በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ወደፊት ምን ለውጥ ይመጣል?

ወደፊት ምን ለውጥ ይመጣል?

ወደፊት ምን ለውጥ ይመጣል?

“ሕዝብ በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም።”

“‘ታምሜአለሁ’ የሚል አይኖርም።”

“ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም።”

ከላይ ያሉት ሐሳቦች ለማመን የሚከብዱ ይመስላሉ። ይሁን እንጂ እነዚህ ተስፋዎች የሕልም እንጀራ እንዳልሆኑ እርግጠኞች መሆን እንችላለን። እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው? ምክንያቱም እነዚህ ቃሎች ዓለምን የመለወጥ አቅም የሌላቸው ፖለቲከኞች የሰጧቸው ባዶ ተስፋዎች አይደሉም። ከዚህ ይልቅ ከላይ የተጠቀሱት ተስፋዎች የተወሰዱት ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነው። *

ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ለዘመናችን የማይጠቅም ጥንታዊ መጽሐፍ እንደሆነ ይሰማቸዋል። አንተስ የሚሰማህ እንደዚህ ነው? ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ለምን ጠለቅ ብለህ አትመረምርም? እንደ እውነቱ ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስ የሰውን ዘር ታሪክ ከመጀመሪያው አንስቶ የሚተርክ ብቸኛ መጽሐፍ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ለሚከተሉት ጉዳዮች በቂ ማብራሪያ ይሰጣል፦

● የሰው ልጅ ችግር ላይ የወደቀው እንዴት እንደሆነ​—ሮም 5:12

● አምላክ ሁኔታውን ለማስተካከል ምን እርምጃ እንደወሰደ​—ዮሐንስ 3:16

● መንግሥታት ዓለማችንን መለወጥ የተሳናቸው ለምን እንደሆነ​—ኤርምያስ 10:23

● አምላክ ዓለምን እንደሚለውጥ በሰጠው ተስፋ ላይ እምነት መጣል የምንችለው ለምን እንደሆነ​—ኢያሱ 23:14

አምላክ በእርግጥ ረሃብን፣ ጦርነትን፣ በሽታንና ሞትን ከምድር ገጽ ያስወግዳል? የሚከተሉትን ሐቆች ከተቀበልክ ይህ ተስፋ እንደሚፈጸም ማመን ከባድ አይሆንብህም።

1. አምላክ ፈጥሮናል።

2. እሱ ስለ እኛ ያስባል።

3. አምላክ ዓለምን ለመለወጥ የሚያስችል ኃይል አለው።

4. ይህንን የማድረግ ዓላማም አለው።

እነዚህን አራት ሐቆች እንድንቀበል የሚያደርገን በቂ ማስረጃ አለ? የዚህ መጽሔት አዘጋጅ የሆኑት የይሖዋ ምሥክሮች መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት ማስረጃዎቹን ራስህ እንድትመረምር ይጋብዙሃል።

ምናልባት መጽሐፍ ቅዱስ ይኖርህ ይሆናል። ይሁንና የምታነበው አልፎ አልፎ ብቻ ሊሆን ይችላል፤ አሊያም ጭራሹኑ አንብበኸው አታውቅ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስን የሚያነቡ ብዙ ሰዎችም እንኳ በውስጡ ያለውን ሐሳብ መረዳት እንደሚከብዳቸው ይናገራሉ። አንተም እንደዚህ የሚሰማህ ከሆነ ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር ተገናኝተህ መጽሐፍ ቅዱስን በነፃ እንድታጠና እንጋብዝሃለን። በመላው ዓለም የሚኖሩ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከዚህ ዝግጅት ጥቅም እያገኙ ነው። ለመሆኑ ይህ ጥናት የሚካሄደው እንዴት ነው?

አንድ የይሖዋ ምሥክር ቤትህ ድረስ ወይም አመቺ የሆነ ሌላ ቦታ በመምጣት አለምንም ክፍያ በየሳምንቱ መጽሐፍ ቅዱስን ሊያስጠናህ ይችላል። በዚህ መልክ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናትህ እንደሚከተሉት ላሉ ጥያቄዎች መልስ እንድታገኝ ይረዳሃል፦ መከራ የሚደርስብን ለምንድን ነው? ሰብዓዊ መንግሥታት ዓለምን መለወጥ ያቃታቸው ለምንድን ነው? የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? ይህ መንግሥት ሰብዓዊ መንግሥታት ያቃታቸውን ነገር ማከናወን የሚችለውስ እንዴት ነው? *

መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ስለሚያስገኘው ጥቅም ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከፈለግህ በአካባቢህ ያሉትን የይሖዋ ምሥክሮች ማናገር አሊያም www.pr418.com የተባለውን ድረ ገጽ መመልከት ትችላለህ። በተጨማሪም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከተዘረዘሩት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መጻፍ ትችላለህ።

[የግርጌ ማስታወሻዎች]

^ አን.5 በዚህ ገጽ አናት ላይ የሚገኙት ጥቅሶች የተወሰዱት ከኢሳይያስ 2:4፣ ከኢሳይያስ 33:24 እና ከራእይ 21:4 ነው።

^ አን.18 በተጨማሪም በዚህ መጽሔት ገጽ 26 እና 27 ላይ የሚገኘውን “መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?​—ዓለምን መለወጥ የሚችለው ማን ነው?” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።