በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምዕራፍ 2

ውብ የአትክልት ቦታ

ውብ የአትክልት ቦታ

ምድር ምን እንደምትመስል ተመልከት! ሁሉም ነገር በጣም ቆንጆ ነው! እስቲ ሣሩን፣ ዛፎቹን፣ አበቦቹንና እንስሳቱን በሙሉ ተመልከት። ዝሆኑንና አንበሶቹን ለይተህ ማመልከት ትችላለህ?

ይህ ውብ የአትክልት ስፍራ ከየት መጣ? አምላክ ምድርን ለእኛ እንዴት አድርጎ እንዳዘጋጃት እንመልከት።

በመጀመሪያ አምላክ በምድር ሁሉ ላይ አረንጓዴ ሣር አበቀለ። በተጨማሪም ብዙ ዓይነት ትናንሽ ዕፅዋትን፣ ቁጥቋጦዎችንና ዛፎችን አበቀለ። እነዚህ ዕፅዋት መሬትን ውብ ያደርጓታል። ይሁን እንጂ ከዚህም የበለጠ ጥቅም አላቸው። ብዙዎቹ ዕፅዋት ጥሩ ጣዕም ያላቸውን ምግቦች ይሰጡናል።

በኋላም አምላክ በውኃ ውስጥ የሚዋኙ ዓሦችንና በሰማይ ላይ የሚበሩ ወፎችን ፈጠረ። አምላክ ውሾችን፣ ድመቶችንና ፈረሶችን እንዲሁም ትላልቅና ትናንሽ እንስሳትን ፈጠረ። በቤታችሁ አካባቢ ምን ዓይነት እንስሳት ይገኛሉ? አምላክ እነዚህን ሁሉ ስለ ፈጠረልን ደስ ሊለን አይገባምን?

በመጨረሻም አምላክ አንድን የተወሰነ የምድር ክፍል በጣም ልዩ አድርጎ አዘጋጀ። ይህንንም የኤደን የአትክልት ስፍራ ብሎ ጠራው። በጣም ጥሩ ቦታ ነበር። በዚያ ቦታ ያለው ነገር ሁሉ ውብ ነበር። አምላክ መላዋ ምድር ልክ እንደዚህ ውብ የአትክልት ስፍራ እንድትሆን ፈልጎ ነበር።

ይሁን እንጂ ይህን የአትክልት ቦታ የሚያሳየውን ሥዕል እስቲ እንደገና ተመልከተው። አምላክ የጎደለ ነገር እንዳለ ተረድቶ ነበር፤ ያ ነገር ምን እንደሆነ ታውቃለህ? ምን እንደሆነ እስቲ እንመልከት