና መሸጣቸው ስህተት የነበረው ለምንድን ነው?

ፍንጭ፦ 2 ቆሮንቶስ 2:17⁠ን አንብብ።

ይሖዋን ማስደሰት ከፈለግን እሱን ለማገልገል የሚገፋፋን ምን ሊሆን ይገባል?

ፍንጭ፦ ማቴዎስ 22:36-40⁠ን እና 1 ጴጥሮስ 5:2⁠ን አንብብ።

ቤተሰብን የሚያሳትፍ፦

እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል፣ ለይሖዋና ለሌሎች ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ ፍቅር ማሳየት የሚችልበትን አንድ ድርጊት በወረቀት ላይ እንዲጽፍ ወይም ይህንን የሚያሳይ ሥዕል እንዲስል አድርጉ። ወረቀቶቹን ለቤተሰባችሁ አባላት አሳዩአቸው፤ ከዚያም በቤተሰብ አንድ ላይ ሆናችሁ ይህንን መቼ እንደምታደርጉ እቅድ አውጡ።

ካርድ በመሰብሰብ መማር

ቆርጠህ አውጣውና ለሁለት አጥፈህ አስቀምጠው

የመጽሐፍ ቅዱስ ካርድ 16 ጢሞቴዎስ

ጥያቄ

ሀ. ይህን ዓረፍተ ነገር አሟላ። የጢሞቴዎስ እናት ․․․․․ እና አያቱ ․․․․․ ጢሞቴዎስን ከ ․․․․․ ጀምሮ ‘ቅዱሳን መጻሕፍትን’ አስተምረውታል።

ለ. ወጣቱ ጢሞቴዎስ የተቀበለው ልዩ ግብዣ ምንድን ነው?

ሐ. ጳውሎስ ስለ ጢሞቴዎስ እንዲህ ብሏል፦ “ስለ እናንተ ጉዳይ ከልብ የሚጨነቅ . . .”

[ሰንጠረዥ]

4026 ዓ.ዓ. አዳም ተፈጠረ

በአንደኛው መቶ ዘመን ዓ.ም. ጢሞቴዎስ የኖረበት ዘመን

1 ዓ.ም.

98 ዓ.ም. የመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተጻፈ

[ካርታ]

የኖረው በልስጥራ ቢሆንም በኢቆንዮን ባሉ ወንድሞች ዘንድ በመልካም ምግባሩ ተመሥክሮለታል

ልስጥራ

ኢቆንዮን

ኢየሩሳሌም

ጢሞቴዎስ

አጭር የሕይወት ታሪክ፦

ጢሞቴዎስ፣ አባቱ የማያምን ቢሆንም እንኳ “ታማኞች ለሆኑት በንግግር፣ በምግባር፣ በፍቅር፣ በእምነትና በንጽሕና አርዓያ” መሆን ችሏል። (1 ጢሞቴዎስ 4:12) “ለአምላክ ማደርን ግብ አድርገህ ራስህን አሠልጥን” የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ምክር ተግባራዊ አድርጓል። (1 ጢሞቴዎስ 4:7) ጢሞቴዎስ ለ15 ዓመታት ያህል ሐዋርያው ጳውሎስን በአገልግሎቱ አግዞታል።

መልስ

ሀ. ኤውንቄ፣ ሎይድ፣ ጨቅላነቱ።—2 ጢሞቴዎስ 1:5፤ 3:14, 15

ለ. ከሐዋርያው ጳውሎስ ጋር እየተጓዘ ማገልገል።—የሐዋርያት ሥራ 16:1-5

ሐ. “. . . እንደ እሱ ያለ በጎ አመለካከት ያለው ሌላ ማንም የለኝም።”—ፊልጵስዩስ 2:20

ሕዝቦችና አገሮች

5. ጋብሪኤላ እና ራውል እንባላለን፤ የ6 እና የ9 ዓመት ልጆች ስንሆን የምንኖረው በብራዚል ነው። በብራዚል ምን ያህል የይሖዋ ምሥክሮች ያሉ ይመስልሃል? 467,000፣ 607,000 ወይስ 720,000?

6. የምንኖርበትን አገር የሚጠቁመው ፊደል የትኛው ነው? በፊደሉ ላይ አክብብ፤ ከዚያም አንተ በምትኖርበት አገር ላይ ምልክት አድርግ፤ የምትኖርበት አገር ከብራዚል በጣም ይርቃል?

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

“ቤተሰብ የሚወያይበት” የሚለውን ዓምድ ተጨማሪ ቅጂ ለማግኘት www.pr418.com ከተባለው ድረ ገጽ ላይ ማተም ይቻላል።

● “ቤተሰብ የሚወያይበት” መልሶች በገጽ 25 ላይ ይገኛሉ

በገጽ 30 እና 31 ላይ ያሉት ጥያቄዎች መልስ

1. ኢየሱስ ሰዎቹን ያባረረው በሰይፍ ሳይሆን በጅራፍ ነበር።

2. ሰዎቹ የሚሸጡት ከብቶችንና በጎችን እንጂ አሳማዎችን አልነበረም።

3. ሰዎቹ የሚሸጡት ጉጉቶችን ሳይሆን ርግቦችን ነበር።

4. የገንዘብ መንዛሪዎቹ የያዙት ሳንቲሞች እንጂ የወረቀት ገንዘብ አልነበረም።

5. 720,000

6. ሐ