በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከውጥረት እፎይታ ማግኘት

ውጥረት አለብህ?

ውጥረት አለብህ?

“ሁሉም ሰው በተወሰነ ደረጃ ውጥረት አለበት፤ እኔ ግን ውጥረት ከአቅሜ በላይ ሆኖብኛል። ውጥረት ያስከተለብኝ፣ አንድ ትልቅ ችግር ሳይሆን የየዕለቱ ውጣ ውረድ እንዲሁም አካላዊና አእምሯዊ ሕመም ያለበትን ባለቤቴን ለብዙ ዓመታት ማስታመሜ የፈጠረብኝ ጫና ነው።”—ጂል a

“ባለቤቴ ጥላኝ ስለሄደች ሁለት ልጆች ያሳደግኩት ብቻዬን ነው። ልጆችን ያለእናት ማሳደግ በጣም ከባድ ነው። በዚያ ላይ ደግሞ ከሥራ ተባረርኩ፤ መኪናዬን የማሠራበት ገንዘብ እንኳ አልነበረኝም። ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ገባኝ። ውጥረቱ ከአቅሜ በላይ ሆኖብኝ ነበር። ራስን ማጥፋት ትክክል እንዳልሆነ ስለተሰማኝ አምላክ ሕይወቴን እንዲወስድና ከዚህ መከራ እንዲገላግለኝ ለመንኩት።”—ባሪ

አንተስ እንደ ጂልና እንደ ባሪ፣ ውጥረት ከአቅምህ በላይ እንደሆነብህ ይሰማሃል? ከሆነ ቀጣዮቹ ርዕሶች እንደሚያጽናኑህና እንደሚረዱህ ተስፋ እናደርጋለን። በርዕሶቹ ውስጥ የውጥረት መንስኤ ምን እንደሆነ፣ ውጥረት ምን ጉዳት እንደሚያስከትል እንዲሁም በተወሰነ መጠንም ቢሆን ከውጥረት እፎይታ ማግኘት የምንችለው እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን።

a ስሞቹ ተቀይረዋል።