በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምዕራፍ 102

ኢየሱስ ተነሳ

ኢየሱስ ተነሳ

ሴትዮዋና ሁለቱ ሰዎች እነማን እንደሆኑ ታውቃለህ? ሴትዮዋ የኢየሱስ ወዳጅ የነበረችው መግደላዊት ማርያም ነች። ነጭ ልብስ የለበሱት ደግሞ መላእክት ናቸው። ማርያም እየተመለከተችው ያለችው ይህ አነስተኛ ክፍል ኢየሱስ ከሞተ በኋላ አስከሬኑ የተቀመጠበት ቦታ ነው። ይህ ቦታ መቃብር ተብሎ ይጠራል። አሁን ግን አስከሬኑ የለም! ማን ወሰደው? እስቲ እንመልከት።

ኢየሱስ ከሞተ በኋላ ካህናቱ ጲላጦስን ‘ኢየሱስ በሕይወት በነበረበት ጊዜ ከሦስት ቀናት በኋላ እንደሚነሳ ተናግሮ ነበር። ደቀ መዛሙርቱ አስከሬኑን ሰርቀው ከሞት ተነስቷል ብለው እንዳያወሩ መቃብሩ እንዲጠበቅ አድርግ!’ አሉት። ጲላጦስ ካህናቱን መቃብሩን የሚጠብቁ ወታደሮች እንዲልኩ ነገራቸው።

ይሁን እንጂ ኢየሱስ በሞተ በሦስተኛው ቀን ገና ሲነጋጋ በድንገት አንድ የይሖዋ መልአክ መጣ። ድንጋዩን አንከባሎ መቃብሩን ከፈተው። ወታደሮቹ በጣም ከመፍራታቸው የተነሳ ባሉበት ደርቀው ቀሩ። በመጨረሻ ወደ መቃብሩ ውስጥ ሲመለከቱ አስከሬኑ የለም! ከወታደሮቹ መካከል ጥቂቶቹ ወደ ከተማይቱ ሄዱና ለካህናቱ ነገሯቸው። እነዚያ መጥፎ ካህናት ምን እንዳደረጉ ታውቃለህ? ወታደሮቹ እንዲዋሹ ገንዘብ ሰጧቸው። ካህናቱ ወታደሮቹን ‘ደቀ መዛሙርቱ በሌሊት መጥተው እኛ ተኝተን ሳለ አስከሬኑን ሰረቁት በሉ’ አሉአቸው።

በዚህ ወቅት የኢየሱስ ጓደኞች የሆኑ ጥቂት ሴቶች መቃብሩን ሊያዩ መጡ። መቃብሩን ባዶ ሆኖ ሲያገኙት ምንኛ ተገርመው ይሆን! ነጭ ልብስ የለበሱ ሁለት መላእክት ድንገት ብቅ አሉ። ‘ኢየሱስን እዚህ የምትፈልጉት ለምንድን ነው? እርሱ ተነስቷል። በፍጥነት ሂዱና ለደቀ መዛሙርቱ ንገሯቸው’ አሉአቸው። ሴቶቹ በፍጥነት እየሮጡ ሄዱ! ሆኖም መንገድ ላይ አንድ ሰው አስቆማቸው። ይህ ሰው ማን እንደሆነ ታውቃለህ? ኢየሱስ ነው! ‘ሂዱና ለደቀ መዛሙርቴ ንገሯቸው’ አላቸው።

ሴቶቹ ለደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ እንደተነሳና እነርሱም እንዳዩት ሲነግሯቸው ደቀ መዛሙርቱ ሊያምኑ አልቻሉም። ጴጥሮስና ዮሐንስ ራሳቸው ለማየት ወደ መቃብሩ ሮጡ፤ ሆኖም መቃብሩ ባዶ ነበር! ጴጥሮስና ዮሐንስ ሲሄዱ መግደላዊት ማርያም እዚያው ቆየች። ወደ መቃብሩ ውስጥ ያየችውና ሁለቱን መላእክት የተመለከተችው በዚህ ጊዜ ነበር።

የኢየሱስ አካል ምን እንደሆነ ታውቃለህ? አምላክ እንዲሰወር አደረገው። አምላክ ኢየሱስን ሲሞት የነበረውን ሥጋዊ አካል ይዞ እንዲነሳ አላደረገውም። በሰማይ ያሉት መላእክት ያላቸውን ዓይነት አንድ አዲስ መንፈሳዊ አካል ሰጠው። ሆኖም ቀጥሎ እንደምንማረው ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ከሞት መነሳቱን እንዲያውቁ ለማድረግ ሰዎች ሊያዩት የሚችሉት አካል መልበስ ይችላል