በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክፍል 7

ኢየሱስ ከሞት ከተነሳበት ጳውሎስ እስከታሰረበት

ኢየሱስ ከሞት ከተነሳበት ጳውሎስ እስከታሰረበት

ኢየሱስ ከሞተ ከሦስት ቀናት በኋላ ተነሣ። በዚያው ቀን ለከታዮቹ አምስት ጊዜ ታያቸው። ኢየሱስ ከዚያ ቀጥሎ ለ40 ቀናት ታይቷቸዋል። ከዚያም ከደቀ መዛሙርቱ መካከል አንዳንዶቹ እያዩት ወደ ሰማይ አረገ። ከአሥር ቀናት በኋላ አምላክ በኢየሩሳሌም ሆነው ሲጠባበቁ በነበሩት የኢየሱስ ተከታዮች ላይ መንፈስ ቅዱስ እንዲወርድ አደረገ።

ከጊዜ በኋላ የአምላክ ጠላቶች ሐዋርያትን እስር ቤት ከተቷቸው፤ ሆኖም አንድ መልአክ አስፈታቸው። ደቀ መዝሙሩ እስጢፋኖስ እስኪሞት ድረስ በተቃዋሚዎች በድንጋይ ተወገረ። ይሁን እንጂ ኢየሱስ ከእነዚህ ተቃዋሚዎች መካከል አንዱን መርጦ እንዴት ልዩ አገልጋዩ እንዳደረገው እንማራለን፤ በኋላም ይህ ሰው ሐዋርያው ጳውሎስ ሆነ። ከዚያም ኢየሱስ ከሞተ ከሦስት ዓመት ተኩል በኋላ አምላክ ሐዋርያው ጴጥሮስን አይሁዳዊ ላልሆነው ለቆርኔሌዎስና ለቤተሰቡ እንዲሰብክ ላከው።

ከ13 ዓመት ገደማ በኋላ ጳውሎስ የመጀመሪያ የስብከት ጉዞውን ጀመረ። በሁለተኛው ጉዞው ጢሞቴዎስ አብሮት ነበር። ጳውሎስና የጉዞ ጓደኞቹ አምላክን በማገልገል እንዴት ብዙ አስደሳች ጊዜያት ማሳለፍ እንደቻሉ እንመለከታለን። በመጨረሻም ጳውሎስ ሮም ውስጥ ታሰረ። ከሁለት ዓመታት በኋላ ተፈታ፤ ሆኖም እንደገና ታሰረና ተገደለ። በክፍል ሰባት ውስጥ ያሉት ታሪኮች ወደ 32 ዓመታት በሚጠጋ ጊዜ ውስጥ የተከናወኑ ናቸው።