በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክፍል 6

ኢየሱስ ከተወለደበት እስከሞተበት

ኢየሱስ ከተወለደበት እስከሞተበት

መልአኩ ገብርኤል ጥሩ ሥነ ምግባር ወደነበራት ማርያም ተብላ ወደምትጠራ አንዲት ወጣት ሴት ተላከ። ገብርኤል ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ የሚገዛ ልጅ እንደምትወልድ ነገራት። ሕፃኑ ኢየሱስ በጋጣ ውስጥ ተወለደ፤ በዚያም ሳለ እረኞች ሊያዩት መጡ። በኋላም አንድ ኮከብ ሰዎችን ከምሥራቅ እየመራ ልጁ ወዳለበት ቦታ አመጣቸው። ኮከቡን እንዲያዩ ያደረጋቸው ማን እንደሆነና ኢየሱስ እሱን ለመግደል ከተደረገው ሙከራ እንዴት ሊተርፍ እንደቻለ እንማራለን።

ከዚያም ኢየሱስ በ12 ዓመቱ በቤተ መቅደስ ውስጥ ከአስተማሪዎች ጋር ሲነጋገር እንመለከታለን። ይህ ከሆነ ከአሥራ ስምንት ዓመታት በኋላ ኢየሱስ ተጠመቀና አምላክ ወደ ምድር ሲልከው እንዲያከናውነው የሰጠውን ስለ መንግሥቱ የመስበክና የማስተማር ሥራ ማከናወን ጀመረ። ኢየሱስ በዚህ ሥራ እንዲረዱት 12 ሰዎች መረጠና ሐዋርያቱ አደረጋቸው።

በተጨማሪም ኢየሱስ ብዙ ተአምራትን ፈጽሟል። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በጥቂት ትናንሽ ዓሦችና በጥቂት ዳቦዎች ብቻ መግቧል። የታመሙትን ፈውሷል፤ አልፎ ተርፎም የሞቱትን አስነስቷል። በመጨረሻም ኢየሱስ ሊገደል አቅራቢያ የደረሱበትን ብዙ ነገሮችና እንዴት እንደተገደለ እንማራለን። ኢየሱስ ሦስት ዓመት ተኩል ገደማ ሰብኳል፤ ስለዚህ ክፍል ስድስት የሚሸፍነው ጊዜ ከ34 ዓመታት ብዙም አይበልጥም።