በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምዕራፍ 30

በእሳት የተያያዘው ቁጥቋጦ

በእሳት የተያያዘው ቁጥቋጦ

ሙሴ ለበጎቹ ሣር ለማግኘት እስከ ኮሬብ ተራራ ድረስ ተጓዘ። እዚያም ሲደርስ በእሳት የተያያዘ ቁጥቋጦ ተመለከተ፤ ቁጥቋጦው ግን አልተቃጠለም ነበር!

‘ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?’ ሲል አሰበና ‘ልሂድና ቀረብ ብዬ ልመልከት’ አለ። ወደ ቁጥቋጦው ሲቀርብ ከቁጥቋጦው ውስጥ አንድ ድምፅ ‘ወደዚህ አትቅረብ። የቆምህባት ስፍራ የተቀደሰች መሬት ስለሆነች ጫማህን አውልቅ’ አለው። አምላክ በአንድ መልአክ አማካኝነት እያነጋገረው ነበር፤ ስለዚህ ሙሴ ፊቱን ሸፈነ።

ከዚያም አምላክ እንዲህ አለው:- ‘በግብፅ ያለውን የሕዝቤን መከራ አይቻለሁ። ነፃ አወጣቸዋለሁ፤ ሕዝቤን ከግብፅ ምድር እንድታወጣ አንተን እልክሃለሁ።’ ይሖዋ ሕዝቡን በጣም ውብ ወደሆነው የከነዓን ምድር ሊወስዳቸው ነው።

ሆኖም ሙሴ እንዲህ አለ:- ‘እኔ ተራ ሰው ነኝ። እንዴት ይህን ማድረግ እችላለሁ? ወደ ግብፅ ብሄድም እንኳ እስራኤላውያን “የላከህ ማን ነው?” ይሉኛል። በዚህ ጊዜ ምን እላቸዋለሁ?’

አምላክም ‘“ወደ እናንተ የላከኝ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅም አምላክ፣ የያዕቆብም አምላክ የሆነው ይሖዋ ነው” ትላቸዋለህ’ ብሎ መለሰለት። በመቀጠልም ይሖዋ ‘ይህ ለዘላለም ስሜ ነው’ አለው።

‘ይሖዋ ላከኝ ስላቸው ባያምኑኝስ’ በማለት ሙሴ ጠየቀ።

‘በእጅህ የያዝከው ምንድን ነው?’ ሲል አምላክ ጠየቀው።

‘በትር ነው’ በማለት ሙሴ መለሰ።

‘ወደ መሬት ጣለው’ አለው። ሙሴ በትሩን ሲጥለው እባብ ሆነ። ከዚያም ይሖዋ ሌላ ተአምር አሳየው። ‘እጅህን ብብትህ ውስጥ አስገባ’ አለው። ሙሴ እንደተባለው አደረገና እጁን ከብብቱ ውስጥ ሲያወጣው ልክ እንደ በረዶ ነጭ ሆነ! እጁ የሥጋ ደዌ የተባለው መጥፎ በሽታ የያዘው ይመስል ነበር። በመቀጠልም ይሖዋ ሙሴ ሦስተኛ ተአምር እንዲሠራ ኃይል ሰጠው። በመጨረሻም ‘እነዚህን ተአምራት ስትፈጽም እስራኤላውያን እኔ እንደላክሁህ ያምናሉ’ አለው።

ከዚያ በኋላ ሙሴ ወደ ቤት ተመለሰና ዮቶርን ‘ወደ ግብፅ ሄጄ ዘመዶቼን እንድጠይቅ ፍቀድልኝ’ አለው። ዮቶርም ሙሴን አሰናበተውና ሙሴ ወደ ግብፅ ተጓዘ