በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምዕራፍ 8

በምድር ላይ የነበሩ ግዙፍ ሰዎች

በምድር ላይ የነበሩ ግዙፍ ሰዎች

ከርዝመቱ የተነሳ የቤትህን ጣሪያ ሊነካ የሚችል አንድ ሰው ወዳንተ ሲመጣ ብትመለከት ምን ይሰማህ ነበር? ይህ ሰው በጣም ግዙፍ መሆን አለበት! በአንድ ወቅት በምድር ላይ ግዙፍ ሰዎች ነበሩ። አባቶቻቸው ከሰማይ የወረዱ መላእክት እንደነበሩ መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል። ነገር ግን ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?

ክፉው መልአክ ሰይጣን ችግር ለመፍጠር ይሯሯጥ እንደነበረ አስታውስ። ሌላው ቀርቶ የአምላክ መላእክት ክፉ እንዲሆኑ ለማድረግ ይጥር ነበር። ከጊዜ በኋላ ከእነዚህ መላእክት መካከል አንዳንዶቹ ሰይጣንን መስማት ጀመሩ። አምላክ በሰማይ እንዲሠሩ የሰጣቸውን ሥራ መሥራት አቆሙ። ከዚያ በኋላ ወደ ምድር ወርደው የሰው አካል ለበሱ። ለምን እንደሆነ ታውቃለህ?

እነዚህ የአምላክ ልጆች ይህን ያደረጉት በምድር ላይ የነበሩትን ቆንጆ ሴቶች አይተው ከእነርሱ ጋር ለመኖር ስለ ፈለጉ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ስለዚህ ወደ ምድር መጡና እነዚህን ሴቶች አገቧቸው። መጽሐፍ ቅዱስ ይህ ድርጊት ትክክል እንዳልሆነ ይናገራል፤ ምክንያቱም አምላክ እነዚህን መላእክት የፈጠራቸው በሰማይ እንዲኖሩ ነው።

እነዚህ መላእክትና ሚስቶቻቸው ልጆች ሲወልዱ የተወለዱት ልጆች የተለዩ ነበሩ። መጀመሪያ እምብዛም ልዩ አልነበሩም ይሆናል። ይሁን እንጂ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደጉና ይበልጥ ጠንካራ እየሆኑ ሄዱና በጣም ግዙፍ ሆኑ።

እነዚህ ግዙፍ ሰዎች ክፉዎች ነበሩ። ግዙፎችና ኃይለኞች ስለ ነበሩ ሰዎችን ያሠቃዩ ነበር። ሁሉም ሰው እንደ እነርሱ ክፉ እንዲሆን ለማስገደድ ይሞክሩ ነበር።

ሄኖክ ቢሞትም እንኳ በምድር ላይ አንድ ጥሩ ሰው ነበር። ይህ ሰው ኖኅ ይባላል። ኖኅ ሁልጊዜ አምላክ ያዘዘውን ያደርግ ነበር።

አምላክ ክፉ ሰዎችን በሙሉ የሚያጠፋበት ጊዜ እንደ ደረሰ ለኖኅ ነገረው። ሆኖም አምላክ ኖኅንና ቤተሰቡን እንዲሁም ብዙ እንስሳትን ከጥፋቱ ለማዳን አስቧል። አምላክ ይህን ያደረገው እንዴት እንደሆነ እስቲ እንመልከት