በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምዕራፍ 15

የሎጥ ሚስት ወደ ኋላ ተመለከተች

የሎጥ ሚስት ወደ ኋላ ተመለከተች

ሎጥና ቤተሰቡ ከአብርሃም ጋር በከነዓን ምድር ይኖሩ ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን አብርሃም ሎጥን ‘በዚህ ቦታ ለእንስሶቻችን በሙሉ የሚበቃ መሬት የለም። እባክህን እንለያይ። አንተ በዚህ ብትሄድ እኔ በዚያ እሄዳለሁ’ አለው።

ሎጥ ምድሪቱን በደንብ ተመለከተ። ውኃ ያለበትንና ለእንስሳቱ የሚሆን ብዙ ጥሩ ሣር የሚገኝበትን በጣም የሚያምር አካባቢ አየ። ይህ በዮርዳኖስ ክልል ውስጥ የሚገኝ ቦታ ነበር። ስለዚህ ሎጥ ቤተሰቡንና እንስሶቹን ይዞ ወደዚያ ሄደ። በመጨረሻም በሰዶም ከተማ ውስጥ መኖር ጀመሩ።

የሰዶም ሰዎች በጣም መጥፎዎች ነበሩ። ሎጥ ጥሩ ሰው ስለ ነበር ይህ ሁኔታ አበሳጭቶት ነበር። አምላክም ቢሆን ተቆጥቶ ነበር። በመጨረሻ አምላክ ሰዎቹ መጥፎዎች በመሆናቸው የተነሳ ሰዶምንና በአቅራቢያው የነበረችውን ጎሞራ የተባለች ከተማ ሊያጠፋቸው መሆኑን ለሎጥ እንዲነግሩ ሁለት መላእክት ላከ።

መላእክቱ ሎጥን ‘ቶሎ በል! ሚስትህንና ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ይዘህ ከዚህ ከተማ ውጣ!’ አሉት። ሎጥና ቤተሰቡ ትንሽ ስለ ዘገዩ መላእክቱ እጃቸውን ይዘው ከከተማው አስወጧቸው። ከዚያም ከመላእክቱ አንዱ ‘ሕይወታችሁን አድኑ! ወደ ኋላ አትመልከቱ። እንዳትሞቱ ወደ ተራሮቹ ሽሹ’ አላቸው።

ሎጥና ሴቶች ልጆቹ የታዘዙትን በማድረግ ከሰዶም ሸሹ። ለጥቂት ጊዜም እንኳ ቆም አላሉም፤ ወደ ኋላም አልተመለከቱም። የሎጥ ሚስት ግን የተሰጠውን ትእዛዝ ጣሰች። ከሰዶም ወጥተው ጥቂት ከተጓዙ በኋላ ቆመችና ወደ ኋላ ተመለከተች። ከዚያም የሎጥ ሚስት የጨው ሐውልት ሆነች። ሥዕሉ ላይ አየሃት?

ከዚህ ጥሩ ትምህርት ማግኘት እንችላለን። አምላክ የሚታዘዙትን እንደሚያድንና እርሱን የማይታዘዙ ግን ሕይወታቸውን እንደሚያጡ ያሳያል።