በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክፍል 1

ከፍጥረት እስከ ጥፋት ውኃ

ከፍጥረት እስከ ጥፋት ውኃ

ሰማይና ምድር ከየት መጡ? ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት እንዲሁም በምድር ላይ ያሉት ብዙ ነገሮች እንዴት ተገኙ? መጽሐፍ ቅዱስ በአምላክ የተፈጠሩ ነገሮች መሆናቸውን በመግለጽ ትክክለኛውን መልስ ይሰጠናል። ስለዚህ መጽሐፋችን ስለ ፍጥረት ሥራዎች በሚተርኩት የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ይጀምራል።

የመጀመሪያዎቹ የአምላክ ፍጥረታት ልክ እንደ እርሱ መንፈሳዊ አካል ያላቸው ፍጥረታት ናቸው። እነዚህ ፍጥረታት መላእክት ይባላሉ። ምድር ግን የተፈጠረችው እንደኛው ላሉ ሰዎች ነው። ስለዚህ አምላክ አዳምና ሔዋን የተባሉትን ወንድና ሴት ፈጥሮ ውብ በሆነ የአትክልት ስፍራ አስቀመጣቸው። ይሁን እንጂ አምላክን ሳይታዘዙ ስለ ቀሩ ለዘላለም በሕይወት የመኖር መብት አጡ።

አዳም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ታላቁ የጥፋት ውኃ ድረስ በጠቅላላው 1, 656 ዓመታት አልፈዋል። በዚህ ጊዜ ውስጥ ብዙ መጥፎ ሰዎች ኖረዋል። በዓይን የማይታዩ መንፈሳዊ አካሎች ማለትም ሰይጣንና ክፉ መላእክቱ በሰማይ ነበሩ። በምድር ላይ ደግሞ ለየት ያለ ኃይል የነበራቸውን አንዳንድ ሰዎች ጨምሮ ቃየንና ሌሎች ብዙ ክፉ ሰዎች ነበሩ። ነገር ግን እንደ አቤል፣ ሄኖክና ኖኅ ያሉ ጥሩ ሰዎችም በምድር ላይ ነበሩ። በክፍል አንድ ውስጥ ስለ እነዚህ ሰዎችና በዚያን ጊዜ ስለተከናወኑት ሁኔታዎች እናነባለን።