በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምዕራፍ 81

በአምላክ እርዳታ መተማመን

በአምላክ እርዳታ መተማመን

በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ከባቢሎን ተነስተው ረጅም ጉዞ ከተጓዙ በኋላ ኢየሩሳሌም ደረሱ። ይሁን እንጂ ኢየሩሳሌም ሲደርሱ ከተማይቱ ትልቅ የፍርስራሽ ክምር ሆና ነበር። በዚያ የሚኖር አንድም ሰው አልነበረም። እስራኤላውያን ሁሉንም ነገር እንደገና እንደ አዲስ መገንባት ነበረባቸው።

መጀመሪያ ከሠሯቸው ነገሮች መካከል አንዱ መሠዊያ ነበር። ይህ ለይሖዋ የእንስሳት መሥዋዕቶች ወይም ስጦታዎች የሚያቀርቡበት ቦታ ነበር። ከጥቂት ወራት በኋላ እስራኤላውያን ቤተ መቅደሱን መገንባት ጀመሩ። ይሁን እንጂ በአቅራቢያቸው በነበሩት አገሮች ውስጥ የሚኖሩት ጠላቶቻቸው እስራኤላውያን ቤተ መቅደሱን እንዲገነቡ አይፈልጉም ነበር። ስለዚህ መሥራታቸውን እንዲያቆሙ ሊያስፈራሯቸው ሞከሩ። በመጨረሻም እነዚህ ጠላቶቻቸው አዲሱ የፋርስ ንጉሥ የግንባታውን ሥራ እንዲያቆሙ የሚያደርግ ሕግ እንዲያወጣ አደረጉ።

ብዙ ዓመታት አለፉ። እስራኤላውያን ከባቢሎን ከተመለሱ 17 ዓመት ሆኗቸው ነበር። ይሖዋ ሕዝቡ ግንባታውን እንደገና እንዲጀምሩ እንዲነግሯቸው ሐጌና ዘካርያስ የተባሉትን ነቢያት ላከ። ሕዝቡ በአምላክ እርዳታ በመተማመን ነቢያቱ ያሏቸውን አደረጉ። ሕጉ እንዳይሠሩ የሚከለክል የነበረ ቢሆንም እንደገና መገንባት ጀመሩ።

ስለዚህ ተንትናይ የተባለ አንድ የፋርስ ባለሥልጣን መጣና እስራኤላውያንን ቤተ መቅደሱን ለመገንባት ማን እንደፈቀደላቸው ጠየቃቸው። እስራኤላውያንም በባቢሎን ሳሉ ንጉሥ ቂሮስ ‘ወደ ኢየሩሳሌም ሂዱና የአምላካችሁን የይሖዋን ቤተ መቅደስ ሥሩ’ ብሏቸው እንደነበረ ነገሩት።

ቂሮስ ከመሞቱ በፊት በእርግጥ ይህን ትእዛዝ መስጠት አለመስጠቱን ለማረጋገጥ ተንትናይ ወደ ባቢሎን ደብዳቤ ላከ። ብዙም ሳይቆይ አዲሱ የፋርስ ንጉሥ መልሱን በደብዳቤ ላከ። ደብዳቤው ቂሮስ ይህን ትእዛዝ እንዳወጣ የሚገልጽ ነበር። በተጨማሪም ንጉሡ ‘እስራኤላውያን የአምላካቸውን ቤተ መቅደስ ይሥሩ። አንተም እንድትረዳቸው አዝዤሃለሁ’ ብሎ ጽፎ ነበር። ቤተ መቅደሱ በአራት ዓመት ገደማ ተሠርቶ አለቀ፤ እስራኤላውያንም በጣም ተደሰቱ።

ይህ ከሆነ በኋላ ብዙ ዓመታት አለፉ። ቤተ መቅደሱ ተሠርቶ ካለቀ 48 ዓመታት ያህል ሆኖት ነበር። በኢየሩሳሌም የነበሩት ሰዎች ድሆች ነበሩ፤ ከተማይቱና የአምላክ ቤተ መቅደስም እምብዛም የሚማርኩ አልነበሩም። በዚያ ወቅት በባቢሎን የነበረው እስራኤላዊው ዕዝራ የአምላክን ቤተ መቅደስ ማስዋብ እንደሚያስፈልግ ተገነዘበ። ምን እንዳደረገ ታውቃለህ?

ዕዝራ የፋርስን ንጉሥ አርጤክስስን ለማነጋገር ሄደ። ይህ ጥሩ ንጉሥ ዕዝራ ወደ ኢየሩሳሌም ይዞት የሚሄደው ብዙ ስጦታ ሰጠው። ዕዝራ እነዚህን ስጦታዎች ወደ ኢየሩሳሌም ለመውሰድ እንዲረዱት በባቢሎን ይኖሩ የነበሩትን እስራኤላውያን ጠየቃቸው። ወደ 6, 000 የሚጠጉ ሰዎች አብረው ለመሄድ ፈቃደኞች ሆኑ። ወደ ኢየሩሳሌም ይዘውት የሚሄዱት ብዙ ብርና ወርቅ እንዲሁም ሌሎች ውድ ነገሮች ነበሩ።

በመንገዱ ላይ ክፉ ሰዎች ስለሚያጋጥሙ ዕዝራ በጣም ተጨነቀ። እነዚህ ሰዎች ብራቸውንና ወርቃቸውን ወስደው ሊገድሏቸው ይችላሉ። ስለዚህ ሥዕሉ ላይ እንደምታየው ዕዝራ ሕዝቡን ጠርቶ አንድ ላይ ሰበሰበ። ከዚያም ረጅሙን ጉዞ ተጉዘው ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄዱ ከአደጋ እንዲጠብቃቸው ወደ ይሖዋ ጸለዩ።

ይሖዋ ከማንኛውም አደጋ ጠብቋቸዋል። ለአራት ወራት ከተጓዙ በኋላ በሰላም ኢየሩሳሌም ደረሱ። ይህ ሁኔታ ይሖዋ በእሱ እርዳታ የሚተማመኑትን ሰዎች ሊጠብቃቸው እንደሚችል አያሳይም?