በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክፍል 8

መጽሐፍ ቅዱስ አስቀድሞ የተናገረው ነገር ይፈጸማል

መጽሐፍ ቅዱስ አስቀድሞ የተናገረው ነገር ይፈጸማል

መጽሐፍ ቅዱስ ባለፉት ዘመናት የተከናወነውን እውነተኛ ታሪክ ብቻ ሳይሆን ወደፊት የሚሆነውንም ነገር ይገልጻል። ሰዎች ስለ ወደፊቱ ጊዜ መናገር አይችሉም። መጽሐፍ ቅዱስ ከአምላክ የመጣ ነው የምንለው ለዚህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ወደፊቱ ጊዜ ምን ይላል?

አንድ ታላቅ የአምላክ ጦርነት እንደሚመጣ ይናገራል። በዚህ ጦርነት አምላክ ክፋትን ሁሉና ክፉ ሰዎችን ከምድር ላይ ጠራርጎ ያጠፋል፤ እሱን የሚያገለግሉትን ሰዎች ግን ይጠብቃቸዋል። የአምላክ ንጉሥ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ የአምላክ አገልጋዮች ሰላምና ደስታ እንዲያገኙና ዳግመኛ እንዳይታመሙ ወይም እንዳይሞቱ ያደርጋል።

አምላክ በምድር ላይ አዲስ ገነት የሚያዘጋጅ መሆኑ በጣም ያስደስተናል፤ አያስደስተንም እንዴ? ሆኖም በዚህች ገነት ውስጥ ለመኖር እንድንችል አንድ ነገር ማድረግ ይኖርብናል። አምላክ ለሚያገለግሉት ሰዎች ወደፊት የሚያመጣላቸውን አስደሳች ነገሮች ማግኘት እንድንችል ምን ማድረግ እንዳለብን በዚህ መጽሐፍ የመጨረሻ ታሪክ ላይ እንማራለን። ስለዚህ ክፍል ስምንትን አንብብና መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ወደፊቱ ጊዜ ምን ብሎ እንደሚናገር ተመልከት