በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ የተሰኘውን መጽሐፍ ለማጥናት የሚረዱ ጥያቄዎች

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ የተሰኘውን መጽሐፍ ለማጥናት የሚረዱ ጥያቄዎች

ታሪክ 1

አምላክ የተለያዩ ነገሮችን መፍጠር ጀመረ

  1. ጥሩ ነገሮች ሁሉ የተገኙት ከየት ነው? ጥሩ ከሆኑ ነገሮች መካከል አንድ ምሳሌ መጥቀስ ትችላለህ?

  2. አምላክ በመጀመሪያ የፈጠረው ማንን ነው?

  3. በመጀመሪያ የተፈጠረው መልአክ ልዩ የነበረው ለምንድን ነው?

  4. ምድር በመጀመሪያ ምን ትመስል እንደነበረ ግለጽ። (ሥዕሉን ተመልከት።)

  5. አምላክ ምድርን ለእንስሳትና ለሰው መኖሪያነት ማዘጋጀት የጀመረው እንዴት ነበር?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ኤርምያስ 10:12ን አንብብ።

    አምላክ በፈጠራቸው ነገሮች አማካኝነት የትኞቹ ባሕርያቱ ተገልጸዋል? (ኢሳ. 40:26፤ ሮሜ 11:33)

  2. ቈላስይስ 1:15-17ን አንብብ።

    ኢየሱስ በፍጥረት ሥራ ላይ ምን ድርሻ ነበረው? ይህስ ለእሱ ያለንን አመለካከት እንዴት ሊነካው ይገባል? (ቈላ. 1:15-17)

  3. ዘፍጥረት 1:1-10ን አንብብ።

    1. (ሀ) ምድር ከየት ተገኘች? (ዘፍ. 1:1)

    2. (ለ) በመጀመሪያው የፍጥረት ቀን ምን ሆነ? (ዘፍ. 1:3-5)

    3. (ሐ) በሁለተኛው የፍጥረት ቀን የሆነውን ግለጽ። (ዘፍ. 1:7, 8)

ታሪክ 2

ውብ የአትክልት ቦታ

  1. 1. ምድር መኖሪያችን እንድትሆን አምላክ ያዘጋጃት እንዴት ነው?

  2. 2. አምላክ የፈጠራቸውን ልዩ ልዩ ዓይነት እንስሳት ግለጽ። (ሥዕሉን ተመልከት።)

  3. 3. የኤደን የአትክልት ቦታ ልዩ የነበረችው ለምንድን ነው?

  4. 4. አምላክ መላዋ ምድር ምን እንድትሆን ይፈልግ ነበር?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፍጥረት 1:11-25ን አንብብ።

    1. (ሀ) አምላክ በሦስተኛው የፍጥረት ቀን ምን ፈጠረ? (ዘፍ. 1:12)

    2. (ለ) በአራተኛው የፍጥረት ቀን ምን ሆነ? (ዘፍ. 1:16)

    3. (ሐ) አምላክ በአምስተኛውና በስድስተኛው ቀን ምን ዓይነት እንስሳትን ፈጠረ? (ዘፍ. 1:20, 21, 25)

  2. ዘፍጥረት 2:8, 9ን አንብብ።

    አምላክ በአትክልት ሥፍራው ውስጥ ምን ሁለት የተለዩ ዛፎች አስቀመጠ? ዛፎቹስ ምን ያመለክቱ ነበር?

ታሪክ 3

የመጀመሪያዎቹ ወንድና ሴት

  1. በታሪክ 3 ላይ የሚታየው ሥዕል በታሪክ 2 ላይ ከሚታየው ሥዕል የሚለየው እንዴት ነው?

  2. የመጀመሪያውን ሰው ማን ፈጠረው? የሰውየውስ ስም ማን ነበር?

  3. አምላክ ለአዳም ምን ሥራ ሰጠው?

  4. አምላክ፣ አዳም ከባድ እንቅልፍ እንዲወስደው ያደረገው ለምን ነበር?

  5. አዳምና ሔዋን ለምን ያህል ጊዜ ሊኖሩ ይችሉ ነበር? ይሖዋ ምን ሥራ እንዲሠሩ ይፈልግባቸው ነበር?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. መዝሙር 83:18ን [NW] አንብብ።

    የአምላክ ስም ማን ነው? በምድር ላይ ያለው ተወዳዳሪ የማይገኝለት ሥልጣኑስ ምንድን ነው? (ኤር. 16:21፤ ዳን. 4:17)

  2. ዘፍጥረት 1:26-31ን አንብብ።

    1. (ሀ) አምላክ በስድስተኛው ቀን ከፈጠራቸው ፍጥረታት ሁሉ ጉልህ ሥፍራ የሚሰጠው ፍጥረት ምንድን ነው? ይህ ፍጥረት ከእንስሳት የሚለየውስ እንዴት ነው? (ዘፍ. 1:26)

    2. (ለ) አምላክ ለሰውም ሆነ ለእንስሳት ምን ዝግጅት አድርጓል? (ዘፍ. 1:30)

  3. ዘፍጥረት 2:7-25ን አንብብ።

    1. (ሀ) አዳም ለእንስሳት ስም እንዲያወጣላቸው የተሰጠው ሥራ ምንን ይጨምር ነበር? (ዘፍ. 2:19)

    2. (ለ) ዘፍጥረት 2:24 ይሖዋ ለጋብቻ፣ ለመለያየትና ለፍቺ ያለውን አመለካከት እንድናስተውል የሚረዳን እንዴት ነው? (ማቴ. 19:4-6, 9)

ታሪክ 4

መኖሪያቸውን ያጡት ለምንድን ነው?

  1. በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው አዳምና ሔዋን ምን ደረሰባቸው?

  2. ይሖዋ የቀጣቸው ለምን ነበር?

  3. አንድ እባብ ለሔዋን ምን ነገራት?

  4. እባቡ ሔዋንን እንዲያነጋግራት ያደረገው ማን ነበር?

  5. አዳምና ሔዋን ገነት የሆነች መኖሪያቸውን ያጡት ለምን ነበር?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፍጥረት 2:16, 17ን እና 3:1-13, 24ን አንብብ።

    1. (ሀ) እባቡ ለሔዋን ያቀረበላት ጥያቄ የይሖዋን ስም የሚያጠፋ የሆነው እንዴት ነበር? (ዘፍ. 3:1-5፤ 1 ዮሐ. 5:3)

    2. (ለ) ሔዋን ለእኛ የማስጠንቀቂያ ምሳሌ ሆና የምታገለግለን እንዴት ነው? (ፊልጵ. 4:8፤ ያዕ. 1:14, 15፤ 1 ዮሐ. 2:16)

    3. (ሐ) አዳምና ሔዋን ጥፋተኝነታቸውን ሳይቀበሉ የቀሩት በምን መንገድ ነው? (ዘፍ. 3:12, 13)

    4. (መ) ከኤደን ገነት በስተ ምሥራቅ እንዲቆሙ የተመደቡት ኪሩቦች የይሖዋን ሉዓላዊነት የደገፉት እንዴት ነው? (ዘፍ. 3:24)

  2. ራእይ 12:9ን አንብብ።

    ሰይጣን የሰውን ዘር ከአምላክ አገዛዝ በማራቅ ረገድ ምን ያህል ተሳክቶለታል? (1 ዮሐ. 5:19)

ታሪክ 5

በችግር የተሞላ ኑሮ ተጀመረ

  1. አዳምና ሔዋን ከገነት ውጪ የገጠማቸው ኑሮ ምን ይመስል ነበር?

  2. አዳምና ሔዋን ምን መሆን ጀመሩ? ለምንስ?

  3. የአዳምና የሔዋን ልጆች የሚያረጁትና የሚሞቱት ለምንድን ነው?

  4. አዳምና ሔዋን ይሖዋን ታዘው ቢሆን ኖሮ እነሱና ልጆቻቸው ምን ዓይነት ሕይወት ይኖራቸው ነበር?

  5. ሔዋን አለመታዘዟ ስቃይ ያስከተለባት እንዴት ነው?

  6. የአዳምና የሔዋን የመጀመሪያዎቹ ሁለት ወንዶች ልጆች ስም ማን ነበር?

  7. በሥዕሉ ላይ የሚታዩት ሌሎች ልጆች እነማን ናቸው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፍጥረት 3:16-23ን እና 4:1, 2ን አንብብ።

    1. (ሀ) ምድሪቱ መረገሟ በአዳም ሕይወት ላይ ተጽዕኖ ያሳደረው እንዴት ነው? (ዘፍ. 3:17-19፤ ሮሜ 8:20, 22)

    2. (ለ) “ሕያው” የሚል ትርጉም ያለው ሔዋን የሚለው ስም ተስማሚ የሆነው ለምንድን ነው? (ዘፍ. 3:20)

    3. (ሐ) አዳምና ሔዋን ኃጢአት ከሠሩ በኋላም እንኳን ቢሆን ይሖዋ አሳቢነት ያሳያቸው እንዴት ነው? (ዘፍ. 3:7, 21)

  2. ራእይ 21:3, 4ን አንብብ።

    ‘በቀድሞው ሥርዓት’ ውስጥ ካሉ ነገሮች መካከል የትኞቹ ነገሮች ጠፍተው ለማየት ትናፍቃለህ?

ታሪክ 6

አንድ ጥሩ ልጅና አንድ መጥፎ ልጅ

  1. ቃየንና አቤል በምን ሥራ ተሰማሩ?

  2. ቃየንና አቤል ለይሖዋ ምን ስጦታ አመጡ?

  3. ይሖዋ በአቤል ስጦታ የተደሰተው ለምን ነበር? በቃየን ስጦታስ ያልተደሰተው ለምን ነበር?

  4. ቃየን ምን ዓይነት ሰው ነበር? ይሖዋ ቃየን እንዲታረም ሊረዳው የሞከረው እንዴት ነው?

  5. ቃየን ከወንድሙ ጋር በሜዳ ሳለ ምን አደረገ?

  6. ቃየን ወንድሙን ከገደለ በኋላ የደረሰበትን ነገር ግለጽ።

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፍጥረት 4:2-26ን አንብብ።

    1. (ሀ) ይሖዋ ቃየን የነበረበትን አደገኛ ሁኔታ የገለጸው እንዴት ነበር? (ዘፍ. 4:7)

    2. (ለ) ቃየን የልቡን ዝንባሌ የገለጸው እንዴት ነው? (ዘፍ. 4:9)

    3. (ሐ) ይሖዋ ንጹሕ ደም ስለማፍሰስ ያለው አመለካከት ምንድን ነው? (ዘፍ. 4:10፤ ኢሳ. 26:21)

  2. አንደኛ ዮሐንስ 3:11, 12ን አንብብ።

    1. (ሀ) ቃየን የተቆጣው ለምን ነበር? ይህስ በዛሬው ጊዜ ለምንኖረው ለእኛ ማስጠንቀቂያ የሚሆነን እንዴት ነው? (ዘፍ. 4:4, 5፤ ምሳሌ 14:30፤ 28:22)

    2. (ለ) የቤተሰባችን አባሎች በሙሉ ይሖዋን የሚቃወሙ በሚሆኑበት ጊዜም እንኳን ጽኑ አቋም መያዝ እንደምንችል መጽሐፍ ቅዱስ የሚያሳየው እንዴት ነው? (መዝ. 27:10፤ ማቴ. 10:21, 22)

  3. ዮሐንስ 11:25ን አንብብ።

    ለጽድቅ ሲሉ የሚሞቱትን ሁሉ በሚመለከት ይሖዋ ምን ዋስትና ይሰጣል? (ዮሐ. 5:24)

ታሪክ 7

ደፋር ሰው

  1. ሄኖክ ከሌሎቹ ሰዎች የተለየ የነበረው እንዴት ነው?

  2. በሄኖክ ዘመን የነበሩ ሰዎች ብዙ መጥፎ ነገር ይሠሩ የነበሩት ለምንድን ነው?

  3. ሰዎች ምን ምን መጥፎ ነገሮችን ይሠሩ ነበር? (ሥዕሉን ተመልከት።)

  4. ሄኖክ ደፋር መሆን ያስፈለገው ለምንድን ነው?

  5. ሰዎች በዚያ ዘመን ምን ያህል ዕድሜ ይኖሩ ነበር? ይሁን እንጂ ሄኖክ የኖረው ስንት ዓመት ነበር?

  6. ሄኖክ ከሞተ በኋላ ምን ተፈጸመ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፍጥረት 5:21-24, 27ን አንብብ።

    1. (ሀ) ሄኖክ ከይሖዋ ጋር ምን ዓይነት ዝምድና ነበረው? (ዘፍ. 5:24)

    2. (ለ) መጽሐፍ ቅዱስ በሚናገረው መሠረት ከሁሉ የበለጠ ረዥም ዕድሜ የኖረው ማን ነበር? ሲሞት ዕድሜው ስንት ነበር? (ዘፍ. 5:27)

  2. ዘፍጥረት 6:5ን አንብብ።

    ሄኖክ ከሞተ በኋላ በምድር ላይ የነበረው ሁኔታ ምን ያህል ከፍቶ ነበር? ይህስ ከዘመናችን ጋር የሚመሳሰለው እንዴት ነው? (2 ጢሞ. 3:13)

  3. ዕብራውያን 11:5ን አንብብ።

    አምላክን ‘ደስ ያሰኘው’ የትኛው የሄኖክ ባሕርይ ነው? ይህስ ምን ውጤት አስገኝቷል? (ዘፍ. 5:22)

  4. ይሁዳ 14, 15ን አንብብ።

    በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያኖች ሰዎችን ስለ መጪው የአርማጌዶን ጦርነት ሲያስጠነቅቁ የሄኖክን ድፍረት ሊኮርጁ የሚችሉት እንዴት ነው? (2 ጢሞ. 4:2፤ ዕብ. 13:6)

ታሪክ 8

በምድር ላይ የነበሩ ግዙፍ ሰዎች

  1. ከአምላክ መላእክት አንዳንዶቹ ሰይጣንን በሰሙ ጊዜ ምን ሁኔታ ተፈጸመ?

  2. አንዳንድ መላእክት በሰማይ የነበራቸውን ሥራ ትተው ወደ ምድር የወረዱት ለምን ነበር?

  3. መላእክት ወደ ምድር ወርደው ሰብአዊ አካል መልበሳቸው ስህተት የነበረው ለምንድን ነው?

  4. የመላእክቱን ልጆች ከሌሎቹ የሰው ልጆች የሚለያቸው ምን ነበር?

  5. በሥዕሉ ላይ እንደምትመለከተው የመላእክቱ ልጆች ግዙፍ በሆኑ ጊዜ ምን ያደርጉ ነበር?

  6. ከሄኖክ በኋላ በምድር ላይ የኖረው ጥሩ ሰው ማን ነበር? አምላክ እሱን የወደደውስ ለምን ነበር?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፍጥረት 6:1-8ን አንብብ።

    ዘፍጥረት 6:6 ጠባያችን የይሖዋን ስሜት እንዴት ሊነካው እንደሚችል የሚገልጸው እንዴት ነው? (መዝ. 78:40, 41፤ ምሳሌ 27:11)

  2. ይሁዳ 6ን አንብብ።

    በኖኅ ዘመን “መኖሪያቸውን የተዉት” መላእክት ለእኛ የማስጠንቀቂያ ምሳሌ የሚሆኑት እንዴት ነው? (1 ቆሮ. 3:5-9፤ 2 ጴጥ. 2:4, 9, 10)

ታሪክ 9

ኖኅ መርከብ ሠራ

  1. በኖኅ ቤተሰብ ውስጥ ስንት ሰዎች ነበሩ? የሦስት ወንዶች ልጆቹ ስም ማን ነበር?

  2. አምላክ ኖኅን ምን ያልተለመደ ሥራ እንዲሠራ ጠየቀው? ለምንስ?

  3. በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ኖኅ ስለ መርከቡ ሲነግራቸው ምን ምላሽ ሰጡ?

  4. አምላክ ኖኅን እንስሳቱን ምን እንዲያደርግ አዘዘው?

  5. አምላክ የመርከቡን በር ከዘጋ በኋላ ኖኅና ቤተሰቡ ምን ማድረግ ነበረባቸው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፍጥረት 6:9-22ን አንብብ።

    1. (ሀ) ኖኅ የታወቀ የእውነተኛው አምላክ አምላኪ እንዲሆን ያደረገው ምንድን ነው? (ዘፍ. 6:9, 22)

    2. (ለ) ይሖዋ ስለ ዓመጽ ምን ይሰማዋል? ይህስ የመዝናኛ ምርጫችንን እንዴት ሊነካው ይገባል? (ዘፍ. 6:11, 12፤ መዝ. 11:5)

    3. (ሐ) በይሖዋ ድርጅት በኩል መመሪያ በምንቀበልበት ጊዜ ኖኅን ልንመስለው የምንችለው እንዴት ነው? (ዘፍ. 6:22፤ 1 ዮሐ. 5:3)

  2. ዘፍጥረት 7:1-9ን አንብብ።

    ይሖዋ ፍጹም ያልነበረውን ኖኅን እንደ ጻድቅ የተመለከተው መሆኑ በዛሬው ጊዜ እኛን የሚያበረታታን እንዴት ነው? (ዘፍ. 7:1፤ ምሳሌ 10:16፤ ኢሳ. 26:7)

ታሪክ 10

ታላቁ የጥፋት ውኃ

  1. ዝናቡ መዝነብ ከጀመረ በኋላ ማንም ሰው ወደ መርከቧ መግባት የማይችለው ለምን ነበር?

  2. ይሖዋ ዝናቡ እንዲዘንብ ያደረገው ለስንት ቀንና ሌሊት ነበር? የውኃውስ ከፍታ ምን ያህል ደርሶ ነበር?

  3. ውኃው ምድርን መሸፈን ሲጀምር መርከቧ ምን ሆነች?

  4. ግዙፎቹ የመላእክት ልጆች ከጥፋት ውኃው ተርፈዋል? አባቶቻቸውስ ምን ሆኑ?

  5. ከአምስት ወራት በኋላ መርከቧ ምን ሆነች?

  6. ኖኅ ቁራውን ከመርከብ አውጥቶ የለቀቀው ለምን ነበር?

  7. ኖኅ ውኃው ከምድር ላይ መድረቁን እንዴት ሊያውቅ ቻለ?

  8. ኖኅና ቤተሰቡ ከዓመት ለሚበልጥ ጊዜ በመርከቧ ውስጥ ከቆዩ በኋላ አምላክ ለኖኅ ምን ብሎ ነገረው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፍጥረት 7:10-24ን አንብብ።

    1. (ሀ) በምድር ላይ ምን ያህል የሕይወት ጥፋት ደርሷል? (ዘፍ. 7:23)

    2. (ለ) ውኃው ከምድር ላይ እስኪደርቅ ምን ያህል ጊዜ ፈጀ? (ዘፍ. 7:24)

  2. ዘፍጥረት 8:1-17ን አንብብ።

    ይሖዋ በመጀመሪያ ለምድር የነበረው ዓላማ እንዳልተለወጠ ዘፍጥረት 8:17 የሚያሳየው እንዴት ነው? (ዘፍ. 1:22)

  3. አንደኛ ጴጥሮስ 3:19, 20ን አንብብ።

    1. (ሀ) ዓመጸኞቹ መላእክት ወደ ሰማይ ሲመለሱ ምን ተፈረደባቸው? (ይሁዳ 6)

    2. (ለ) የኖኅና የቤተሰቡ ታሪክ ይሖዋ ሕዝቡን ለማዳን ባለው ችሎታ ላይ ያለንን እምነት የሚያጠናክርልን እንዴት ነው? (2 ጴጥ. 2:9)

ታሪክ 11

የመጀመሪያው ቀስተ ደመና

  1. በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው ኖኅ ከመርከቡ እንደወጣ ምን አደረገ?

  2. ከጥፋት ውኃው በኋላ አምላክ ለኖኅና ለቤተሰቡ ምን ትእዛዝ ሰጣቸው?

  3. አምላክ ምን ቃል ገባ?

  4. ቀስተ ደመና ስናይ ምን ማስታወስ ይኖርብናል?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፍጥረት 8:18-22ን አንብብ።

    1. (ሀ) በዛሬው ጊዜ እኛ ለይሖዋ ‘መልካም መዓዛ’ ማቅረብ የምንችለው እንዴት ነው? (ዘፍ. 8:21፤ ዕብ. 13:15, 16)

    2. (ለ) ይሖዋ ስለ ሰው ልጅ የልብ ሁኔታ ምን አስተያየት ሰጠ? በመሆኑም እኛ ምን ዓይነት ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል? (ዘፍ. 8:21፤ ማቴ. 15:18, 19)

  2. ዘፍጥረት 9:9-17ን አንብብ።

    1. (ሀ) ይሖዋ ከምድር ፍጥረታት ሁሉ ጋር ምን ቃል ኪዳን አደረገ? (ዘፍ. 9:10, 11)

    2. (ለ) የቀስተ ደመናው ቃል ኪዳን በሥራ ላይ የሚውለው ለምን ያህል ጊዜ ነው? (ዘፍ. 9:16)

ታሪክ 12

ሰዎች አንድ ትልቅ ግንብ ሠሩ

  1. ናምሩድ ማን ነበር? አምላክ ስለ እሱ የነበረው ስሜት ምን ነበር?

  2. በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው ሰዎች ጡብ የሚሠሩት ለምን ነበር?

  3. ይሖዋ በግንባታ ሥራቸው ያልተደሰተው ለምን ነበር?

  4. አምላክ ግንቡን እንዳይሠሩ ያስቆማቸው እንዴት ነው?

  5. ከተማዋ ምን ተብላ ተጠራች? የዚህ ስም ትርጉምስ ምንድን ነው?

  6. አምላክ ቋንቋቸውን ካደባለቀባቸው በኋላ ሰዎቹ ምን ሆኑ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፍጥረት 10:1, 8-10ን አንብብ።

    ናምሩድ ምን የተለዩ ባሕርያት ነበሩት? ይህስ ለእኛ ምን ማስጠንቀቂያ ይሰጠናል? (ምሳሌ 3:31)

  2. ዘፍጥረት 11:1-9ን አንብብ።

    ግንቡን ለመሥራት ያነሳሳቸው ምን ነበር? የግንባታ ዕቅዱ ሳይሳካ የቀረውስ ለምን ነበር? (ዘፍ. 11:4፤ ምሳሌ 16:18፤ ዮሐ. 5:44)

ታሪክ 13

የአምላክ ወዳጅ የሆነው አብርሃም

  1. በዑር ከተማ ምን ዓይነት ሰዎች ይኖሩ ነበር?

  2. በሥዕሉ ላይ የሚታየው ሰው ማን ነው? የተወለደው መቼ ነበር? የሚኖረውስ የት ነበር?

  3. አምላክ አብርሃምን ምን እንዲያደርግ ነገረው?

  4. አብርሃም የአምላክ ወዳጅ ተብሎ የተጠራው ለምንድን ነው?

  5. አብርሃም ዑርን ለቆ ሲወጣ አብረውት የሄዱት እነማን ነበሩ?

  6. አብርሃም ወደ ከነዓን ምድር ሲደርስ አምላክ ምን ብሎ ነገረው?

  7. አብርሃም 99 ዓመት ሲሆነው አምላክ ምን ቃል ገባለት?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፍጥረት 11:27-32ን አንብብ።

    1. (ሀ) አብርሃምና ሎጥ የሚዛመዱት እንዴት ነበር? (ዘፍ. 11:27)

    2. (ለ) ታራ ቤተሰቡን ይዞ ወደ ከነዓን ለመሄድ እንደተነሳ ቢነገርለትም ይህን ጉዞ ለማድረግ ሐሳቡን ያመጣው አብርሃም መሆኑን እንዴት እናውቃለን? አብርሃም ይህን ያደረገውስ ለምን ነበር? (ዘፍ. 11:31፤ ሥራ 7:2-4)

  2. ዘፍጥረት 12:1-7ን አንብብ።

    አብርሃም ወደ ከነዓን ምድር ከደረሰ በኋላ ይሖዋ ምን ተጨማሪ ቃል ገባለት? (ዘፍ. 12:7)

  3. ዘፍጥረት 17:1-8, 15-17ን አንብብ።

    1. (ሀ) አብራም በ99 ዓመቱ ምን የስም ለውጥ ተደረገለት? ለምንስ? (ዘፍ. 17:5)

    2. (ለ) ይሖዋ ለሣራ ምን በረከት እንደሚሰጣት ቃል ገባላት? (ዘፍ. 17:15, 16)

  4. ዘፍጥረት 18:9-19ን አንብብ።

    1. (ሀ) በ⁠ዘፍጥረት 18:19 ላይ እንደተገለጸው በአባቶች ላይ የተጣለው ኃላፊነት ምንድን ነው? (ዘዳ. 6:6, 7፤ ኤፌ. 6:4)

    2. (ለ) ከይሖዋ ምንም ነገር መደበቅ እንደማንችል የሚያሳየው የትኛው የሣራ ተሞክሮ ነው? (ዘፍ. 18:12, 15፤ መዝ. 44:21)

ታሪክ 14

አምላክ የአብርሃምን እምነት ፈተነው

  1. አምላክ ለአብርሃም ምን ቃል ገባለት? ቃሉን የጠበቀውስ እንዴት ነው?

  2. በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው አምላክ የአብርሃምን እምነት የፈተነው እንዴት ነው?

  3. አብርሃም፣ አምላክ ይህን ትእዛዝ የሰጠበት ምክንያት ባይገባውም እንኳን ምን አደረገ?

  4. አብርሃም ልጁን ለመሠዋት ቢላዋ ባነሳ ጊዜ ምን ሆነ?

  5. አብርሃም በአምላክ ላይ ያለው እምነት ምን ያህል ጠንካራ ነው?

  6. አምላክ አብርሃም መሥዋዕት አድርጎ እንዲያቀርበው ምን ሰጠው? እንዴትስ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፍጥረት 21:1-7ን አንብብ።

    አብርሃም ልጁን በስምንተኛው ቀን የገረዘው ለምን ነበር? (ዘፍ. 17:10-12፤ 21:4)

  2. ዘፍጥረት 22:1-18ን አንብብ።

    ይስሐቅ ለአባቱ ለአብርሃም ታዛዥነት ያሳየው እንዴት ነበር? ይህስ ወደፊት ለሚፈጸም አንድ ከፍተኛ ትርጉም ያለው ነገር ምሳሌ የሆነው እንዴት ነው? (ዘፍ. 22:7-9፤ 1 ቆሮ. 5:7፤ ፊልጵ. 2:8, 9)

ታሪክ 15

የሎጥ ሚስት ወደ ኋላ ተመለከተች

  1. አብርሃምና ሎጥ የተለያዩት ለምንድን ነው?

  2. ሎጥ በሰዶም ለመኖር የመረጠው ለምን ነበር?

  3. የሰዶም ሰዎች እንዴት ያሉ ነበሩ?

  4. ሁለት መላእክት ለሎጥ ምን ማስጠንቀቂያ ሰጡት?

  5. የሎጥ ሚስት የጨው ዐምድ ሆና የቀረችው ለምን ነበር?

  6. በሎጥ ሚስት ላይ ከደረሰው ነገር ምን ትምህርት እናገኛለን?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፍጥረት 13:5-13ን አንብብ።

    በግለሰቦች መካከል የሚነሱ አለመግባባቶችን በመፍታት ረገድ ከአብርሃም ምን እንማራለን? (ዘፍ. 13:8, 9፤ ሮሜ 12:10፤ ፊልጵ. 2:3, 4)

  2. ዘፍጥረት 18:20-33ን አንብብ።

    ይሖዋ ከአብርሃም ጋር ያደረገው ውይይት ይሖዋና ኢየሱስ በጽድቅ እንደሚፈርዱ እንድንተማመን የሚያደርገን እንዴት ነው? (ዘፍ. 18:25, 26፤ ማቴ. 25:31-33)

  3. ዘፍጥረት 19:1-29ን አንብብ።

    1. (ሀ) ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ አምላክ ለግብረ ሰዶም ስላለው አመለካከት ምን ያሳያል? (ዘፍ. 19:5, 13፤ ዘሌ. 20:13)

    2. (ለ) ሎጥና አብርሃም ለአምላክ አመራር ምላሽ የሰጡበት መንገድ ምን ልዩነት አለው? እኛስ ከዚህ ምን እንማራለን? (ዘፍ. 19:15, 16, 19, 20፤ 22:3)

  4. ሉቃስ 17:28-32ን አንብብ።

    የሎጥ ሚስት ለቁሳዊ ነገሮች ምን ዓይነት ዝንባሌ ነበራት? ይህስ ለእኛ ማስጠንቀቂያ ሆኖ የሚያገለግለን እንዴት ነው? (ሉቃስ 12:15፤ 17:31, 32፤ ማቴ. 6:19-21, 25)

  5. ሁለተኛ ጴጥሮስ 2:6-8ን አንብብ።

    እንደ ሎጥ ሁሉ እኛም በዙሪያችን ላለው ፈሪሃ አምላክ የሌለው ዓለም ያለን አመለካከት ምን ሊሆን ይገባዋል? (ሕዝ. 9:4፤ 1 ዮሐ. 2:15-17)

ታሪክ 16

ይስሐቅ ጥሩ ሚስት አገኘ

  1. በሥዕሉ ላይ ያሉት ወንድና ሴት እነማን ናቸው?

  2. አብርሃም ለልጁ ሚስት ለማግኘት ምን አደረገ? ለምንስ?

  3. የአብርሃም አገልጋይ ያቀረበው ጸሎት መልስ ያገኘው እንዴት ነበር?

  4. ርብቃ ይስሐቅን ማግባት ትፈልግ እንደሆነ ስትጠየቅ ምን መልስ ሰጠች?

  5. ይስሐቅ እንደገና ደስተኛ እንዲሆን ያደረገው ነገር ምንድን ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፍጥረት 24:1-67ን አንብብ።

    1. (ሀ) ርብቃ የአብርሃምን አገልጋይ በውኃ ጉድጓዱ አጠገብ ባገኘችው ጊዜ ምን ጥሩ ባሕርያት አሳየች? (ዘፍ. 24:17-20፤ ምሳሌ 31:17, 31)

    2. (ለ) አብርሃም ለይስሐቅ ያደረገው የጋብቻ ዝግጅት በዛሬው ጊዜ ላሉ ክርስቲያኖች ምን ጥሩ ምሳሌ ይሆናቸዋል? (ዘፍ. 24:37, 38፤ 1 ቆሮ. 7:39፤ 2 ቆሮ. 6:14)

    3. (ሐ) እንደ ይስሐቅ ሁሉ እኛም ለማሰላሰል ጊዜ መመደብ ያለብን ለምንድን ነው? (ዘፍ. 24:63፤ መዝ. 77:12፤ ፊልጵ. 4:8)

ታሪክ 17

የማይመሳሰሉ መንትዮች

  1. ኤሳውና ያዕቆብ እነማን ናቸው? የማይመሳሰሉ የሆኑትስ እንዴት ነው?

  2. ኤሳውና ያዕቆብ አያታቸው አብርሃም ሲሞት ስንት ዓመታቸው ነበር?

  3. ኤሳው እናትና አባቱን ያሳዘነ ምን ነገር አደረገ?

  4. ኤሳው በወንድሙ በያዕቆብ በጣም የተናደደው ለምንድን ነው?

  5. ይስሐቅ ለልጁ ለያዕቆብ ምን መመሪያ ሰጠው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፍጥረት 25:5-11, 20-34ን አንብብ።

    1. (ሀ) የርብቃን ሁለት ልጆች በሚመለከት ይሖዋ ምን ትንቢት ተናገረ? (ዘፍ. 25:23)

    2. (ለ) ያዕቆብና ኤሳው ስለ ብኩርና መብት የነበራቸው አመለካከት ምን ልዩነት ነበረው? (ዘፍ. 25:31-34)

  2. ዘፍጥረት 26:34, 35፤ 27:1-46 እና 28:1-5ን አንብብ።

    1. (ሀ) ኤሳው ለመንፈሳዊ ነገሮች አድናቆት የሌለው መሆኑ የታየው እንዴት ነበር? (ዘፍ. 26:34, 35፤ 27:46)

    2. (ለ) ይስሐቅ፣ ያዕቆብ የአምላክን በረከት ማግኘት እንዲችል ምን ማድረግ እንዳለበት ነገረው? (ዘፍ. 28:1-4)

  3. ዕብራውያን 12:16, 17ን አንብብ።

    ቅዱስ ነገሮችን የሚንቁ ሰዎች የሚደርስባቸውን ሁኔታ በተመለከተ የኤሳው ምሳሌ ምን ያሳያል?

ታሪክ 18

ያዕቆብ ወደ ካራን ሄደ

  1. በሥዕሉ ላይ የምትታየው ወጣት ማን ነች? ያዕቆብስ ምን አደረገላት?

  2. ያዕቆብ ራሄልን ለማግባት ሲል ምን ለማድረግ ፈቃደኛ ነበር?

  3. ያዕቆብ ራሄልን የሚያገባበት ጊዜ ሲደርስ ላባ ምን አደረገ?

  4. ያዕቆብ ራሄልን ለማግባት ሲል ምን ለማድረግ ተስማማ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፍጥረት 29:1-30ን አንብብ።

    1. (ሀ) ላባ ያዕቆብን ቢያታልለውም እንኳን ያዕቆብ የተከበረ ሰው መሆኑን ያሳየው እንዴት ነው? እኛስ ከዚህ ምን እንማራለን? (ዘፍ. 25:27፤ 29:26-28፤ ማቴ. 5:37)

    2. (ለ) ያዕቆብ የተወው ምሳሌ በእውነተኛ ፍቅርና በወረት ፍቅር መካከል ያለውን ልዩነት የሚያሳየው እንዴት ነው? (ዘፍ. 29:18, 20, 30፤ ማሕ. 8:6)

    3. (ሐ) የያዕቆብ ቤተሰብ አባሎች የሆኑትና በኋላም ልጆች የወለዱለት አራት ሴቶች እነማን ናቸው? (ዘፍ. 29:23, 24, 28, 29)

ታሪክ 19

ያዕቆብ ትልቅ ቤተሰብ አለው

  1. ያዕቆብ ከመጀመሪያ ሚስቱ ከልያ የወለዳቸው ስድስት ወንዶች ልጆች ስም ማን ነው?

  2. የልያ አገልጋይ ዘለፋ ለያዕቆብ የወለደቻቸው ሁለት ወንዶች ልጆች እነማን ናቸው?

  3. የራሄል አገልጋይ ባላ ለያዕቆብ የወለደቻቸው ሁለት ወንዶች ልጆች እነማን ናቸው?

  4. ራሄል የወለደቻቸው ሁለት ወንዶች ልጆች እነማን ናቸው? ሁለተኛ ልጅዋን በምትወልድበት ጊዜ ግን ምን ሆነ?

  5. በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው ያዕቆብ ስንት ወንዶች ልጆች አሉት? ከእነሱስ እነማን ተገኙ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፍጥረት 29:32-35፤ 30:1-26 እና ዘፍጥረት 35:16-19ን አንብብ።

    በያዕቆብ 12 ወንዶች ልጆች እንደታየው በድሮ ዘመን ዕብራውያን ወንዶች ልጆች አብዛኛውን ጊዜ ስም የሚወጣላቸው እንዴት ነበር?

  2. ዘፍጥረት 37:35ን አንብብ።

    በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሰችው ዲና ብቻ ብትሆንም እንኳን ያዕቆብ ሌሎች ሴቶች ልጆች እንደነበሩት እንዴት እናውቃለን? (ዘፍ. 37:34, 35)

ታሪክ 20

ዲና ችግር አጋጠማት

  1. አብርሃምና ይስሐቅ ልጆቻቸው በከነዓን ምድር ከሚኖሩት ሰዎች ጋር እንዲጋቡ የማይፈልጉት ለምን ነበር?

  2. ያዕቆብ ሴት ልጁ ከከነዓናውያን ልጃገረዶች ጋር ጓደኝነት መመሥረቷን ይደግፈው ነበር?

  3. በሥዕሉ ላይ ዲናን እየተመለከታት ያለው ሰው ማን ነው? ምን መጥፎ ነገርስ ፈጸመ?

  4. የዲና ወንድሞች ስምዖንና ሌዊ የሆነውን ነገር ሲሰሙ ምን አደረጉ?

  5. ያዕቆብ ስምዖንና ሌዊ ባደረጉት ነገር ተስማምቶ ነበር?

  6. በቤተሰቡ ላይ ለደረሰው ችግር በሙሉ መንስኤ የሆነው ነገር ምንድን ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፍጥረት 34:1-31ን አንብብ።

    1. (ሀ) ዲና ከከነዓን ምድር ሴቶች ጋር መገናኘቷ አንድ ቀን ብቻ የተፈጠረ አጋጣሚ ነው? አብራራ። (ዘፍ. 34:1)

    2. (ለ) ዲና ክብረ ንጽሕናዋን ለማጣቷ በከፊል ተጠያቂ የምትሆነው ለምንድን ነው? (ገላ. 6:7)

    3. (ሐ) በዛሬው ጊዜ ያሉ ወጣቶች የዲናን የማስጠንቀቂያ ምሳሌ ልብ እንዳሉት ሊያሳዩ የሚችሉት እንዴት ነው? (ምሳሌ 13:20፤ 1 ቆሮ. 15:33፤ 1 ዮሐ. 5:19)

ታሪክ 21

ዮሴፍን ወንድሞቹ ጠሉት

  1. የዮሴፍ ወንድሞች የቀኑበት ለምን ነበር? ምንስ አደረጉ?

  2. ዮሴፍን ወንድሞቹ ምን ሊያደርጉት ፈለጉ? ሮቤል ግን ምን አለ?

  3. እስማኤላውያን ነጋዴዎች ሲመጡ ምን ሆነ?

  4. የዮሴፍ ወንድሞች አባታቸው ዮሴፍ ሞቷል ብሎ እንዲያስብ ምን አደረጉ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፍጥረት 37:1-35ን አንብብ።

    1. (ሀ) ክርስቲያኖች በጉባኤ ውስጥ ኃጢአት ሲሠራ ካዩ በመናገር የዮሴፍን ምሳሌነት ሊኮርጁ የሚችሉት እንዴት ነው? (ዘፍ. 37:2፤ ዘሌ. 5:1፤ 1 ቆሮ. 1:11)

    2. (ለ) ዮሴፍን ወንድሞቹ ክህደት እንዲፈጽሙበት ያደረጋቸው ነገር ምንድን ነው? (ዘፍ. 37:11, 18፤ ምሳሌ 27:4፤ ያዕ. 3:14-16)

    3. (ሐ) ያዕቆብ ያደረገው ምን የተለመደ የሐዘን መግለጫ ነው? (ዘፍ. 37:35)

ታሪክ 22

ዮሴፍ እስር ቤት ገባ

  1. ዮሴፍ ወደ ግብፅ ሲወሰድ ዕድሜው ስንት ነበር? እዚያ ሲደርስስ ምን ሆነ?

  2. ዮሴፍ እስር ቤት ሊገባ የቻለው እንዴት ነው?

  3. ዮሴፍ በእስር ቤት ምን ኃላፊነት ተሰጠው?

  4. ዮሴፍ በእስር ቤት ሳለ ለፈርዖን የመጠጥ አሳላፊና ለእንጀራ ቤቱ ኃላፊ ምን አደረገላቸው?

  5. የመጠጥ አሳላፊው ከእስር ቤት ከተፈታ በኋላ ምን ሆነ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፍጥረት 39:1-23ን አንብብ።

    በዮሴፍ ዘመን ምንዝርን የሚከለክል ከአምላክ የተሰጠ ሕግ ስላልነበረ ዮሴፍን ከጶጢፋር ሚስት እንዲሸሽ የገፋፋው ምን ነበር? (ዘፍ. 2:24፤ 20:3፤ 39:9)

  2. ዘፍጥረት 40:1-23ን አንብብ።

    1. (ሀ) የመጠጥ አሳላፊው ያየውን ሕልምና ይሖዋ ለዮሴፍ የሰጠውን ፍቺ በአጭሩ ግለጽ። (ዘፍ. 40:9-13)

    2. (ለ) የእንጀራ ቤቱ ኃላፊ ምን ሕልም አየ? ትርጉሙስ ምን ነበር? (ዘፍ. 40:16-19)

    3. (ሐ) በዛሬው ጊዜ ያለው ታማኝና ልባም ባሪያ የዮሴፍን ዓይነት አመለካከት የሚያንጸባርቀው እንዴት ነው? (ዘፍ. 40:8፤ መዝ. 36:9፤ ዮሐ. 17:17፤ ሥራ 17:2, 3)

    4. (መ) ዘፍጥረት 40:20 ክርስቲያኖች የልደት ክብረ በዓልን በተመለከተ ሊኖራቸው የሚገባውን አመለካከት የሚጠቁመው እንዴት ነው? (መክ. 7:1፤ ማር. 6:21-28)

ታሪክ 23

የፈርዖን ሕልሞች

  1. ፈርዖን አንድ ቀን ሌሊት ምን ሁኔታ አጋጠመው?

  2. የመጠጥ አሳላፊው በመጨረሻ ዮሴፍን ያስታወሰው ለምንድን ነው?

  3. በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው ፈርዖን ምን ሁለት ሕልሞች አየ?

  4. ዮሴፍ የሕልሙ ትርጉም ምን መሆኑን ተናገረ?

  5. ዮሴፍ በግብፅ ምድር ከፈርዖን ቀጥሎ ታላቅ ባለ ሥልጣን ለመሆን የበቃው እንዴት ነው?

  6. የዮሴፍ ወንድሞች ወደ ግብፅ የሄዱት ለምን ነበር? ዮሴፍን ሊያውቁት ያልቻሉትስ ለምንድን ነው?

  7. ዮሴፍ ምን ሕልም አስታወሰ? ይህስ ምን እንዲረዳ አስቻለው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፍጥረት 41:1-57ን አንብብ።

    1. (ሀ) ዮሴፍ በፈርዖን ፊት ቀርቦ ሕልሙን ሲፈታ ክብሩን ለይሖዋ የሰጠው እንዴት ነው? በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያኖች የዮሴፍን ምሳሌ መኮረጅ የሚችሉት በምን መንገድ ነው? (ዘፍ. 41:16, 25, 28፤ ማቴ. 5:16፤ 1 ጴጥ. 2:12)

    2. (ለ) በግብፅ ምድር የረሀብ ዘመንን አስከትለው የመጡት ምርት የተትረፈረፈባቸው ዓመታት በዛሬው ጊዜ በይሖዋ ሕዝቦች መንፈሳዊ ሁኔታና በሕዝበ ክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት በግልጽ የሚያሳዩት እንዴት ነው? (ዘፍ. 41:29, 30፤ አሞጽ 8:11, 12)

  2. ዘፍጥረት 42:1-8ን እና 50:20ን አንብብ።

    በአገሩ ልማድ መሠረት በአንድ ባለ ሥልጣን ፊት ሲቀረብ ለሥልጣኑ አክብሮት ለመግለጽ ለጥ ብሎ እጅ መንሳት የተለመደ ከሆነ የይሖዋ አምላኪዎችም እንዲህ ቢያደርጉ ስህተት ነው? (ዘፍ. 42:6)

ታሪክ 24

ዮሴፍ ወንድሞቹን ፈተናቸው

  1. ዮሴፍ ወንድሞቹን ሰላዮች ናችሁ ያላቸው ለምን ነበር?

  2. ያዕቆብ የሁሉም ታናሽ የሆነው ልጁ ብንያም ወደ ግብፅ እንዲሄድ የፈቀደው ለምን ነበር?

  3. የዮሴፍ የብር ጽዋ በብንያም ስልቻ ውስጥ ሊገኝ የቻለው እንዴት ነው?

  4. ይሁዳ ብንያምን ለማስለቀቅ ምን ሐሳብ አቀረበ?

  5. የዮሴፍ ወንድሞች እንደተለወጡ የታየው እንዴት ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፍጥረት 42:9-38ን አንብብ።

    በዘፍጥረት 42:18 ላይ የሚገኘው የዮሴፍ አነጋገር በዛሬው ጊዜ በይሖዋ ድርጅት ውስጥ ኃላፊነት ላላቸው ሰዎች ጥሩ ማሳሰቢያ የሚሆናቸው እንዴት ነው? (ነህ. 5:15፤ 2 ቆሮ. 7:1, 2)

  2. ዘፍጥረት 43:1-34ን አንብብ።

    1. (ሀ) በኩር የሆነው ሮቤል ቢሆንም ይሁዳ የወንድሞቹ ቃል አቀባይ እንደሆነ በግልጽ የታየው እንዴት ነው? (ዘፍ. 43:3, 8, 9፤ 44:14, 18፤ 1 ዜና 5:2)

    2. (ለ) ዮሴፍ ወንድሞቹን በግልጽ የፈተናቸው እንዴት ነው? ለምንስ? (ዘፍ. 43:33, 34)

  3. ዘፍጥረት 44:1-34ን አንብብ።

    1. (ሀ) ዮሴፍ ማንነቱ እንዳይታወቅ ሲል ራሱን ምን አስመስሎ አቀረበ? (ዘፍ. 44:5, 15፤ ዘሌ. 19:26)

    2. (ለ) የዮሴፍ ወንድሞች በፊት ለወንድማቸው የነበራቸው የምቀኝነት መንፈስ እንደለቀቃቸው ያሳዩት እንዴት ነው? (ዘፍ. 44:13, 33, 34)

ታሪክ 25

ቤተሰቡ ወደ ግብፅ ሄደ

  1. ዮሴፍ ራሱን ለወንድሞቹ ሲገልጥ ምን ሆነ?

  2. ዮሴፍ ለወንድሞቹ ደግነት በተሞላበት ሁኔታ ምን ገለጸላቸው?

  3. ፈርዖን ስለ ዮሴፍ ወንድሞች ሲሰማ ምን አለ?

  4. የያዕቆብ ቤተሰብ ወደ ግብፅ ሲገቡ ብዛታቸው ምን ያህል ነበር?

  5. የያዕቆብ ቤተሰብ ምን ተብለው ተጠሩ? ለምንስ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፍጥረት 45:1-28ን አንብብ።

    በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው የዮሴፍ ታሪክ ይሖዋ አገልጋዮቹን ለመጉዳት ታስቦ የተደረገን ነገር ለበጎ ሊለውጠው እንደሚችል የሚያሳየው እንዴት ነው? (ዘፍ. 45:5-8፤ ኢሳ. 8:10፤ ፊልጵ. 1:12-14)

  2. ዘፍጥረት 46:1-27ን አንብብ።

    ያዕቆብ ወደ ግብፅ በሚሄድበት ጊዜ ይሖዋ ምን ዋስትና ሰጠው? (ዘፍጥረት 46:1-4የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ)

ታሪክ 26

ኢዮብ ለአምላክ ታማኝ ሆኗል

  1. ኢዮብ ማን ነበር?

  2. ሰይጣን ምን ለማድረግ ሞከረ? ይሁን እንጂ ተሳክቶለታል?

  3. ይሖዋ ለሰይጣን ምን እንዲያደርግ ፈቀደለት? ለምንስ?

  4. የኢዮብ ሚስት “እግዚአብሔርን ስደብና ሙት” ያለችው ለምን ነበር? (ሥዕሉን ተመልከት።)

  5. በሁለተኛው ሥዕል ላይ እንደምትመለከተው ይሖዋ ኢዮብን የባረከው እንዴት ነው? ለምንስ?

  6. እኛም እንደ ኢዮብ ለይሖዋ ታማኞች ከሆንን ምን በረከት እናገኛለን?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ኢዮብ 1:1-22ን አንብብ።

    በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያኖች ኢዮብን ሊመስሉት የሚችሉት እንዴት ነው? (ኢዮብ 1:1፤ ፊልጵ. 2:15፤ 2 ጴጥ. 3:14)

  2. ኢዮብ 2:1-13ን አንብብ።

    ኢዮብና ሚስቱ ሰይጣን ላመጣባቸው ስደት ምላሽ የሰጡባቸው ሁለት የተለያዩ መንገዶች ምንድን ናቸው? (ኢዮብ 2:9, 10፤ ምሳሌ 19:3፤ ሚክ. 7:7፤ ሚል. 3:14)

  3. ኢዮብ 42:10-17ን አንብብ።

    1. (ሀ) ኢዮብና ኢየሱስ ለተከተሉት የታማኝነት ጎዳና የተቀበሏቸው ሽልማቶች ምን ተመሳሳይነት አላቸው? (ኢዮብ 42:12፤ ፊልጵ. 2:9-11)

    2. (ለ) ኢዮብ ለአምላክ ታማኝ በመሆኑ ያገኘው በረከት እኛን የሚያበረታታን እንዴት ነው? (ኢዮብ 42:10, 12፤ ዕብ. 6:10፤ ያዕ. 1:2-4, 12፤ 5:11)

ታሪክ 27

አንድ ክፉ ንጉሥ ግብፅን መግዛት ጀመረ

  1. በሥዕሉ ላይ የሚታየው መግረፊያ የያዘው ሰው ማን ነው? እየገረፈ ያለውስ ማንን ነው?

  2. ዮሴፍ ከሞተ በኋላ እስራኤላውያን ምን ደረሰባቸው?

  3. ግብፃውያን እስራኤላውያንን የፈሯቸው ለምንድን ነው?

  4. ፈርዖን እስራኤላውያንን ለሚያዋልዱት ሴቶች ምን ትእዛዝ ሰጣቸው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፀአት 1:6-22ን አንብብ።

    1. (ሀ) ይሖዋ ለአብርሃም የገባለትን ቃል ኪዳን መፈጸም የጀመረው በምን መንገድ ነበር? (ዘፀ. 1:7፤ ዘፍ. 12:2፤ ሥራ 7:17)

    2. (ለ) ዕብራውያን አዋላጆች ለሕይወት ቅድስና አክብሮት ያሳዩት እንዴት ነው? (ዘፀ. 1:17፤ ዘፍ. 9:6)

    3. (ሐ) አዋላጆቹ ለይሖዋ ላሳዩት ታማኝነት የተካሱት እንዴት ነው? (ዘፀ. 1:20, 21፤ ምሳሌ 19:17)

    4. (መ) ሰይጣን ትንቢት የተነገረለትን የአብርሃም ዘር በተመለከተ ይሖዋ ያለውን ዓላማ ለማጨናገፍ ሙከራ ያደረገው እንዴት ነው? (ዘፀ. 1:22፤ ማቴ. 2:16)

ታሪክ 28

ሕፃኑ ሙሴ ከሞት የዳነበት ሁኔታ

  1. በሥዕሉ ላይ የሚታየው ሕፃን ማን ነው? የጨበጠውስ የማንን ጣት ነው?

  2. የሙሴ እናት ሙሴን ከመገደል ለማዳን ስትል ምን አደረገች?

  3. በሥዕሉ ላይ የምትታየው ትንሽ ልጃገረድ ማን ናት? ምንስ አደረገች?

  4. የፈርዖን ሴት ልጅ ሕፃኑን ባገኘችው ጊዜ ሚርያም ምን ሐሳብ አቀረበች?

  5. ልዕልቷ ለሙሴ እናት ምን አለቻት?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፀአት 2:1-10ን አንብብ።

    የሙሴ እናት እሱን በሕፃንነቱ ወራት ለማሠልጠንና ለማስተማር ምን አጋጣሚ ነበራት? ይህስ በዛሬው ጊዜ ላሉ ወላጆች ምን ምሳሌ ይሆናቸዋል? (ዘፀ. 2:9, 10፤ ዘዳ. 6:6-9፤ ምሳሌ 22:6፤ ኤፌ. 6:4፤ 2 ጢሞ. 3:15)

ታሪክ 29

ሙሴ የሸሸበት ምክንያት

  1. ሙሴ ያደገው የት ነው? ይሁንና ስለ ወላጆቹ ምን ያውቅ ነበር?

  2. ሙሴ 40 ዓመት ሲሆነው ምን አደረገ?

  3. ሙሴ ሲጣላ ያገኘውን እስራኤላዊ ምን አለው? ሰውየውስ ምን መልስ ሰጠ?

  4. ሙሴ ከግብፅ ሸሽቶ የሄደው ለምንድን ነው?

  5. ሙሴ ሸሽቶ የሄደው ወዴት ነው? እዚያስ ማንን አገኘ?

  6. ሙሴ ከግብፅ ሸሽቶ ከሄደ በኋላ ለ40 ዓመታት ምን ሲያደርግ ቆየ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፀአት 2:11-25ን አንብብ።

    ሙሴ የግብፅን ጥበብ ሁሉ የተማረ ቢሆንም እንኳ ለይሖዋና ለሕዝቦቹ ታማኝ መሆኑን ያሳየው እንዴት ነው? (ዘፀ. 2:11, 12፤ ዕብ. 11:24)

  2. የሐዋርያት ሥራ 7:22-29ን አንብብ።

    ሙሴ በራሱ ተነሳሽነት የእስራኤልን ሕዝብ ከባርነት ለማዳን ካደረገው ሙከራ ምን እንማራለን? (ሥራ 7:23-25፤ 1 ጴጥ. 5:6, 10)

ታሪክ 30

በእሳት የተያያዘው ቁጥቋጦ

  1. በሥዕሉ ላይ የሚታየው ተራራ ምን ተብሎ ይጠራል?

  2. ሙሴ በጎቹን ይዞ ወደ ተራራው በሄደ ጊዜ ምን ያልተለመደ ነገር እንዳየ ግለጽ።

  3. በእሳት ከተያያዘው ቁጥቋጦ ውስጥ ምን ድምፅ ተሰማ? ድምፁስ የማን ነበር?

  4. ሕዝቡን እየመራ ከግብፅ እንደሚያወጣቸው አምላክ ሲነግረው ሙሴ ምን መልስ ሰጠ?

  5. አምላክ፣ ሕዝቡ ሙሴን ማን እንደላከው ከጠየቁት ምን እንዲላቸው ነገረው?

  6. ሙሴ አምላክ እንደላከው ማስረጃ ማቅረብ የሚችለው እንዴት ነበር?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፀአት 3:1-22ን አንብብ።

    የሙሴ ተሞክሮ አንድን ቲኦክራሲያዊ ሥራ ለመፈጸም ብቃት እንደሌለን ቢሰማንም እንኳ ይሖዋ እንደሚረዳን እንድንተማመን የሚያደርገን እንዴት ነው? (ዘፀ. 3:11, 13፤ 2 ቆሮ. 3:5, 6)

  2. ዘፀአት 4:1-20ን አንብብ።

    1. (ሀ) ሙሴ በምድያም በቆየባቸው 40 ዓመታት ምን የአመለካከት ለውጥ አድርጓል? በጉባኤ ውስጥ መብት ለማግኘት በመጣጣር ላይ ያሉ ወንድሞች ከዚህ ምን ትምህርት ሊያገኙ ይችላሉ? (ዘፀ. 2:11, 12፤ 4:10, 13፤ ሚክ. 6:8፤ 1 ጢሞ. 3:1, 6, 10)

    2. (ለ) ይሖዋ በድርጅቱ በኩል ተግሣጽ ቢሰጠንም እንኳን የሙሴ ምሳሌ ስለምን ነገር እርግጠኞች እንድንሆን ያደርገናል? (ዘፀ. 4:12-14፤ መዝ. 103:14፤ ዕብ. 12:4-11)

ታሪክ 31

ሙሴና አሮን ፈርዖንን አነጋገሩት

  1. ሙሴና አሮን የፈጸሟቸው ተአምራት በእስራኤላውያን ላይ ምን ተጽዕኖ አሳደሩ?

  2. ሙሴና አሮን ለፈርዖን ምን ነገሩት? የፈርዖንስ ምላሽ ምን ነበር?

  3. በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው አሮን በትሩን መሬት ላይ ሲጥለው ምን ሆነ?

  4. ይሖዋ ለፈርዖን ትምህርት የሰጠው እንዴት ነው? ፈርዖንስ ምን አለ?

  5. ከአሥረኛው መቅሠፍት በኋላ ምን ሆነ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፀአት 4:27-31ን እና 5:1-23ን አንብብ።

    ፈርዖን “ይሖዋን አላውቅም” ሲል ምን ማለቱ ነበር? (ዘፀ. 5:2 NW፤ 1 ሳሙ. 2:12፤ ሮሜ 1:21)

  2. ዘፀአት 6:1-13, 26-30ን አንብብ።

    1. (ሀ) ይሖዋ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ያልታወቀላቸው በምን መልኩ ነበር? (ዘፀ. 3:13, 14፤ 6:3፤ ዘፍ. 12:8)

    2. (ለ) ሙሴ ለተላከበት ሥራ ብቁ እንዳልሆነ ቢሰማውም እንኳ ይሖዋ የተጠቀመበት መሆኑን ማወቃችን ምን እንዲሰማን ያደርጋል? (ዘፀ. 6:12, 30፤ ሉቃስ 21:13-15)

  3. ዘፀአት 7:1-13ን አንብብ።

    1. (ሀ) ሙሴና አሮን የይሖዋን የፍርድ መልእክት ለፈርዖን በድፍረት በመናገራቸው በዛሬው ጊዜ ላሉት የአምላክ አገልጋዮች ምን ምሳሌ ትተዋል? (ዘፀ. 7:2, 3, 6፤ ሥራ 4:29-31)

    2. (ለ) ይሖዋ በግብፅ አማልክት ላይ የበላይነቱን ያሳየው እንዴት ነው? (ዘፀ. 7:12፤ 1 ዜና 29:12)

ታሪክ 32

አሥሩ መቅሰፍቶች

  1. እዚህ ላይ የቀረቡትን ሥዕሎች መሠረት በማድረግ ይሖዋ በግብፅ ላይ ያመጣቸውን የመጀመሪያዎቹን ሦስት መቅሰፍቶች ግለጽ።

  2. በመጀመሪያዎቹ ሦስት መቅሰፍቶችና በተቀሩት መቅሰፍቶች መካከል የነበረው ልዩነት ምንድን ነው?

  3. አራተኛው፣ አምስተኛውና ስድስተኛው መቅሰፍቶች ምን ነበሩ?

  4. ሰባተኛው፣ ስምንተኛውና ዘጠነኛው መቅሰፍቶች ምን እንደሆኑ ግለጽ።

  5. አሥረኛው መቅሰፍት ከመምጣቱ በፊት አምላክ ለእስራኤላውያን ምን እንዲያደርጉ ነገራቸው?

  6. አሥረኛው መቅሰፍት ምን ነበር? ከዚህ መቅሰፍት በኋላስ ምን ተፈጸመ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፀአት 7:19 እስከ 8:23ን አንብብ።

    1. (ሀ) የግብፅ አስማተኞች የይሖዋን የመጀመሪያ ተአምራት አስመስለው መሥራት ቢችሉም ከሦስተኛው መቅሰፍት በኋላ ግን ምን ለመቀበል ተገደዋል? (ዘፀ. 8:18, 19፤ ማቴ. 12:24-28)

    2. (ለ) አራተኛው መቅሰፍት ይሖዋ ሕዝቡን ለመጠበቅ ያለውን ኃይል ያሳየው እንዴት ነው? የአምላክ ሕዝቦች ይህን ማወቃቸው አስቀድሞ በትንቢት የተነገረው “ታላቅ መከራ” በሚመጣበት ጊዜ ምን እንዲሰማቸው ያደርጋል? (ዘፀ. 8:22, 23፤ ራእይ 7:13, 14፤ 2 ዜና 16:9)

  2. ዘፀአት 8:24፤ 9:3, 6, 10, 11, 14, 16, 23-25 እና 10:13-15, 21-23ን አንብብ።

    1. (ሀ) አሥሩ መቅሰፍቶች የትኞቹን ሁለት ወገኖች የሚያጋልጡ ነበሩ? ይህስ በዛሬው ጊዜ ለእነዚህ ወገኖች ያለንን አመለካከት የሚነካው እንዴት ነው? (ዘፀ. 8:10, 18, 19፤ 9:14)

    2. (ለ) ዘፀአት 9:16 ሰይጣን እስካሁን ድረስ እንዲኖር የተፈቀደለት ለምን እንደሆነ እንድንገነዘብ የሚረዳን እንዴት ነው? (ሮሜ 9:21, 22)

  3. ዘፀአት 12:21-32ን አንብብ።

    የማለፍ በዓል ብዙዎች መዳን እንዲያገኙ ያስቻለው እንዴት ነው? የማለፍ በዓል ምን ያመለክታል? (ዘፀ. 12:21-23፤ ዮሐ. 1:29፤ ሮሜ 5:18, 19, 21፤ 1 ቆሮ. 5:7)

ታሪክ 33

ቀይ ባሕርን መሻገር

  1. ከሴቶቹና ከሕፃናቱ ሌላ ከግብፅ የወጡት እስራኤላውያን ወንዶች ስንት ነበሩ? ከእነሱ ጋር የወጡት ሌሎች ሰዎችስ እነማን ነበሩ?

  2. ፈርዖን እስራኤላውያን እንዲሄዱ ከፈቀደላቸው በኋላ ምን ተሰማው? ምንስ አደረገ?

  3. ይሖዋ ሕዝቡን ከግብፃውያን ጥቃት ለመከላከል ምን አደረገ?

  4. ሙሴ በትሩን በቀይ ባሕር ላይ በዘረጋ ጊዜ ምን ሆነ? ከዚያስ እስራኤላውያን ምን አደረጉ?

  5. ግብፃውያን እስራኤላውያንን ተከትለው ወደ ባሕሩ ሲገቡ ምን ሆኑ?

  6. እስራኤላውያን ይሖዋ ስላዳናቸው መደሰታቸውንና አመስጋኞች መሆናቸውን ያሳዩት እንዴት ነበር?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፀአት 12:33-36ን አንብብ።

    ይሖዋ፣ ሕዝቡ በግብፅ ላሳለፉት የባርነት ሕይወት የልፋታቸውን ዋጋ እንዲያገኙ ያደረገው እንዴት ነው? (ዘፀ. 3:21, 22፤ 12:35, 36)

  2. ዘፀአት 14:1-31ን አንብብ።

    በ⁠ዘፀአት 14:13, 14 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘው የሙሴ ንግግር በቅርቡ በሚመጣው የአርማጌዶን ጦርነት ወቅት የይሖዋ አገልጋዮች ምን እንዲያደርጉ ይረዳቸዋል? (2 ዜና 20:17፤ መዝ. 91:8)

  3. ዘፀአት 15:1-8, 20, 21ን አንብብ።

    1. (ሀ) የይሖዋ አገልጋዮች ለእርሱ የምስጋና መዝሙር መዘመር የሚኖርባቸው ለምንድን ነው? (ዘፀ. 15:1, 2፤ መዝ. 105:2, 3፤ ራእይ 15:3, 4)

    2. (ለ) በቀይ ባሕር አጠገብ ሚርያምና ሌሎቹ እስራኤላውያን ሴቶች ለይሖዋ ያቀረቡት ውዳሴ በዛሬው ጊዜ ላሉት ክርስቲያን ሴቶች ምሳሌ የሚሆነው እንዴት ነው? (ዘፀ. 15:20, 21፤ መዝ. 68:11)

ታሪክ 34

አዲስ ዓይነት ምግብ

  1. በሥዕሉ ላይ እንደምታየው ሕዝቡ ከመሬት ላይ የሚለቅሙት ምንድን ነው? ምን ተብሎስ ይጠራል?

  2. ሙሴ መናውን ስለመልቀም ለሕዝቡ ምን መመሪያ ሰጠ?

  3. ይሖዋ ለሕዝቡ በስድስተኛው ቀን ምን እንዲያደርጉ ነገራቸው? ለምንስ?

  4. ሕዝቡ መናውን ለሰባተኛው ቀን ሲያስተርፉ ይሖዋ ምን ተአምር ፈጸመ?

  5. ይሖዋ ሕዝቡን መና የመገባቸው ለምን ያህል ጊዜ ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፀአት 16:1-36 እና ዘኍልቍ 11:7-9ን አንብብ።

    1. (ሀ) በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ ያለውን ሥልጣን የማክበርን አስፈላጊነት በተመለከተ ዘፀአት 16:8 ምን ያሳያል? (ዕብ. 13:17)

    2. (ለ) እስራኤላውያን በምድረ በዳ ሳሉ ሕልውናቸው የተመካው በይሖዋ ላይ መሆኑን በየዕለቱ እንዲያስታውሱ የሚያደርጋቸው ምን ነበር? (ዘፀ. 16:14-16, 35፤ ዘዳ. 8:2, 3)

    3. (ሐ) ኢየሱስ መናው ምን ምሳሌያዊ ትርጉም እንዳለው ተናግሯል? እኛስ “ከሰማይ [ከመጣው] እንጀራ” የምንጠቀመው እንዴት ነው? (ዮሐ. 6:31-35, 40)

  2. ኢያሱ 5:10-12ን አንብብ።

    እስራኤላውያን መና የበሉት ለስንት ዓመታት ነበር? ይህስ ፈተና የሆነባቸው እንዴት ነው? እኛስ ከዚህ ታሪክ ምን እንማራለን? (ዘፀ. 16:35፤ ዘኍ. 11:4-6፤ 1 ቆሮ. 10:10, 11)

ታሪክ 35

ይሖዋ ሕጎቹን ሰጠ

  1. እስራኤላውያን ከግብፅ ከወጡ ከሁለት ወራት ገደማ በኋላ የት ሰፈሩ?

  2. ይሖዋ፣ ሕዝቡ ምን እንዲያደርጉ እንደሚፈልግ ተናገረ? የሕዝቡስ መልስ ምን ነበር?

  3. ይሖዋ ለሙሴ ሁለት የድንጋይ ጽላቶች የሰጠው ለምን ነበር?

  4. ይሖዋ ለእስራኤላውያን ከአሥርቱ ትእዛዛት በተጨማሪ ምን ሕጎች ሰጣቸው?

  5. ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለቱ ታላላቅ ሕጎች ያላቸው የትኞቹን ትእዛዛት ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፀአት 19:1-25፤ 20:1-21፤ 24:12-18 እና 31:18ን አንብብ።

    በ⁠ዘፀአት 19:8 ላይ የተመዘገቡት ቃላት ራስን ወሰኖ ክርስቲያን መሆን ምን ማድረግን እንደሚጨምር እንድንገነዘብ የሚረዱት እንዴት ነው? (ማቴ. 16:24፤ 1 ጴጥ. 4:1-3)

  2. ዘዳግም 6:4-6፤ ዘሌዋውያን 19:18 እና ማቴዎስ 22:36-40ን አንብብ።

    ክርስቲያኖች ለአምላክና ለጎረቤቶቻቸው ክርስቲያናዊ ፍቅር የሚያሳዩት እንዴት ነው? (ማር. 6:34፤ ሥራ 4:20፤ ሮሜ 15:2)

ታሪክ 36

ከወርቅ የተሠራው ጥጃ

  1. በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው ሰዎቹ ምን እያደረጉ ነው? ለምንስ?

  2. ይሖዋ የተቆጣው ለምንድን ነው? ሙሴ ሰዎቹ የሚሠሩትን ሲያይ ምን አደረገ?

  3. ሙሴ ከሕዝቡ መካከል አንዳንዶቹን ምን እንዲያደርጉ ነገራቸው?

  4. ይህ ታሪክ ምን ትምህርት ሊሰጠን ይገባል?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፀአት 32:1-35ን አንብብ።

    1. (ሀ) ይህ ታሪክ ይሖዋ የሐሰት ሃይማኖትን ከእውነተኛው አምልኮ ጋር መቀላቀልን በተመለከተ ምን እንደሚሰማው የሚያሳየው እንዴት ነው? (ዘፀ. 32:4-6, 10፤ 1 ቆሮ. 10:7, 11)

    2. (ለ) ክርስቲያኖች እንደ ዘፈንና ጭፈራ ያሉትን መዝናኛዎች በሚመርጡበት ጊዜ ምን ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው? (ዘፀ. 32:18, 19፤ ኤፌ. 5:15, 16፤ 1 ዮሐ. 2:15-17)

    3. (ሐ) የሌዊ ነገድ ለጽድቅ በመቆም ረገድ ምን ጥሩ ምሳሌ ትቷል? (ዘፀ. 32:25-28፤ መዝ. 18:25)

ታሪክ 37

ለአምልኮ የሚያገለግል ድንኳን

  1. በሥዕሉ ላይ የሚታየው ቤት ምን ይባላል? ለምንስ አገልግሎት ይውል ነበር?

  2. ይሖዋ፣ ሙሴን ድንኳኑን በቀላሉ ሊነቃቀል እንደሚችል አድርጎ እንዲሠራው የነገረው ለምን ነበር?

  3. በድንኳኑ ጫፍ በሚገኘው አነስተኛ ክፍል ውስጥ ያለው ሣጥን ምንድን ነው? በሣጥኑ ውስጥ ምን አለ?

  4. ይሖዋ፣ ሊቀ ካህን እንዲሆን የመረጠው ማንን ነው? የሊቀ ካህኑ ተግባርስ ምንድን ነው?

  5. በሰፊው የድንኳኑ ክፍል ውስጥ የሚገኙትን ሦስት ነገሮች ጥቀስ።

  6. በማደሪያው ድንኳን ግቢ ውስጥ የሚገኙት ሁለት ነገሮች ምንድን ናቸው? አገልግሎታቸውስ ምንድን ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘፀአት 25:8-40፤ 26:1-37፤ 27:1-8 እና ዘፀአት 28:1ን አንብብ።

    “በምስክሩ ታቦት” ላይ ያሉት ኪሩቤል ምን ያመለክታሉ? (ዘፀ. 25:20, 22፤ ዘኍ. 7:89፤ 2 ነገ. 19:15)

  2. ዘፀአት 30:1-10, 17-21፤ 34:1, 2 እና ዕብራውያን 9:1-5ን አንብብ።

    1. (ሀ) ይሖዋ በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉት ካህናት አካላዊ ንጽሕናቸውን መጠበቃቸው አስፈላጊ መሆኑን በጥብቅ የገለጸው ለምን ነበር? ይህስ በዛሬው ጊዜ ለእኛ ምን ትምህርት ይዟል? (ዘፀ. 30:18-21፤ 40:30, 31፤ ዕብ. 10:22)

    2. (ለ) ሐዋርያው ጳውሎስ ለዕብራውያን ክርስቲያኖች ደብዳቤውን በጻፈበት ወቅት የመገናኛው ድንኳንና የሕጉ ቃል ኪዳን የሚሰጡት አገልግሎት እንዳበቃ ያሳየው እንዴት ነው? (ዕብ. 9:1, 9፤ 10:1)

ታሪክ 38

አሥራ ሁለቱ ሰላዮች

  1. በሥዕሉ ላይ ከሚታየው የወይን ዘለላ ምን ልዩ ነገር ተመለከትህ? ይህ ወይን ከየት የመጣ ነው?

  2. ሙሴ ወደ ከነዓን ምድር አሥራ ሁለት ሰላዮች የላከው ለምን ነበር?

  3. አሥሩ ሰላዮች ወደ ሙሴ ሲመለሱ ምን ተናገሩ?

  4. ሁለት ሰላዮች በይሖዋ እንደሚተማመኑ ያሳዩት እንዴት ነው? ስማቸውስ ማን ይባላል?

  5. ይሖዋ የተቆጣው ለምን ነበር? ሙሴንስ ምን አለው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘኍልቍ 13:1-33ን አንብብ።

    1. (ሀ) ምድሪቱን እንዲሰልሉ የተመረጡት እነማን ነበሩ? ምን አስደሳች አጋጣሚስ ነበራቸው? (ዘኍ. 13:2, 3, 18-20)

    2. (ለ) ኢያሱና ካሌብ ከሌሎቹ ሰላዮች የተለየ አመለካከት የነበራቸው ለምን ነበር? ይህስ ለእኛ ምን ያስተምረናል? (ዘኍ. 13:28-30፤ ማቴ. 17:20፤ 2 ቆሮ. 5:7)

  2. ዘኍልቍ 14:1-38ን አንብብ።

    1. (ሀ) በይሖዋ ምድራዊ ወኪሎች ላይ ማጉረምረምን በተመለከተ የትኛውን ማስጠንቀቂያ ልብ ልንለው ይገባል? (ዘኍ. 14:2, 3, 27፤ ማቴ. 25:40, 45፤ 1 ቆሮ. 10:10)

    2. (ለ) ዘኍልቍ 14:24 ይሖዋ ለእያንዳንዱ አገልጋዩ በግል ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ የሚያመለክተው እንዴት ነው? (1 ነገ. 19:18፤ ምሳሌ 15:3)

ታሪክ 39

የአሮን በትር አበባ አወጣች

  1. በሙሴና በአሮን ሥልጣን ላይ ያመጹት እነማን ነበሩ? ዓመጸኞቹ ሙሴን ምን አሉት?

  2. ሙሴ ለቆሬና ለ250 ተከታዮቹ ምን እንዲያደርጉ ነገራቸው?

  3. ሙሴ ለሕዝቡ ምን አላቸው? ተናግሮ እንደጨረሰስ ምን ሆነ?

  4. ቆሬና 250 ተከታዮቹ ምን ደረሰባቸው?

  5. የአሮን ልጅ አልዓዛር የሞቱትን ሰዎች ጥናዎች ወስዶ ምን አደረገበት? ለምንስ?

  6. ይሖዋ የአሮን በትር አበባ እንድታወጣ ያደረገው ለምን ነበር? (ሥዕሉን ተመልከት።)

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘኍልቍ 16:1-49ን አንብብ።

    1. (ሀ) ቆሬና ተከታዮቹ ምን አደረጉ? ይህስ በይሖዋ ላይ እንደማመጽ የተቆጠረው ለምንድን ነው? (ዘኍ. 16:9, 10, 18፤ ዘሌ. 10:1, 2፤ ምሳሌ 11:2)

    2. (ለ) ቆሬና 250 “የማኅበረ ሰቡ መሪዎች” ምን የተሳሳተ አመለካከት ነበራቸው? (ዘኍ. 16:1-3፤ ምሳሌ 15:33፤ ኢሳ. 49:7)

  2. ዘኍልቍ 17:1-11 እና 26:10ን አንብብ።

    1. (ሀ) የአሮን በትር አበባ ማውጣቷ ምን ያመለክት ነበር? ይሖዋ የአሮን በትር በታቦቱ ውስጥ እንድትቀመጥ ያዘዘው ለምን ነበር? (ዘኍ. 17:5, 8, 10)

    2. (ለ) የአሮን በትር አበባ ማውጣቷ ምን ጠቃሚ ትምህርት ይሰጠናል? (ዘኍ. 17:10፤ ሥራ 20:28፤ ፊልጵ. 2:14፤ ዕብ. 13:17)

ታሪክ 40

ሙሴ አለቱን መታ

  1. እስራኤላውያን በምድረ በዳ ሳሉ ይሖዋ የተንከባከባቸው እንዴት ነው?

  2. እስራኤላውያን በቃዴስ ሰፍረው እያለ ምን ብለው አጉረመረሙ?

  3. ይሖዋ ለሕዝቡና ለእንስሶቻቸው ውኃ የሰጣቸው እንዴት ነው?

  4. በሥዕሉ ላይ ወደ ራሱ እየጠቆመ ያለው ሰው ማን ነው? እንዲህ ያደረገውስ ለምንድን ነው?

  5. ይሖዋ በሙሴና በአሮን ላይ የተቆጣው ለምንድን ነው? የተቀጡትስ እንዴት ነው?

  6. በሖር ተራራ ላይ ምን ተፈጸመ? ከዚያ በኋላ የእስራኤል ሊቀ ካህን የሆነው ማን ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘኍልቍ 20:1-13, 22-29 እና ዘዳግም 29:5ን አንብብ።

    1. (ሀ) እስራኤላውያን በበረሃ ሳሉ ይሖዋ ካደረገላቸው እንክብካቤ ምን እንማራለን? (ዘዳ. 29:5፤ ማቴ. 6:31፤ ዕብ. 13:5፤ ያዕ. 1:17)

    2. (ለ) ይሖዋ ሙሴና አሮን በእስራኤላውያን ፊት ሳይቀድሱት መቅረታቸውን እንዴት ተመለከተው? (ዘኍ. 20:12፤ 1 ቆሮ. 10:12፤ ራእይ 4:11)

    3. (ሐ) ሙሴ ይሖዋ የሰጠውን ተግሣጽ ከተቀበለበት መንገድ ምን እንማራለን? (ዘኍ. 12:3፤ 20:12, 27, 28፤ ዘዳ. 32:4፤ ዕብ. 12:7-11)

ታሪክ 41

የነሐስ እባብ

  1. በሥዕሉ ላይ እንደምታየው በእንጨቱ ላይ የተጠመጠመው ምንድን ነው? ይሖዋ ሙሴ እንዲህ እንዲያደርግ ያዘዘው ለምን ነበር?

  2. ሕዝቡ አምላክ ላደረገላቸው ነገር ሁሉ አመስጋኝ ያልሆኑት እንዴት ነው?

  3. ይሖዋ እነርሱን ለመቅጣት መርዛማ እባቦች ከላከባቸው በኋላ ሕዝቡ ሙሴ ምን እንዲያደርግ ጠየቁት?

  4. ይሖዋ፣ ሙሴ የነሐስ እባብ እንዲሠራ ያዘዘው ለምን ነበር?

  5. እኛስ ከዚህ ታሪክ ምን እንማራለን?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘኍልቍ 21:4-9ን አንብብ።

    1. (ሀ) እስራኤላውያን ይሖዋ ያዘጋጀላቸውን ምግብ በተመለከተ ማጉረምረማቸው ለእኛ ምን ማስጠንቀቂያ ይሆነናል? (ዘኍ. 21:5, 6፤ ሮሜ 2:4)

    2. (ለ) እስራኤላውያን በቀጣዮቹ መቶ ዘመናት የነሐሱን እባብ ምን ለማድረግ ተጠቀሙበት? ንጉሥ ሕዝቅያስስ ምን እርምጃ ወሰደ? (ዘኍ. 21:9፤ 2 ነገ. 18:1-4)

  2. ዮሐንስ 3:14, 15ን አንብብ።

    የነሐሱ እባብ በእንጨት ላይ መሰቀሉ የኢየሱስ ክርስቶስን መሰቀል የሚያመለክተው እንዴት ነው? (ገላ. 3:13፤ 1 ጴጥ. 2:24)

ታሪክ 42

አንዲት አህያ ተናገረች

  1. ባላቅ ማን ነው? በለዓም ወደ እርሱ እንዲመጣ የላከበት ለምንድን ነው?

  2. የበለዓም አህያ መንገዱ ላይ የተኛችው ለምንድን ነው?

  3. አህያዋ በለዓምን ምን አለችው?

  4. አንድ መልአክ በለዓምን ምን አለው?

  5. በለዓም እስራኤልን ለመርገም ሲሞክር ምን ሆነ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘኍልቍ 21:21-35ን አንብብ።

    እስራኤላውያን የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንንና የባሳንን ንጉሥ ዐግን ድል ያደረጓቸው ለምን ነበር? (ዘኍ. 21:21, 23, 33, 34)

  2. ዘኍልቍ 22:1-40ን አንብብ።

    በለዓም እስራኤልን ለመርገም የተነሳው ለምን ነበር? እኛስ ከዚህ ምን ትምህርት እናገኛለን? (ዘኍ. 22:16, 17፤ ምሳሌ 6:16, 18፤ 2 ጴጥ. 2:15፤ ይሁዳ 11)

  3. ዘኍልቍ 23:1-30ን አንብብ።

    በለዓም የይሖዋ አምላኪ እንደሆነ ቢናገርም ይህ እውነት አለመሆኑን በተግባሩ ያሳየው እንዴት ነው? (ዘኍ. 23:3, 11-14፤ 1 ሳሙ. 15:22)

  4. ዘኍልቍ 24:1-25ን አንብብ።

    ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ የይሖዋ ዓላማ እንደሚፈጸም ያለንን እምነት የሚያጠናክርልን እንዴት ነው? (ዘኍ. 24:10፤ ኢሳ. 54:17)

ታሪክ 43

ኢያሱ መሪ ሆነ

  1. በሥዕሉ ላይ ከሙሴ ጋር ቆመው የሚታዩት ሁለት ሰዎች እነማን ናቸው?

  2. ይሖዋ ኢያሱን ምን አለው?

  3. ሙሴ ወደ ናባው ተራራ ጫፍ የወጣው ለምንድን ነው? እዚያ ሳለ ይሖዋ ምን አለው?

  4. ሙሴ ሲሞት ዕድሜው ስንት ነበር?

  5. ሕዝቡ ያዘኑት ለምንድን ነው? ይሁን እንጂ እንዲደሰቱ የሚያደርግ ምን ምክንያት አላቸው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዘኍልቍ 27:12-23ን አንብብ።

    ኢያሱ ከይሖዋ ምን ከባድ ኃላፊነት ተቀበለ? በዛሬው ጊዜ ይሖዋ ለሕዝቡ እንደሚያስብ የሚታየው እንዴት ነው? (ዘኍ. 27:15-19፤ ሥራ 20:28፤ ዕብ. 13:7)

  2. ዘዳግም 3:23-29ን አንብብ።

    ሙሴና አሮን ወደ ተስፋይቱ ምድር እንዲሻገሩ ይሖዋ ያልፈቀደላቸው ለምንድን ነው? እኛስ ከዚህ ምን ትምህርት እናገኛለን? (ዘዳ. 3:25-27፤ ዘኍ. 20:12, 13)

  3. ዘዳግም 31:1-8, 14-23ን አንብብ።

    ሙሴ ለእስራኤላውያን የተናገራቸው የመሰነባበቻ ቃላት የይሖዋን ተግሣጽ በትሕትና እንደተቀበለ የሚያሳዩት እንዴት ነው? (ዘዳ. 31:6-8, 23)

  4. ዘዳግም 32:45-52ን አንብብ።

    የአምላክ ቃል በሕይወታችን ውስጥ ምን ተጽዕኖ ሊያሳድር ይገባል? (ዘዳ. 32:47፤ ዘሌ. 18:5፤ ዕብ. 4:12)

  5. ዘዳግም 34:1-12ን አንብብ።

    ሙሴ ቃል በቃል ይሖዋን አይቶት ባያውቅም ዘዳግም 34:10 ከይሖዋ ጋር ስለነበረው ዝምድና ምን ያመለክታል? (ዘፀ. 33:11, 20፤ ዘኍ. 12:8)

ታሪክ 44

ረዓብ ሰላዮቹን ደበቀች

  1. ረዓብ የምትኖረው የት ነበር?

  2. በሥዕሉ ላይ የምታያቸው ሁለት ሰዎች እነማን ናቸው? ወደ ኢያሪኮ የሄዱትስ ለምንድን ነው?

  3. የኢያሪኮ ንጉሥ ረዓብን ምን እንድታደርግ አዘዛት? እርሷስ ምን መልስ ሰጠች?

  4. ረዓብ ሁለቱን ሰዎች የረዳቻቸው እንዴት ነው? ምን ውለታ እንዲውሉላት ጠየቀቻቸው?

  5. ሁለቱ ሰላዮች ለረዓብ ምን ቃል ገቡላት?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ኢያሱ 2:1-24ን አንብብ።

    በ⁠ዘፀአት 23:28 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘው ይሖዋ የገባው ቃል እስራኤላውያን ኢያሪኮን ለመውጋት በወጡ ጊዜ ፍጻሜ ያገኘው አንዴት ነው? (ኢያሱ 2:9-11)

  2. ዕብራውያን 11:31ን አንብብ።

    የረዓብ ምሳሌ የእምነትን አስፈላጊነት የሚያጎላው እንዴት ነው? (ሮሜ 1:17፤ ዕብ. 10:39፤ ያዕ. 2:25)

ታሪክ 45

የዮርዳኖስን ወንዝ መሻገር

  1. እስራኤላውያን የዮርዳኖስን ወንዝ እንዲሻገሩ ይሖዋ ምን ተአምር ፈጸመ?

  2. እስራኤላውያን የዮርዳኖስን ወንዝ ለመሻገር እንዲችሉ በእምነት ምን እርምጃ መውሰድ ነበረባቸው?

  3. ይሖዋ፣ ኢያሱ ከወንዙ ውስጥ 12 ድንጋዮችን እንዲሰበስብ ያዘዘው ለምን ነበር?

  4. ካህናቱ ከዮርዳኖስ ወንዝ እንደወጡ ምን ተፈጸመ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ኢያሱ 3:1-17ን አንብብ።

    1. (ሀ) ይህ ታሪክ እንደሚያሳየው እኛም የይሖዋን እርዳታና በረከት ለማግኘት እንድንችል ምን ማድረግ ያስፈልገናል? (ኢያሱ 3:13, 15፤ ምሳሌ 3:5፤ ያዕ. 2:22, 26)

    2. (ለ) እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን ሲሻገሩ ወንዙ ምን ያህል ሞልቶ ነበር? ይህስ የይሖዋን ስም ከፍ ከፍ ያደረገው እንዴት ነበር? (ኢያሱ 3:15፤ 4:18፤ መዝ. 66:5-7)

  2. ኢያሱ 4:1-18ን አንብብ

    ከዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ የተወሰዱት 12 ድንጋዮች በጌልገላ የተቀመጡበት ዓላማ ምን ነበር? (ኢያሱ 4:4-7)

ታሪክ 46

የኢያሪኮ ግንብ

  1. ይሖዋ፣ ተዋጊዎቹና ካህናቱ ለስድስት ቀናት ምን እንዲያደርጉ አዘዛቸው?

  2. ሰዎቹ በሰባተኛው ቀን ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል?

  3. በሥዕሉ ላይ እንደምታየው የኢያሪኮ ግንብ ምን እየሆነ ነው?

  4. በመስኮቱ ላይ ቀይ ገመድ የተንጠለጠለው ለምንድን ነው?

  5. ኢያሱ፣ ተዋጊዎቹ የኢያሪኮን ሕዝብና ከተማይቷን ምን እንዲያደርጉ አዘዛቸው? ብሩን፣ ወርቁን፣ ነሐሱንና ብረቱን ግን ምን አድርጉት አላቸው?

  6. ሁለቱ ሰላዮች ምን እንዲያደርጉ ተነገራቸው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ኢያሱ 6:1-25ን አንብብ።

    1. (ሀ) እስራኤላውያን በሰባተኛው ቀን በኢያሪኮ ዙሪያ ያደረጉት የሰልፍ ጉዞ የይሖዋ ምሥክሮች በዚህ የመጨረሻ ዘመን ከሚያከናውኑት የስብከት እንቅስቃሴ ጋር የሚመሳሰለው እንዴት ነው? (ኢያሱ 6:15, 16፤ ኢሳ. 60:22፤ ማቴ. 24:14፤ 1 ቆሮ. 9:16)

    2. (ለ) በኢያሱ 6:26 ላይ የተመዘገበው ትንቢት ከ500 ዓመታት በኋላ የተፈጸመው እንዴት ነው? ይህስ የአምላክን ቃል በተመለከተ ምን ያስተምረናል? (1 ነገ. 16:34፤ ኢሳ. 55:11)

ታሪክ 47

በእስራኤል የነበረ ሌባ

  1. በሥዕሉ ላይ ከኢያሪኮ የወሰደውን ሀብት ሲቀብር የሚታየው ሰው ማን ነው? እየረዱት ያሉትስ እነማን ናቸው?

  2. የአካንና የቤተሰቡ ድርጊት ያን ያህል ከባድ የሆነው ለምንድን ነው?

  3. ኢያሱ፣ እስራኤላውያን በጋይ በተደረገው ጦርነት የተሸነፉት ለምን እንደሆነ በጠየቀ ጊዜ ይሖዋ ምን መልስ ሰጠው?

  4. አካንና ቤተሰቡ ወደ ኢያሱ ከቀረቡ በኋላ ምን ተደረጉ?

  5. በአካን ላይ የተላለፈው ፍርድ ለእኛ ምን ጠቃሚ ትምህርት ይሰጠናል?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ኢያሱ 7:1-26ን አንብብ።

    1. (ሀ) ኢያሱ ያቀረበው ጸሎት ከፈጣሪው ጋር ስለነበረው ዝምድና ምን ያሳያል? (ኢያሱ 7:7-9፤ መዝ. 119:145፤ 1 ዮሐ. 5:14)

    2. (ለ) የአካን ምሳሌ ምን ያሳያል? ይህስ ለእኛ ማስጠንቀቂያ የሚሆነን እንዴት ነው? (ኢያሱ 7:11, 14, 15፤ ምሳሌ 15:3፤ 1 ጢሞ. 5:24፤ ዕብ. 4:13)

  2. ኢያሱ 8:1-29ን አንብብ።

    በዛሬው ጊዜ ባለው የክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ በግለሰብ ደረጃ ምን ኃላፊነት አለብን? (ኢያሱ 7:13፤ ዘሌ. 5:1፤ ምሳሌ 28:13)

ታሪክ 48

ጥበበኞቹ ገባዖናውያን

  1. የገባዖን ሰዎች በአካባቢው በነበሩት ከተሞች ከሚኖሩት ከነዓናውያን የተለዩ የነበሩት እንዴት ነው?

  2. በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው ገባዖናውያን ምን አደረጉ? ለምንስ?

  3. ኢያሱና የእስራኤላውያን መሪዎች ለገባዖናውያን ምን ብለው ቃል ገቡላቸው? ከሦስት ቀናት በኋላ ግን ምን ምስጢር አወቁ?

  4. በሌሎች ከተሞች የነበሩ ነገሥታት ገባዖናውያን ከእስራኤል ጋር ዕርቅ መፍጠራቸውን ሲሰሙ ምን አደረጉ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ኢያሱ 9:1-27ን አንብብ።

    1. (ሀ) ይሖዋ “[በምድሪቱ] የሚኖሩትን ሁሉ” እንዲያጠፉ እስራኤላውያንን ያዘዛቸው ቢሆንም ገባዖናውያንን ማዳኑ የትኞቹ ባሕርያቱ ጎልተው እንዲታዩ አድርጓል? (ኢያሱ 9:22, 24 የ1954 ትርጉም፤ ማቴ. 9:13፤ ሥራ 10:34, 35፤ 2 ጴጥ. 3:9)

    2. (ለ) ኢያሱ ከገባዖናውያን ጋር የገባውን ቃል በመጠበቁ በዛሬው ጊዜ ላሉት ክርስቲያኖች ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው እንዴት ነው? (ኢያሱ 9:18, 19፤ ማቴ. 5:37፤ ኤፌ. 4:25)

  2. ኢያሱ 10:1-5ን አንብብ።

    በዛሬው ጊዜ ያለው እጅግ ብዙ ሕዝብ ገባዖናውያንን የሚመስለው እንዴት ነው? በዚህስ ምክንያት የምን ዒላማ ይሆናል? (ኢያሱ 10:4፤ ዘካ. 8:23፤ ማቴ. 25:35-40፤ ራእይ 12:17)

ታሪክ 49

ፀሐይ ባለችበት ቦታ ቆመች

  1. በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው ኢየሱ ምን እያለ ነው? ለምንስ?

  2. ይሖዋ ኢያሱንና ተዋጊዎቹን የረዳቸው እንዴት ነው?

  3. ኢያሱ ድል ያደረጋቸው የጠላት ነገሥታት ስንት ናቸው? ይህን ለማድረግ ምን ያህል ጊዜ ወሰደበት?

  4. ኢያሱ የከነዓንን ምድር የከፋፈለው ለምንድን ነው?

  5. ኢያሱ ሲሞት ዕድሜው ስንት ነበር? ሕዝቡስ ከዚያ በኋላ ምን ሆኑ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ኢያሱ 10:6-15ን አንብብ።

    ይሖዋ ለእስራኤላውያን ፀሐይንና ጨረቃን ባሉበት ቦታ እንዲቆሙ እንዳደረገላቸው ማወቃችን በዛሬው ጊዜ ምን የመተማመን ስሜት ያሳድርብናል? (ኢያሱ 10:8, 10, 12, 13፤ መዝ. 18:3፤ ምሳሌ 18:10)

  2. ኢያሱ 12:7-24ን አንብብ።

    በከነዓን የነበሩት 31 ነገሥታት እንዲሸነፉ ያደረገው ማን ነው? ይህን ማወቃችንስ በዚህ ዘመን የምንኖረውን የአምላክ አገልጋዮች የሚጠቅመን እንዴት ነው? (ኢያሱ 12:7፤ 24:11-13፤ ዘዳ. 31:8፤ ሉቃስ 21:9, 25-28)

  3. ኢያሱ 14:1-5ን አንብብ።

    ምድሪቱ ለእስራኤላውያን ነገዶች የተከፋፈለችው እንዴት ነው? ይህስ በገነት ውስጥ ስለሚኖረው ርስት ምን ያመለክታል? (ኢያሱ 14:2፤ ኢሳ. 65:21፤ ሕዝ. 47:21-23፤ 1 ቆሮ. 14:33)

  4. መሳፍንት 2:8-13ን አንብብ።

    በዛሬው ጊዜ በእስራኤል እንደነበረው እንደ ኢያሱ በመሆን ክህደት እንዳይስፋፋ የሚከላከሉት እነማን ናቸው? (መሳ. 2:8, 10, 11፤ ማቴ. 24:45-47፤ 2 ተሰ. 2:3-6፤ ቲቶ 1:7-9፤ ራእይ 1:1፤ 2:1, 2)

ታሪክ 50

ሁለት ደፋር ሴቶች

  1. መሳፍንት እነማን ናቸው? የአንዳንዶቹስ ስም ማን ይባላል?

  2. ዲቦራ ምን ልዩ መብት ነበራት? ይህስ ምን ማድረግን ይጨምራል?

  3. ንጉሥ ኢያቢስና የሠራዊቱ አለቃ ሲሣራ እስራኤልን ባስጨነቋቸው ጊዜ፣ ይሖዋ በዲቦራ በኩል ለመስፍኑ ባርቅ ምን መልእክት ላከበት? ዲቦራ በድሉ ክብር የሚያገኘው ማን እንደሚሆን ተናገረች?

  4. ኢያኤል ደፋር ሴት መሆኗን ያሳየችው እንዴት ነው?

  5. ንጉሥ ኢያቢስ ከሞተ በኋላ ምን ሆነ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. መሳፍንት 2:14-22ን አንብብ።

    እስራኤላውያን ይሖዋ በእነርሱ እንዲቆጣ ያደረጉት እንዴት ነበር? እኛስ ከዚህ ምን ትምህርት እናገኛለን? (መሳ. 2:20፤ ምሳሌ 3:1, 2፤ ሕዝ. 18:21-23)

  2. መሳፍንት 4:1-24ን አንብብ።

    በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያን ሴቶች በእምነትና በድፍረት ረገድ ከዲቦራና ከኢያኤል ምሳሌነት ምን ትምህርት ያገኛሉ? (መሳ. 4:4, 8, 9, 14, 21, 22፤ ምሳሌ 31:30፤ 1 ቆሮ. 16:13)

  3. መሳፍንት 5:1-31ን አንብብ።

    ባርቅና ዲቦራ የዘመሩት የድል መዝሙር መጪውን የአርማጌዶን ጦርነት በሚመለከት እንደ ጸሎት ሆኖ ሊያገለግል የሚችለው እንዴት ነው? (መሳ. 5:3, 31፤ 1 ዜና 16:8-10፤ ራእይ 7:9, 10፤ 16:16፤ 19:19-21)

ታሪክ 51

ሩትና ናዖሚ

  1. ናዖሚ ወደ ሞዓብ ምድር የሄደችው ለምንድን ነው?

  2. ሩትና ዖርፋ እነማን ናቸው?

  3. ናዖሚ፣ ሩትና ዖርፋ ወደ ሕዝባቸው እንዲመለሱ ስትነግራቸው ምን ምላሽ ሰጧት?

  4. ቦዔዝ ማን ነው? ሩትንና ናዖሚን የረዳቸውስ እንዴት ነው?

  5. የቦዔዝና የሩት ልጅ ስም ማን ነው? ይህንን ልጅ ልናስታውሰው የሚገባን ለምንድን ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ሩት 1:1-17ን አንብብ።

    1. (ሀ) ሩት ለናዖሚ ያላትን ፍቅርና ታማኝነት ደስ በሚል አነጋገር የገለጸችው እንዴት ነው? (ሩት 1:16, 17)

    2. (ለ) የሩት አመለካከት “ሌሎች በጎች” በምድር ላይ ላሉት ቅቡዓን ክርስቲያኖች ያላቸውን አመለካከት ጥሩ አድርጎ የሚገልጸው እንዴት ነው? (ዮሐ. 10:16፤ ዘካ. 8:23)

  2. ሩት 2:1-23ን አንብብ።

    ሩት በዛሬው ጊዜ ላሉት ወጣት ሴቶች ግሩም ምሳሌ የምትሆነው እንዴት ነው? (ሩት 2:17, 18፤ ምሳሌ 23:22፤ 31:15)

  3. ሩት 3:5-13ን አንብብ።

    1. (ሀ) ቦዔዝ፣ ሩት ወጣት ወንድ በማግባት ፈንታ እሱን ለማግባት ፈቃደኛ በመሆኗ ምን ተሰማው?

    2. (ለ) ሩት የነበራት ዝንባሌ ስለ ጽኑ ፍቅር ምን ያስተምረናል? (ሩት 3:10፤ 1 ቆሮ. 13:4, 5)

  4. ሩት 4:7-17ን አንብብ።

    በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያን ወንዶች እንደ ቦዔዝ መሆን የሚችሉት እንዴት ነው? (ሩት 4:9, 10፤ 1 ጢሞ. 3:1, 12, 13፤ 5:8)

ታሪክ 52

ጌዴዎንና 300 ተዋጊዎቹ

  1. እስራኤላውያን ብዙ መከራ ያጋጠማቸው ለምንና እንዴት ነበር?

  2. ይሖዋ ለጌዴዎን በሠራዊቱ ውስጥ ያሉት ሰዎች በጣም ብዙ እንደሆኑ የነገረው ለምንድን ነው?

  3. ጌዴዎን የፈሩት ሰዎች ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ከተናገረ በኋላ ስንት ሰዎች ቀሩ?

  4. ሥዕሉን በመመልከት ይሖዋ የጌዴዎንን ሠራዊት ወደ 300 የቀነሰው እንዴት እንደሆነ ግለጽ።

  5. ጌዴዎን 300 ተዋጊዎቹን ያደራጀው እንዴት ነው? እስራኤላውያንስ በውጊያው ያሸነፉት እንዴት ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. መሳፍንት 6:36-40ን አንብብ።

    1. (ሀ) ጌዴዎን የይሖዋን ፈቃድ በእርግጠኝነት ለማወቅ ጥረት ያደረገው እንዴት ነው?

    2. (ለ) ዛሬስ የይሖዋ ፈቃድ ምን እንደሆነ ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው? (ምሳሌ 2:3-6፤ ማቴ. 7:7-11፤ 2 ጢሞ. 3:16, 17)

  2. መሳፍንት 7:1-25ን አንብብ።

    1. (ሀ) ግዴለሽነት ካሳዩት ሰዎች በተቃራኒ ንቁ ከነበሩት 300 ሰዎች ምን ትምህርት እናገኛለን? (መሳ. 7:3, 6፤ ሮሜ 13:11, 12፤ ኤፌ. 5:15-17)

    2. (ለ) ሦስት መቶዎቹ ተዋጊዎች ጌዴዎንን በመመልከት ትምህርት እንዳገኙ ሁሉ እኛም ታላቁን ጌዴዎን፣ ኢየሱስ ክርስቶስን በመመልከት ምን እንማራለን? (መሳ. 7:17፤ ማቴ. 11:29, 30፤ 28:19, 20፤ 1 ጴጥ. 2:21)

    3. (ሐ) መሳፍንት 7:21 በይሖዋ ድርጅት ውስጥ በተመደብንበት በማንኛውም ቦታ ደስ ብሎን እንድናገለግል የሚረዳን እንዴት ነው? (1 ቆሮ. 4:2፤ 12:14-18፤ ያዕ. 4:10)

  3. መሳፍንት 8:1-3ን አንብብ።

    ከአንድ ወንድም ወይም ከአንዲት እህት ጋር የተፈጠረን አለመግባባት መፍታትን በተመለከተ ጌዴዎን ከኤፍሬማውያን ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት ከፈታበት መንገድ ምን ልንማር እንችላለን? (ምሳሌ 15:1፤ ማቴ. 5:23, 24፤ ሉቃስ 9:48)

ታሪክ 53

ዮፍታሔ የገባው ቃል

  1. ዮፍታሔ ማን ነው? የኖረውስ በምን ዓይነት ዘመን ነበር?

  2. ዮፍታሔ ለይሖዋ ምን በማለት ቃል ገባ?

  3. ዮፍታሔ አሞናውያንን ድል አድርጎ ወደ ቤቱ ሲመለስ ያዘነው ለምን ነበር?

  4. የዮፍታሔ ልጅ አባቷ ስለገባው ቃል ስትሰማ ምን አለች?

  5. ሕዝቡ የዮፍታሔን ልጅ የሚወዷት ለምን ነበር?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. መሳፍንት 10:6-18ን አንብብ።

    እስራኤላውያን ለይሖዋ ታማኝ ስላለመሆናቸው ከሚገልጸው ታሪክ ምን የማስጠንቀቂያ ትምህርት እናገኛለን? (መሳ. 10:6, 15, 16፤ ሮሜ 15:4፤ ራእይ 2:10)

  2. መሳፍንት 11:1-11, 29-40ን አንብብ።

    1. (ሀ) ዮፍታሔ ሴት ልጁን “የሚቃጠል መሥዋዕት” አድርጎ ሰጥቷል ሲባል በእሳት አቃጥሎ መሥዋዕት አድርጓታል ማለት እንዳልሆነ እንዴት እናውቃለን? (መሳ. 11:31፤ ዘሌ. 16:24፤ ዘዳ. 18:10, 12)

    2. (ለ) ታዲያ ዮፍታሔ ሴት ልጁን መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው እንዴት ነው?

    3. (ሐ) ዮፍታሔ ለይሖዋ የተሳለውን ስእለት አስመልክቶ ከነበረው አመለካከት ምን ልንማር እንችላለን? (መሳ. 11:35, 39፤ መክ. 5:4, 5፤ ማቴ. 16:24)

    4. (መ) የዮፍታሔ ልጅ በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ላይ በመሠማራት ረገድ ለወጣት ክርስቲያኖች ግሩም ምሳሌ የምትሆነው እንዴት ነው? (መሳ. 11:36፤ ማቴ. 6:33፤ ፊልጵ. 3:8)

ታሪክ 54

ኃይለኛው ሰው

  1. በምድር ላይ ከኖሩት ሰዎች ሁሉ ኃይለኛ የነበረው ሰው ማን ይባላል? ኃይል የሰጠውስ ማን ነው?

  2. በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው ሳምሶን በአንድ ወቅት ያገኘውን ትልቅ አንበሳ ምን አደረገው?

  3. በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው ሳምሶን ለደሊላ ምን ምስጢር እየነገራት ነው? ይህስ በፍልስጥኤማውያን ለመያዝ ያበቃው እንዴት ነው?

  4. ሳምሶን በሞተበት ዕለት ጠላቶቹ የሆኑ 3,000 ፍልስጥኤማውያንን መግደል የቻለው እንዴት ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. መሳፍንት 13:1-14ን አንብብ።

    ማኑሄና ሚስቱ ልጆችን በማሳደግ ረገድ ለወላጆች ጥሩ ምሳሌ የሚሆኑት እንዴት ነው? (መሳ. 13:8፤ መዝ. 127:3፤ ኤፌ. 6:4)

  2. መሳፍንት 14:5-9ን እና 15:9-16ን አንብብ።

    1. (ሀ) ሳምሶን አንበሳ ስለ መግደሉ፣ የታሰረባቸውን አዳዲስ ገመዶች ስለ መበጣጠሱና በአህያ መንጋጋ 1,000 ሰዎች ስለ መግደሉ የሚገልጸው ዘገባ የይሖዋን ቅዱስ መንፈስ አሠራር በተመለከተ ምን ያስተምረናል?

    2. (ለ) በዛሬው ጊዜስ መንፈስ ቅዱስ እኛንም የሚረዳን እንዴት ነው? (መሳ. 14:6፤ 15:14፤ ዘካ. 4:6፤ ሥራ 4:31)

  3. መሳፍንት 16:18-31ን አንብብ።

    ሳምሶን በመጥፎ ጓደኝነት የተጎዳው እንዴት ነው? እኛስ ከዚህ ምን እንማራለን? (መሳ. 16:18, 19፤ 1 ቆሮ. 15:33)

ታሪክ 55

አምላክን ያገለገለ አንድ ትንሽ ልጅ

  1. በሥዕሉ ላይ የሚታየው ትንሽ ልጅ ማን ነው? ሌሎቹስ እነማን ናቸው?

  2. ሐና አንድ ቀን ወደ ይሖዋ መገናኛ ድንኳን ሄዳ ምን ብላ ጸለየች? ይሖዋስ መልስ የሰጣት እንዴት ነው?

  3. ሳሙኤል በይሖዋ ድንኳን እንዲያገለግል ሲወሰድ ዕድሜው ስንት ነበር? እናቱስ በየዓመቱ ምን ታደርግለት ነበር?

  4. የዔሊ ልጆች ስም ማን ይባላል? ምን ዓይነት ሰዎችስ ነበሩ?

  5. ይሖዋ ሳሙኤልን የጠራው እንዴት ነበር? ምን መልእክትስ ነገረው?

  6. ሳሙኤል አድጎ ትልቅ ሰው ሲሆን ምን ሆነ? ሲያረጅስ ምን ነገር ተፈጸመ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. አንደኛ ሳሙኤል 1:1-28ን አንብብ።

    1. (ሀ) ሕልቃና በእውነተኛው አምልኮ ቤተሰቡን በመምራት ረገድ ለቤተሰብ ራሶች ግሩም ምሳሌ የሚሆናቸው እንዴት ነው? (1 ሳሙ. 1:3, 21፤ ማቴ. 6:33፤ ፊልጵ. 1:10)

    2. (ለ) ሐና አስቸጋሪ ሁኔታ ሲያጋጥማት ከወሰደችው እርምጃ ምን ትምህርት ልናገኝ እንችላለን? (1 ሳሙ. 1:10, 11፤ መዝ. 55:22፤ ሮሜ 12:12)

  2. አንደኛ ሳሙኤል 2:11-36ን አንብብ።

    ዔሊ ከይሖዋ ይበልጥ ልጆቹን ያከበረው እንዴት ነው? ይህስ ለእኛ ማስጠንቀቂያ ሆኖ የሚያገለግለው እንዴት ነው? (1 ሳሙ. 2:22-24, 27, 29፤ ዘዳ. 21:18-21፤ ማቴ. 10:36, 37)

  3. አንደኛ ሳሙኤል 4:16-18ን አንብብ።

    ከጦር ሜዳ ምን የሚል ተደራራቢ መርዶ መጣ? ይህስ በዔሊ ላይ ምን ውጤት አስከተለ?

  4. አንደኛ ሳሙኤል 8:4-9ን አንብብ።

    እስራኤላውያን ይሖዋን በጣም ያሳዘኑት እንዴት ነው? እኛስ ዛሬ መንግሥቱን በታማኝነት መደገፍ የምንችለው እንዴት ነው? (1 ሳሙ. 8:5, 7፤ ዮሐ. 17:16፤ ያዕ. 4:4)

ታሪክ 56

የመጀመሪያው የእስራኤል ንጉሥ የሆነው ሳኦል

  1. በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው ሳሙኤል ምን እያደረገ ነው? ለምንስ?

  2. ይሖዋ ሳኦልን የወደደው ለምን ነበር? ሳኦል ምን ዓይነት ሰው ነበር?

  3. የሳኦል ልጅ ማን ይባላል? እሱስ ምን አድርጓል?

  4. ሳኦል ሳሙኤልን መጠበቅ ሲገባው እርሱ ራሱ መሥዋዕት ያቀረበው ለምን ነበር?

  5. ስለ ሳኦል ከቀረበው ታሪክ ምን ትምህርት እናገኛለን?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. አንደኛ ሳሙኤል 9:15-21ን እና 10:17-27ን አንብብ።

    ሳኦል ትሑት መሆኑ አንዳንድ ሰዎች ስለ እርሱ በንቀት በተናገሩ ጊዜ በችኮላ እርምጃ ከመውሰድ እንዲቆጠብ የረዳው እንዴት ነው? (1 ሳሙ. 9:21፤ 10:21, 22, 27፤ ምሳሌ 17:27)

  2. አንደኛ ሳሙኤል 13:5-14ን አንብብ።

    ሳኦል በጌልገላ የፈጸመው ኃጢአት ምን ነበር? (1 ሳሙ. 10:8፤ 13:8, 9, 13)

  3. አንደኛ ሳሙኤል 15:1-35ን አንብብ።

    1. (ሀ) ሳኦል ከአማሌቃውያን ንጉሥ ከአጋግ ጋር በተያያዘ ምን ከባድ ኃጢአት ሠርቷል? (1 ሳሙ. 15:2, 3, 8, 9, 22)

    2. (ለ) ሳኦል ድርጊቱን ትክክል ለማስመሰልና ጥፋቱን በሌሎች ላይ ለማላከክ የሞከረው እንዴት ነው? (1 ሳሙ. 15:24)

    3. (ሐ) በዛሬው ጊዜ ምክር ሲሰጠን የትኛውን ማስጠንቀቂያ ልብ ማለት ይገባናል? (1 ሳሙ. 15:19-21፤ መዝ. 141:5፤ ምሳሌ 9:8, 9፤ 11:2)

ታሪክ 57

አምላክ ዳዊትን መረጠው

  1. በሥዕሉ ላይ የሚታየው ልጅ ስሙ ማን ነው? ደፋር መሆኑንስ እንዴት እናውቃለን?

  2. ዳዊት የሚኖረው የት ነው? አባቱና አያቱ ማን ይባላሉ?

  3. ይሖዋ ሳሙኤልን በቤተ ልሔም ወደሚገኘው ወደ እሴይ ቤት እንዲሄድ የነገረው ለምን ነበር?

  4. እሴይ ሰባቱን ልጆቹን ወደ ሳሙኤል ባመጣቸው ጊዜ ምን ሁኔታ ተከሰተ?

  5. ዳዊት ሲመጣ ይሖዋ ለሳሙኤል ምን ነገረው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. አንደኛ ሳሙኤል 17:34, 35ን አንብብ።

    እነዚህ ሁኔታዎች ዳዊት ደፋርና በይሖዋ የሚተማመን ልጅ መሆኑን ጎላ አድርገው የሚገልጹት እንዴት ነው? (1 ሳሙ. 17:37)

  2. አንደኛ ሳሙኤል 16:1-14ን አንብብ።

    1. (ሀ) በ⁠1 ሳሙኤል 16:7 ላይ የሚገኙት ይሖዋ የተናገራቸው ቃላት የማናዳላ እንድንሆንና በውጫዊ መልክ እንዳንታለል የሚረዱን እንዴት ነው? (ሥራ 10:34, 35፤ 1 ጢሞ. 2:4)

    2. (ለ) በሳኦል ላይ የደረሰው ሁኔታ ይሖዋ ከአንድ ሰው ላይ መንፈሱን ሲያነሳ በምትኩ ክፉ መንፈስ እንደሚገባ ወይም ግለሰቡ መጥፎ ነገር የመሥራት ከፍተኛ ፍላጎት እንደሚያድርበት የሚያሳየው እንዴት ነው? (1 ሳሙ. 16:14፤ ማቴ. 12:43-45፤ ገላ. 5:16)

ታሪክ 58

ዳዊትና ጎልያድ

  1. ጎልያድ የእስራኤልን ሠራዊት የተፈታተነው እንዴት ነው?

  2. ጎልያድ ምን ያህል ግዙፍ ነው? ንጉሥ ሳኦል ጎልያድን ለሚገድል ሰው ምን ሽልማት እንደሚሰጥ ቃል ገባ?

  3. ዳዊት ገና ትንሽ ልጅ ስለሆነ ጎልያድን ውጊያ ሊገጥመው እንደማይችል ሳኦል ሲነግረው ምን አለ?

  4. ዳዊት ለጎልያድ የሰጠው መልስ በይሖዋ እንደሚተማመን የሚያሳየው እንዴት ነው?

  5. በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው ዳዊት ጎልያድን የገደለው በምንድን ነው? ከዚህ በኋላ ፍልስጥኤማውያን ምን አደረጉ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. አንደኛ ሳሙኤል 17:1-54ን አንብብ።

    1. (ሀ) ዳዊት እንዳይፈራ ያደረገው ነገር ምንድን ነው? ድፍረቱን ልንኮርጅ የምንችለውስ እንዴት ነው? (1 ሳሙ. 17:37, 45፤ ኤፌ. 6:10, 11)

    2. (ለ) ክርስቲያኖች ሲጫወቱም ሆነ ሲዝናኑ ጎልያድ ካሳየው ዓይነት የፉክክር መንፈስ መራቅ የሚኖርባቸው ለምንድን ነው? (1 ሳሙ. 17:8፤ ገላ. 5:26፤ 1 ጢሞ. 4:8)

    3. (ሐ) ዳዊት የተናገራቸው ቃላት በአምላክ ኃይል ላይ እምነት እንዳለው የሚያሳዩት እንዴት ነው? (1 ሳሙ. 17:45-47፤ 2 ዜና 20:15)

    4. (መ) ይህ ታሪክ ውጊያ የተካሄደው በሁለት ሠራዊት መካከል ብቻ ሳይሆን እውነተኛ አምላክ በሆነው በይሖዋና በሐሰት አማልክት መካከል እንደሆነ የሚያሳየው እንዴት ነው? (1 ሳሙ. 17:43, 46, 47)

    5. (ሠ) ቅቡዓን ቀሪዎች በይሖዋ በመታመን ረገድ የዳዊትን ምሳሌ የሚከተሉት እንዴት ነው? (1 ሳሙ. 17:37፤ ኤር. 1:17-19፤ ራእይ 12:17)

ታሪክ 59

ዳዊት መሸሽ የነበረበት ለምንድን ነው?

  1. ሳኦል በዳዊት ላይ ቅናት ያደረበት ለምንድን ነው? ይሁን እንጂ የሳኦል ልጅ ዮናታን የተለየ የሆነው እንዴት ነው?

  2. አንድ ቀን ዳዊት ለሳኦል በገና ሲጫወትለት ምን አጋጠመው?

  3. ሳኦል ልጁን ሜልኮልን ለዳዊት ከመዳሩ በፊት ዳዊት ምን ማድረግ እንዳለበት ተናገረ? ሳኦል ይህን ያለው ለምንድን ነው?

  4. ሥዕሉ እንደሚያሳየው ዳዊት ለሳኦል በገና እየተጫወተለት ሳለ ለሦስተኛ ጊዜ ምን ተከሰተ?

  5. ሜልኮል ዳዊትን ከሞት ያዳነችው እንዴት ነው? ከዚያ በኋላ ዳዊት ለሰባት ዓመታት ያህል ምን ማድረግ ግድ ሆኖበት ነበር?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. አንደኛ ሳሙኤል 18:1-30ን አንብብ።

    1. (ሀ) ዮናታን ለዳዊት የነበረው ፈጽሞ የማይቀዘቅዝ ፍቅር ‘በሌሎች በጎችና’ ‘በታናሹ መንጋ’ መካከል ያለውን ፍቅር የሚያሳየው እንዴት ነው? (1 ሳሙ. 18:1፤ ዮሐ. 10:16፤ ሉቃስ 12:32፤ ዘካ. 8:23)

    2. (ለ) ዮናታን የሳኦል ወራሽ የመሆን መብት የነበረው ቢሆንም 1 ሳሙኤል 18:4 ዮናታን ንጉሥ እንዲሆን ለታጨው ሰው ከፍተኛ የታዛዥነት መንፈስ እንዳሳየ የሚያሳየው እንዴት ነው?

    3. (ሐ) የሳኦል ታሪክ ቅናት ከባድ ኃጢአት ወደ መፈጸም ሊያመራ እንደሚችል የሚያሳየው እንዴት ነው? ይህስ ለእኛ ምን የማስጠንቀቂያ ትምህርት ይዞልናል? (1 ሳሙ. 18:7-9, 25፤ ያዕ. 3:14-16)

  2. አንደኛ ሳሙኤል 19:1-17ን አንብብ።

    ዮናታን ዳዊትን በሚመለከት ከሳኦል ጋር በተነጋገረ ጊዜ የራሱን ሕይወት አደጋ ላይ የጣለው እንዴት ነው? (1 ሳሙ. 19:1, 4-6፤ ምሳሌ 16:14)

ታሪክ 60

አቢግያና ዳዊት

  1. በሥዕሉ ላይ ወደ ዳዊት ስትመጣ የምትታየው ሴት ስሟ ማን ነው? ምን ዓይነት ባሕርይስ ነበራት?

  2. ናባል ማን ነው?

  3. ዳዊት መልእክተኞቹን ወደ ናባል የላከው ለምን ነበር?

  4. ናባል የዳዊትን መልእክተኞች ምን አላቸው? ዳዊትስ ምን ምላሽ ሰጠ?

  5. አቢግያ አስተዋይ ሴት መሆኗን ያሳየችው እንዴት ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. አንደኛ ሳሙኤል 22:1-4ን አንብብ።

    የዳዊት ቤተሰብ በክርስቲያናዊ ወንድማማችነት እርስ በርስ መደጋገፍ እንደሚኖርብን የሚያሳይ ጥሩ ምሳሌ የተወልን እንዴት ነው? (ምሳሌ 17:17፤ 1 ተሰ. 5:14)

  2. አንደኛ ሳሙኤል 25:1-43ን አንብብ።

    1. (ሀ) ናባል ሌሎችን በጣም የሚንቅ ሰው እንደሆነ የተገለጸው ለምንድን ነው? (1 ሳሙ. 25:2-5, 10, 14, 21, 25)

    2. (ለ) በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያን ሚስቶች ከአቢግያ ምን ሊማሩ ይችላሉ? (1 ሳሙ. 25:32, 33፤ ምሳሌ 31:26፤ ኤፌ. 5:24)

    3. (ሐ) አቢግያ፣ ዳዊት ምን ሁለት ክፉ ነገሮችን እንዳያደርግ ረድታዋለች? (1 ሳሙ. 25:31, 33፤ ሮሜ 12:19፤ ኤፌ. 4:26)

    4. (መ) ዳዊት አቢግያ ለነገረችው ቃል የሰጠው ምላሽ፣ በዛሬው ጊዜ ያሉ ወንዶች ይሖዋ ለሴቶች ያለው አመለካከት እንዲኖራቸው የሚረዳቸው እንዴት ነው? (ሥራ 21:8, 9፤ ሮሜ 2:11፤ 1 ጴጥ. 3:7)

ታሪክ 61

ዳዊት ነገሠ

  1. ሳኦል በሰፈሩ ውስጥ ተኝቶ ሳለ ዳዊትና አቢሳ ምን አደረጉ?

  2. ዳዊት ሳኦልን ምን ብሎ ጠየቀው?

  3. ዳዊት ከሳኦል ጋር ከተነጋገረ በኋላ ወዴት ሄደ?

  4. ዳዊት በጣም ግሩም መዝሙር የጻፈው ምን አሳዛኝ ነገር ስላጋጠመው ነው?

  5. ዳዊት በኬብሮን በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ስንት ነበር? ከልጆቹ መካከል አንዳንዶቹ ማን ይባላሉ?

  6. ዳዊት ከጊዜ በኋላ ንጉሥ ሆኖ የገዛው የት ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. አንደኛ ሳሙኤል 26:1-25ን አንብብ።

    1. (ሀ) በ⁠1 ሳሙኤል 26:11 ላይ የተመዘገቡት ቃላት እንደሚያሳዩት ዳዊት ለቲኦክራሲያዊ ሥርዓት ምን አመለካከት ነበረው? (መዝ. 37:7፤ ሮሜ 13:2)

    2. (ለ) ለሌሎች ፍቅራዊ ደግነት ለማሳየት ልባዊ ጥረት አድርገን በምላሹ ተቃራኒ ነገር ሲገጥመን ዳዊት በ1 ሳሙኤል 26:23 ላይ የተናገራቸው ቃላት ተገቢ አመለካከት እንዲኖረን የሚረዱን እንዴት ነው? (1 ነገ. 8:32፤ መዝ. 18:20)

  2. ሁለተኛ ሳሙኤል 1:26ን አንብብ።

    በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያኖች እንደ ዳዊትና ዮናታን ‘እርስ በርስ ከልብ መዋደድ’ የሚችሉት እንዴት ነው? (1 ጴጥ. 4:8፤ ቈላ. 3:14፤ 1 ዮሐ. 4:12)

  3. ሁለተኛ ሳሙኤል 5:1-10ን አንብብ።

    1. (ሀ) ዳዊት ንጉሥ ሆኖ የገዛው ለስንት ዓመት ነው? ይህ ጊዜስ የሚከፋፈለው እንዴት ነው? (2 ሳሙ. 5:4, 5)

    2. (ለ) ዳዊት ብርቱ ወይም ታላቅ ሊሆን የቻለው እንዴት ነው? ይህስ በዛሬው ጊዜ ለምንኖረው ምን ያስገነዝበናል? (2 ሳሙ. 5:10፤ 1 ሳሙ. 16:13፤ 1 ቆሮ. 1:31፤ ፊልጵ. 4:13)

ታሪክ 62

በዳዊት ቤት ውስጥ ችግር ተፈጠረ

  1. ይሖዋ የከነዓንን ምድር ለእነማን ሰጠ?

  2. አንድ ቀን ምሽት ዳዊት በቤቱ ሰገነት ላይ ሳለ ምን ተከሰተ?

  3. ይሖዋ በዳዊት ላይ በጣም የተቆጣው ለምንድን ነው?

  4. በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው ይሖዋ ዳዊት ኃጢአት መሥራቱን እንዲነግረው ማንን ላከ? ይህ ሰው በዳዊት ላይ ምን እንደሚደርስበት ተናገረ?

  5. ዳዊት ምን ዓይነት ችግር ደረሰበት?

  6. ከዳዊት በኋላ በእስራኤል ላይ ንጉሥ የሆነው ማን ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ሁለተኛ ሳሙኤል 11:1-27ን አንብብ።

    1. (ሀ) በይሖዋ አገልግሎት መጠመዳችን ጥበቃ የሚሆንልን እንዴት ነው?

    2. (ለ) ዳዊት ኃጢአት ለመሥራት የዳረገው ምንድን ነው? ይህስ በዛሬው ጊዜ ላሉ የይሖዋ አገልጋዮች ምን ማስጠንቀቂያ ይሆናቸዋል? (2 ሳሙ. 11:2፤ ማቴ. 5:27-29፤ 1 ቆሮ. 10:12፤ ያዕ. 1:14, 15)

  2. ሁለተኛ ሳሙኤል 12:1-18ን አንብብ።

    1. (ሀ) ሽማግሌዎችና ወላጆች ናታን ለዳዊት ምክር ከሰጠበት መንገድ ምን ትምህርት ያገኛሉ? (2 ሳሙ. 12:1-4፤ ምሳሌ 12:18፤ ማቴ. 13:34)

    2. (ለ) ይሖዋ ለዳዊት ምሕረት ያደረገለት ለምንድን ነው? (2 ሳሙ. 12:13፤ መዝ. 32:5፤ 2 ቆሮ. 7:9, 10)

ታሪክ 63

ጠቢቡ ንጉሥ ሰሎሞን

  1. ይሖዋ ሰሎሞንን ምን ብሎ ጠየቀው? እሱስ ምን ብሎ መለሰ?

  2. ይሖዋ በሰሎሞን ልመና ስለተደሰተ ምን እንደሚሰጠው ቃል ገባለት?

  3. ሁለት ሴቶች ምን ከባድ ችግር ይዘው ወደ ሰሎሞን ቀረቡ?

  4. በሥዕሉ ላይ እንደምትመለከተው ሰሎሞን ችግሩን የፈታው እንዴት ነው?

  5. የሰሎሞን የግዛት ዘመን ምን ይመስል ነበር? እንዲህ የሆነውስ ለምንድን ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. አንደኛ ነገሥት 3:3-28ን አንብብ።

    1. (ሀ) በዛሬው ጊዜ በአምላክ ድርጅት ውስጥ ኃላፊነት ያላቸው ወንዶች ሰሎሞን በ⁠1 ነገሥት 3:7 ላይ ካቀረበው ልባዊ ልመና ምን ይማራሉ? (መዝ. 119:105፤ ምሳሌ 3:5, 6)

    2. (ለ) ሰሎሞን ያቀረበው ጸሎት ሊጸለይባቸው ስለሚገቡ ነገሮች ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው እንዴት ነው? (1 ነገ. 3:9, 11፤ ምሳሌ 30:8, 9፤ 1 ዮሐ. 5:14)

    3. (ሐ) ሰሎሞን በሁለቱ ሴቶች መካከል የነበረውን ክርክር የፈታበት መንገድ የታላቁ ሰሎሞን የኢየሱስ ክርስቶስን የወደፊት ግዛት በተመለከተ ምን ዓይነት የመተማመን ስሜት ያሳድርብናል? (1 ነገ. 3:28፤ ኢሳ. 9:6, 7፤ 11:2-4)

  2. አንደኛ ነገሥት 4:29-34ን አንብብ።

    1. (ሀ) ሰሎሞን ታዛዥ ልብ እንዲሰጠው ያቀረበውን ልመና ይሖዋ የመለሰለት እንዴት ነው? (1 ነገ. 4:29)

    2. (ለ) ሰዎች የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ካደረጉት ጥረት አንጻር የአምላክን ቃል ስለማጥናት ምን አመለካከት ሊኖረን ይገባል? (1 ነገ. 4:29, 34፤ ዮሐ. 17:3፤ 2 ጢሞ. 3:16)

ታሪክ 64

ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ሠራ

  1. ሰሎሞን የይሖዋን ቤተ መቅደስ ሠርቶ ለመጨረስ ምን ያህል ጊዜ ወሰደበት? ግንባታው ብዙ ገንዘብ የፈጀውስ ለምንድን ነው?

  2. ቤተ መቅደሱ ስንት ዋና ዋና ክፍሎች አሉት? በውስጠኛው ክፍል ውስጥ የተቀመጠውስ ምንድን ነው?

  3. ቤተ መቅደሱ ተሠርቶ ሲያልቅ ሰሎሞን ምን ብሎ ጸለየ?

  4. ይሖዋ በሰሎሞን ጸሎት እንደተደሰተ ያሳየው እንዴት ነው?

  5. ሰሎሞንን ሚስቶቹ ምን እንዲያደርግ ገፋፉት? ሰሎሞን ምን ደረሰበት?

  6. ይሖዋ በሰሎሞን ላይ የተቆጣው ለምን ነበር? ይሖዋ ሰሎሞንን ምን አለው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. አንደኛ ዜና መዋዕል 28:9, 10ን አንብብ።

    በ⁠1 ዜና መዋዕል 28:9, 10 ላይ ተመዝግበው ከሚገኙት የዳዊት ቃላት አንጻር በዕለታዊ ሕይወታችን ምን ለማድረግ መጣር ይኖርብናል? (መዝ. 19:14፤ ፊልጵ. 4:8, 9)

  2. ሁለተኛ ዜና መዋዕል 6:12-21, 32-42ን አንብብ።

    1. (ሀ) ሰሎሞን ሰው የሠራው ማንኛውም ሕንጻ ሉዓላዊውን አምላክ ይሖዋን ሊይዝ እንደማይችል ያመለከተው እንዴት ነው? (2 ዜና 6:18፤ ሥራ 17:24, 25)

    2. (ለ) በ⁠2 ዜና መዋዕል 6:32, 33 ላይ የሚገኙት የሰሎሞን ቃላት ስለ ይሖዋ ምን ይገልጻሉ? (ሥራ 10:34, 35፤ ገላ. 2:6)

  3. ሁለተኛ ዜና መዋዕል 7:1-5ን አንብብ።

    የእስራኤል ልጆች ክብሩን ባዩ ጊዜ ለይሖዋ ምስጋና ለማቅረብ እንደተገፋፉ ሁሉ በዛሬው ጊዜ እኛም ይሖዋ ለሕዝቡ በሚያዘንበው በረከት ላይ ማሰላሰላችን ምን እንድናደርግ ሊያነሳሳን ይገባል? (2 ዜና 7:3፤ መዝ. 22:22፤ 34:1፤ 96:2)

  4. አንደኛ ነገሥት 11:9-13ን አንብብ።

    የሰሎሞን የሕይወት ጎዳና እስከ መጨረሻው ድረስ ታማኝ ሆኖ የመኖርን አስፈላጊነት የሚያሳየው እንዴት ነው? (1 ነገ. 11:4, 9፤ ማቴ. 10:22፤ ራእይ 2:10)

ታሪክ 65

የእስራኤል መንግሥት ተከፋፈለ

  1. በሥዕሉ ላይ የሚታዩት ሁለት ሰዎች ማን ይባላሉ? ምን የኃላፊነት ቦታስ ነበራቸው?

  2. አኪያ ለብሶት የነበረውን አዲስ ልብስ ምን እያደረገው ነው? እንዲህ ማድረጉ ምን ያመለክታል?

  3. ሰሎሞን ኢዮርብዓምን ምን ሊያደርገው ሞክሮ ነበር?

  4. ሕዝቡ ኢዮርብዓምን በአሥሩ ነገድ ላይ ያነገሡት ለምንድን ነው?

  5. ኢዮርብዓም ሁለት የወርቅ ጥጆች የሠራው ለምንድን ነው? ከዚያ በኋላ ብዙም ሳይቆይ በምድሪቱ ላይ ምን ደረሰ?

  6. የሁለቱ ነገድ መንግሥትና በኢየሩሳሌም የነበረው የይሖዋ ቤተ መቅደስ ምን ደረሰባቸው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. አንደኛ ነገሥት 11:26-43ን አንብብ።

    ኢዮርብዓም ምን ዓይነት ሰው ነበር? ይሖዋ ሕጉን ከጠበቀ ምን እንደሚያደርግለት ቃል ገብቶለት ነበር? (1 ነገ. 11:28, 38)

  2. አንደኛ ነገሥት 12:1-33ን አንብብ።

    1. (ሀ) በሥልጣን አላግባብ መጠቀምን በተመለከተ ወላጆችና ሽማግሌዎች ከሮብዓም መጥፎ ምሳሌነት ምን ሊማሩ ይችላሉ? (1 ነገ. 12:13፤ መክ. 7:7፤ 1 ጴጥ. 5:2, 3)

    2. (ለ) ወጣቶች በሕይወታቸው ውስጥ ከባድ ውሳኔዎችን በሚያደርጉበት ጊዜ አስተማማኝ መመሪያ ለማግኘት እነማንን ማማከር ይኖርባቸዋል? (1 ነገ. 12:6, 7፤ ምሳሌ 1:8, 9፤ 2 ጢሞ. 3:16, 17፤ ዕብ. 13:7)

    3. (ሐ) ኢዮርብዓም ሁለት የጥጃ አምልኮ ማዕከሎችን እንዲያቋቁም ያነሳሳው ምንድን ነው? ይህስ በይሖዋ ላይ እምነት እንዳጣ ያሳየው እንዴት ነው? (1 ነገ. 11:37፤ 12:26-28)

    4. (መ) በአሥሩ ነገድ መንግሥት የሚተዳደረው ሕዝብ በእውነተኛው አምልኮ ላይ እንዲያምጽ የመራው ማን ነው? (1 ነገ. 12:32, 33)

ታሪክ 66

ክፉዋ ንግሥት ኤልዛቤል

  1. ኤልዛቤል ማን ነች?

  2. በአንድ ወቅት ንጉሥ አክዓብ ያዘነው ለምን ነበር?

  3. ኤልዛቤል ባሏ አክዓብ የናቡቴን የወይን እርሻ እንዲወስድ ምን አደረገች?

  4. ይሖዋ ኤልዛቤልን ለመቅጣት ማንን ላከ?

  5. በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው ኢዩ ወደ ኤልዛቤል ቤተ መንግሥት ሲደርስ እርሷ ምን አደረገች?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. አንደኛ ነገሥት 16:29-33ን እና 18:3, 4ን አንብብ።

    በንጉሥ አክዓብ የግዛት ዘመን በእስራኤል የነበረው ሁኔታ ምን ያህል አስከፊ ነበር? (1 ነገ. 14:9)

  2. አንደኛ ነገሥት 21:1-16ን አንብብ።

    1. (ሀ) ናቡቴ ድፍረትና ታማኝነት ያሳየው እንዴት ነው? (1 ነገ. 21:1-3፤ ዘሌ. 25:23-28)

    2. (ለ) የሚያበሳጭ ሁኔታ ሲያጋጥመን ከአክዓብ ምሳሌ ምን ልንማር እንችላለን? (1 ነገ. 21:4፤ ሮሜ 5:3-5)

  3. ሁለተኛ ነገሥት 9:30-37ን አንብብ።

    ኢዩ የይሖዋን ፈቃድ ለመፈጸም ካሳየው ቅንዓት ምን ልንማር እንችላለን? (2 ነገ. 9:4-10፤ 2 ቆሮ. 9:1, 2፤ 2 ጢሞ. 4:2)

ታሪክ 67

ኢዮሣፍጥ በይሖዋ ተማመነ

  1. ኢዮሣፍጥ ማን ነው? የኖረውስ በየትኛው ዘመን ነበር?

  2. እስራኤላውያን የፈሩት ለምን ነበር? ከእነርሱ ብዙዎቹስ ምን አደረጉ?

  3. ይሖዋ ለኢዮሣፍጥ ጸሎት ምን መልስ ሰጠ?

  4. ውጊያው ከመጀመሩ በፊት ይሖዋ ምን አደረገ?

  5. ከኢዮሣፍጥ ምን ትምህርት እናገኛለን?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ሁለተኛ ዜና መዋዕል 20:1-30ን አንብብ።

    1. (ሀ) የአምላክ ታማኝ አገልጋዮች አስፈሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሟቸው ምን ማድረግ እንደሚኖርባቸው ኢዮሣፍጥ ያሳየው እንዴት ነው? (2 ዜና 20:12፤ መዝ. 25:15፤ 62:1)

    2. (ለ) ይሖዋ ምንጊዜም ከሕዝቡ ጋር የሚገናኝበት መገናኛ መሥመር ነበረው፤ በዛሬው ጊዜስ የሚጠቀመው በየትኛው የመገናኛ መሥመር ነው? (2 ዜና 20:14, 15፤ ማቴ. 24:45-47፤ ዮሐ. 15:15)

    3. (ሐ) ‘ሁሉን በሚችል አምላክ ታላቅ ቀን በሚሆነው ጦርነት’ ላይ በኢዮሣፍጥ ዘመን ከነበረው ጋር የሚመሳሰል ሁኔታ የሚገጥመን እንዴት ነው? (2 ዜና 20:15, 17፤ 32:8፤ ራእይ 16:14, 16)

    4. (መ) አቅኚዎችና ሚስዮናውያን በኢዮሣፍጥ ዘመን የነበሩትን ሌዋውያን ምሳሌ በመኮረጅ በዛሬው ጊዜ ለሚካሄደው ዓለም አቀፍ የስብከት ሥራ ምን ዓይነት አስተዋጽኦ ያበረክታሉ? (2 ዜና 20:19, 21፤ ሮሜ 10:13-15፤ 2 ጢሞ. 4:2)

ታሪክ 68

ከሞቱ በኋላ እንደገና ሕያው የሆኑ ሁለት ልጆች

  1. በሥዕሉ ላይ የሚታዩት ሦስት ሰዎች እነማን ናቸው? ትንሹ ልጅስ ምን ሆኖ ነበር?

  2. ኤልያስ ልጁን በሚመለከት ምን ብሎ ጸለየ? ከዚያ በኋላስ ምን ሆነ?

  3. የኤልያስ ረዳት ስሙ ማን ይባላል?

  4. ኤልሳዕ በሱነም ወዳለችው ሴት ቤት እንዲመጣ የተጠራው ለምንድን ነው?

  5. ኤልሳዕ ምን አደረገ? የሞተው ልጅስ ምን ሆነ?

  6. ኤልያስና ኤልሳዕ ካከናወኑት ነገር እንደታየው ይሖዋ ምን የማድረግ ኃይል አለው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. አንደኛ ነገሥት 17:8-24ን አንብብ።

    1. (ሀ) የኤልያስ ታዛዥነትና እምነት የተፈተነው እንዴት ነው? (1 ነገ. 17:9፤ 19:1-4, 10)

    2. (ለ) በሰራፕታ የምትኖረው መበለት እምነቷ አስደናቂ የነበረው ለምንድን ነው? (1 ነገ. 17:12-16፤ ሉቃስ 4:25, 26)

    3. (ሐ) የሰራፕታዋ መበለት ተሞክሮ ኢየሱስ በማቴዎስ 10:41, 42 ላይ የተናገራቸው ቃላት እውነት መሆናቸውን የሚያረጋግጠው እንዴት ነው? (1 ነገ. 17:10-12, 17, 23, 24)

  2. ሁለተኛ ነገሥት 4:8-37ን አንብብ።

    1. (ሀ) በሱነም የምትኖረው ሴት እንግዳ ተቀባይ ስለመሆን ምን ታስተምረናለች? (2 ነገ. 4:8፤ ሉቃስ 6:38፤ ሮሜ 12:13፤ 1 ዮሐ. 3:17)

    2. (ለ) በዛሬው ጊዜ ለአምላክ አገልጋዮች ደግነት ልናሳይ የምንችለው በየትኞቹ መንገዶች ነው? (ሥራ 20:35፤ 28:1, 2፤ ገላ. 6:9, 10፤ ዕብ. 6:10)

ታሪክ 69

አንዲት ልጅ አንድ ኃያል ሰው ረዳች

  1. በሥዕሉ ላይ የምትታየው ትንሽ ልጅ ለሴትየዋ ምን እየነገረቻት ነው?

  2. በሥዕሉ ላይ የምትታየው ሴትዮ ማን ነች? ልጅቷስ በዚህች ሴትዮ ቤት ምን ታደርጋለች?

  3. ኤልሳዕ በአገልጋዩ በኩል ለንዕማን ምን መመሪያ ሰጠው? ንዕማን የተናደደው ለምንድን ነው?

  4. ንዕማን አገልጋዮቹ የሰጡትን ምክር ሲሰማ ምን ሆነ?

  5. ኤልሳዕ የንዕማንን ስጦታ መቀበል ያልፈለገው ለምን ነበር? ይሁን እንጂ ግያዝ ምን አደረገ?

  6. ግያዝ ምን ደረሰበት? እኛስ ከዚህ ምን እንማራለን?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ሁለተኛ ነገሥት 5:1-27ን አንብብ።

    1. (ሀ) እስራኤላዊቷ ልጃገረድ የተወችው ምሳሌ በዛሬው ጊዜ ያሉትን ወጣቶች የሚያበረታታቸው እንዴት ነው? (2 ነገ. 5:3፤ መዝ. 8:2፤ 148:12, 13)

    2. (ለ) ቅዱስ ጽሑፋዊ ምክር ሲሰጠን የንዕማንን ምሳሌ ማስታወሳችን ጠቃሚ የሚሆነው ለምንድን ነው? (2 ነገ. 5:15፤ ዕብ. 12:5, 6፤ ያዕ. 4:6)

    3. (ሐ) የኤልሳዕን ምሳሌነት ከግያዝ ጋር በማነጻጸር ምን ልንማር እንችላለን? (2 ነገ. 5:9, 10, 14-16, 20፤ ማቴ. 10:8፤ ሥራ 5:1-5፤ 2 ቆሮ. 2:17)

ታሪክ 70

ዮናስና ትልቁ ዓሣ

  1. ዮናስ ማን ነው? ይሖዋስ ምን እንዲያደርግ ነግሮት ነበር?

  2. ዮናስ፣ ይሖዋ ሂድ ብሎ ወዳዘዘው ቦታ መሄድ ስላልፈለገ ምን አደረገ?

  3. ማዕበሉ ጸጥ እንዲልላቸው ዮናስ መርከበኞቹን ምን እንዲያደርጉ ነገራቸው?

  4. በሥዕሉ ላይ እንደምታየው ዮናስ ውኃው ውስጥ ሲሰጥም ምን ሆነ?

  5. ዮናስ በትልቁ ዓሣ ሆድ ውስጥ ለምን ያህል ጊዜ ቆየ? በዚያስ ሆኖ ምን አደረገ?

  6. ዮናስ ከትልቁ ዓሣ ሆድ ውስጥ ከወጣ በኋላ ወዴት ሄደ? ይህስ ምን ያስተምረናል?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዮናስ 1:1-17ን አንብብ።

    ከሁኔታው ለመረዳት እንደሚቻለው ዮናስ በነነዌ እንዲሰብክ ስለተሰጠው ተልእኮ ምን ተሰምቶት ነበር? (ዮናስ 1:2, 3፤ ምሳሌ 3:7፤ መክ. 8:12)

  2. ዮናስ 2:1, 2, 10ን አንብብ።

    የዮናስ ተሞክሮ ይሖዋ ለጸሎታችን መልስ እንደሚሰጥ እርግጠኞች እንድንሆን የሚያደርገን እንዴት ነው? (መዝ. 22:24፤ 34:6፤ 1 ዮሐ. 5:14)

  3. ዮናስ 3:1-10ን አንብብ።

    1. (ሀ) ዮናስ የተሰጠውን ተልእኮ በመጀመሪያ ላይ ሳይፈጽም ቢቀርም ከዚያ በኋላ ይሖዋ የተጠቀመበት መሆኑ ምን ማበረታቻ ይሰጠናል? (መዝ. 103:14፤ 1 ጴጥ. 5:10)

    2. (ለ) ዮናስ ከነነዌ ሰዎች ጋር ያሳለፈው ተሞክሮ በክልላችን የሚገኙ ሰዎችን በተመለከተ አስቀድሞ ከመፍረድ ስለመቆጠብ ምን ያስተምረናል? (ዮናስ 3:6-9፤ መክ. 11:6፤ ሥራ 13:48)

ታሪክ 71

አምላክ ገነት እንደሚያመጣ ቃል ገብቷል

  1. ኢሳይያስ ማን ነው? የኖረውስ መቼ ነበር? ይሖዋ ለኢሳይያስ ምን አሳየው?

  2. “ገነት” የሚለው ቃል ትርጉም ምንድን ነው? “ገነት” የሚለውን ቃል ስትሰማ ምን ትዝ ይልሃል?

  3. ይሖዋ ለኢሳይያስ አዲሷን ገነት አስመልክቶ ምን ነገሮችን እንዲጽፍ ነግሮታል?

  4. አዳምና ሔዋን ውብ መኖሪያቸውን ያጡት ለምን ነበር?

  5. ይሖዋ ለሚወዱት ሰዎች ምን እንደሚያደርግላቸው ቃል ገብቷል?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ኢሳይያስ 11:6-9ን አንብብ።

    1. (ሀ) የአምላክ ቃል በአዲሱ ዓለም ውስጥ በእንስሳትና በሰዎች መካከል የሚኖረውን ሰላም የሚገልጸው እንዴት ነው? (መዝ. 148:10, 13፤ ኢሳ. 65:25፤ ሕዝ. 34:25)

    2. (ለ) የኢሳይያስ ቃላት በዛሬው ጊዜ በይሖዋ ሕዝቦች መካከል በመንፈሳዊ ሁኔታ እየተፈጸሙ ያሉት አንዴት ነው? (ሮሜ 12:2፤ ኤፌ. 4:23, 24)

    3. (ሐ) በአሁኑ ጊዜም ሆነ በአዲሱ ዓለም፣ በሰው ባሕርይ ላይ ለሚታየው ለውጥ ሊመሰገን የሚገባው ማን ነው? (ኢሳ. 48:17, 18፤ ገላ. 5:22, 23፤ ፊልጵ. 4:7)

  2. ራእይ 21:3, 4ን አንብብ።

    1. (ሀ) አምላክ ማደሪያውን በሰው ልጆች መካከል ማድረጉ የሚያመለክተው በምሳሌያዊ ሁኔታ መገኘቱን እንጂ በአካል መገኘቱን አለመሆኑን ቅዱሳን መጻሕፍት የሚያሳዩት እንዴት ነው? (ዘሌ. 26:11, 12፤ 2 ዜና 6:18፤ ኢሳ. 66:1፤ ራእይ 21:2, 3, 22-24)

    2. (ለ) የሚወገደው ምን ዓይነት እንባና ሥቃይ ነው? (ሉቃስ 8:49-52፤ ሮሜ 8:21, 22፤ ራእይ 21:4)

ታሪክ 72

አምላክ ንጉሥ ሕዝቅያስን ረዳው

  1. በሥዕሉ ላይ የሚታየው ሰው ማን ነው? በጣም የተጨነቀውስ ለምንድን ነው?

  2. ሕዝቅያስ በአምላክ ፊት የዘረጋቸው እነዚህ ደብዳቤዎች ምንድን ናቸው? ሕዝቅያስ ምን ብሎ ጸለየ?

  3. ሕዝቅያስ ምን ዓይነት ንጉሥ ነው? ይሖዋ በነቢዩ ኢሳይያስ በኩል ምን መልእክት ላከለት?

  4. በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው የይሖዋ መልአክ አሦራውያንን ምን አደረጋቸው?

  5. የሁለቱ ነገድ መንግሥት ለጊዜው ሰላም አግኝቶ የነበረ ቢሆንም ሕዝቅያስ ከሞተ በኋላ ምን ሆነ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ሁለተኛ ነገሥት 18:1-36ን አንብብ።

    1. (ሀ) የአሦር ቃል አቀባይ የሆነው ራፋስቂስ የእስራኤላውያንን እምነት ለማዳከም የጣረው እንዴት ነው? (2 ነገ. 18:19, 21፤ ዘፀ. 5:2፤ መዝ. 64:3)

    2. (ለ) የይሖዋ ምሥክሮች ተቃዋሚዎች ሲያጋጥሟቸው የሕዝቅያስን ምሳሌነት ልብ የሚሉት እንዴት ነው? (2 ነገ. 18:36፤ መዝ. 39:1፤ ምሳሌ 26:4፤ 2 ጢሞ. 2:24)

  2. ሁለተኛ ነገሥት 19:1-37ን አንብብ።

    1. (ሀ) በዛሬው ጊዜ ያሉት የይሖዋ ሕዝቦች በመከራ ወቅት ሕዝቅያስን ሊኮርጁ የሚችሉት እንዴት ነው? (2 ነገ. 19:1, 2፤ ምሳሌ 3:5, 6፤ ዕብ. 10:24, 25፤ ያዕ. 5:14, 15)

    2. (ለ) ንጉሥ ሰናክሬም የደረሰበት ሦስት እጥፍ ሽንፈት ምንድን ነው? በትንቢታዊ ሁኔታ የሚያመለክተውስ ማንን ነው? (2 ነገ. 19:32, 35, 37፤ ራእይ 20:2, 3)

  3. ሁለተኛ ነገሥት 21:1-6, 16ን አንብብ።

    ምናሴ በኢየሩሳሌም ከገዙት ክፉ ነገሥታት ሁሉ የከፋ ነበር ሊባል የሚችለው ለምንድን ነው? (2 ዜና 33:4-6, 9)

ታሪክ 73

የመጨረሻው የእስራኤል ጥሩ ንጉሥ

  1. ኢዮስያስ ንጉሥ የሆነው በስንት ዓመቱ ነበር? ለሰባት ዓመት ከነገሠ በኋላ ምን ማድረግ ጀመረ?

  2. በመጀመሪያው ሥዕል ላይ ኢዮስያስ ምን ሲያደርግ ይታይሃል?

  3. ሰዎቹ ቤተ መቅደሱን በሚያድሱበት ጊዜ ሊቀ ካህኑ ምን አገኘ?

  4. ኢዮስያስ ልብሱን የቀደደው ለምንድን ነው?

  5. ነቢይቱ ሕልዳና ወደ ኢዮስያስ የላከችው ከይሖዋ የመጣ መልእክት ምንድን ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ሁለተኛ ዜና መዋዕል 34:1-28ን አንብብ።

    1. (ሀ) በልጅነታቸው መጥፎ አስተዳደግ ለነበራቸው ሁሉ ኢዮስያስ ምን ምሳሌ ትቶላቸዋል? (2 ዜና 33:21-25፤ 34:1, 2፤ መዝ. 27:10)

    2. (ለ) ኢዮስያስ በነገሠ በ8ኛው፣ በ12ኛውና በ18ኛው ዓመት እውነተኛውን አምልኮ ለማራመድ ምን ጉልህ እርምጃዎችን ወስዷል? (2 ዜና 34:3, 8)

    3. (ሐ) ንጉሥ ኢዮስያስና ሊቀ ካህኑ ኬልቅያስ ከተዉት ምሳሌ የአምልኮ ቦታችንን ስለ መጠገን ምን ትምህርት እናገኛለን? (2 ዜና 34:9-13፤ ምሳሌ 11:14፤ 1 ቆሮ. 10:31)

ታሪክ 74

ያለ ፍርሃት ይናገር የነበረው ሰው

  1. በሥዕሉ ላይ የሚታየው ወጣት ማን ነው?

  2. ኤርምያስ ነቢይ እንደሚሆን ሲያውቅ ምን ተሰማው? ይሁን እንጂ ይሖዋ ምን አለው?

  3. ኤርምያስ ለሕዝቡ የትኛውን መልእክት መናገሩን ቀጠለ?

  4. ካህናቱ ኤርምያስ መናገሩን እንዲያቆም ለማድረግ የሞከሩት እንዴት ነው? ይሁን እንጂ ኤርምያስ አለመፍራቱን እንዴት አሳየ?

  5. እስራኤላውያን ከመጥፎ መንገዳቸው ባለመመለሳቸው ምን ደረሰባቸው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ኤርምያስ 1:1-8ን አንብብ።

    1. (ሀ) የኤርምያስ ተሞክሮ እንደሚያሳየው አንድን ሰው ለይሖዋ አገልግሎት ብቁ የሚያደርገው ምንድን ነው? (2 ቆሮ. 3:5, 6)

    2. (ለ) የኤርምያስ ምሳሌ በዛሬው ጊዜ ለሚገኙ ወጣቶች ምን ማበረታቻ ይሰጣቸዋል? (መክ. 12:1፤ 1 ጢሞ. 4:12)

  2. ኤርምያስ 10:1-5ን አንብብ።

    ኤርምያስ በጣዖታት መታመን ከንቱ መሆኑን ለማሳየት ምን ኃይለኛ አገላለጽ ተጠቅሟል? (ኤር. 10:5፤ ኢሳ. 46:7፤ ዕን. 2:19)

  3. ኤርምያስ 26:1-16ን አንብብ።

    1. (ሀ) በዛሬው ጊዜ ቅቡዓን ቀሪዎች ማስጠንቀቂያውን ሲያሰሙ፣ ይሖዋ ለኤርምያስ ‘አንዲትም ቃል ሳያስቀር’ እንዲናገር የሰጠውን ትእዛዝ ልብ ማለታቸውን ያሳዩት እንዴት ነው? (ኤር. 26:2፤ ዘዳ. 4:2፤ ሥራ 20:27)

    2. (ለ) ኤርምያስ በዛሬው ጊዜ የይሖዋን ማስጠንቀቂያ ለአሕዛብ እያወጁ ላሉት የይሖዋ ምሥክሮች ምን ጥሩ ምሳሌ ትቶላቸዋል? (ኤር. 26:8, 12, 14, 15፤ 2 ጢሞ. 4:1-5)

  4. ሁለተኛ ነገሥት 24:1-17ን አንብብ።

    የይሁዳ ሕዝቦች ለይሖዋ ታማኝ አለመሆናቸው ምን አስከፊ መዘዝ አስከተለባቸው? (2 ነገ. 24:2-4, 14)

ታሪክ 75

በባቢሎን የነበሩ አራት ልጆች

  1. በሥዕሉ ላይ የሚታዩት አራት ልጆች እነማን ናቸው? ወደ ባቢሎን የሄዱትስ ለምን ነበር?

  2. ናቡከደነፆር አራቱን ልጆች ምን ሊያደርጋቸው አቀደ? ለአገልጋዮቹስ ምን ትእዛዝ ሰጠ?

  3. ዳንኤል ለራሱና ለሦስቱ ጓደኞቹ እንዲቀርብላቸው የሚፈልጉትን ምግብና መጠጥ በሚመለከት ምን ልመና አቀረበ?

  4. ዳንኤልና ሦስት ጓደኞቹ ለአሥር ቀናት አትክልት ከተመገቡ በኋላ ከሌሎቹ ወጣቶች ጋር ሲወዳደሩ እንዴት ሆነው ተገኙ?

  5. ዳንኤልና ሦስት ጓደኞቹ በንጉሡ ቤተ መንግሥት ውስጥ ሊገኙ የቻሉት እንዴት ነው? ከካህናቱና ከጠቢባኑ ሁሉ የተሻሉ ሆነው የተገኙትስ በምን መንገድ ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዳንኤል 1:1-21ን አንብብ።

    1. (ሀ) ፈተናዎችን ለመቋቋምና ድክመቶችን ለማሸነፍ የምንፈልግ ከሆነ ምን ዓይነት ጥረት ማድረግ ያስፈልገናል? (ዳን. 1:8፤ ዘፍ. 39:7, 10፤ ገላ. 6:9)

    2. (ለ) በዛሬው ጊዜ ያሉ ወጣቶች አንዳንዶች ‘ደስ እንደሚያሰኙ’ አድርገው በሚቆጥሯቸው በየትኞቹ ነገሮች እንዲካፈሉ ግፊት ሊደረግባቸው ወይም ሊፈተኑ ይችላሉ? (ዳን. 1:8 የ1980 ትርጉም፤ ምሳሌ 20:1፤ 2 ቆሮ. 6:17–7:1)

    3. (ሐ) ስለ አራቱ ዕብራውያን ወጣቶች የቀረበው የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ዓለማዊ እውቀት ስለ መቅሰም ምን እንድንገነዘብ ይረዳናል? (ዳን. 1:20፤ ኢሳ. 54:13፤ 1 ቆሮ. 3:18-20)

ታሪክ 76

ኢየሩሳሌም ጠፋች

  1. በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው ኢየሩሳሌምና እስራኤላውያን ምን ሆኑ?

  2. ሕዝቅኤል ማን ነው? ይሖዋ እንዴት ያሉ አስደንጋጭ ነገሮችን አሳየው?

  3. እስራኤላውያን ለይሖዋ አክብሮት ስላልነበራቸው ይሖዋ ምን ብሎ ማለ?

  4. ንጉሥ ናቡከደነፆር እስራኤላውያን ሲያምጹበት ምን አደረጋቸው?

  5. ይሖዋ በእስራኤላውያን ላይ ይህን የመሰለ አሰቃቂ ጥፋት እንዲደርስ የፈቀደው ለምንድን ነው?

  6. የእስራኤል ምድር ሰው አልባ የሆነው እንዴት ነው? ለምን ያህል ጊዜስ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ሁለተኛ ነገሥት 25:1-26ን አንብብ።

    1. (ሀ) ሴዴቅያስ ማን ነበር? እርሱስ ምን ደረሰበት? ይህስ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ፍጻሜ የሆነው እንዴት ነው? (2 ነገ. 25:5-7፤ ሕዝ. 12:13-15)

    2. (ለ) ይሖዋ እስራኤላውያን ታማኝ ላለመሆናቸው ተጠያቂ ያደረገው ማንን ነው? (2 ነገ. 25:9, 11, 12, 18, 19፤ 2 ዜና 36:14, 17)

  2. ሕዝቅኤል 8:1-18ን አንብብ።

    ሕዝበ ክርስትና ከሃዲዎቹን ፀሐይ አምላኪ እስራኤላውያን የምትመስለው እንዴት ነው? (ሕዝ. 8:16፤ ኢሳ. 5:20, 21፤ ዮሐ. 3:19-21፤ 2 ጢሞ. 4:3)

ታሪክ 77

ለምስሉ አልሰገዱም

  1. የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ለሕዝቡ ምን ትእዛዝ ሰጠ?

  2. ሦስቱ የዳንኤል ጓደኞች ለወርቁ ምስል ያልሰገዱት ለምንድን ነው?

  3. ናቡከደነፆር ለምስሉ እንዲሰግዱ ሌላ ዕድል በሰጣቸው ጊዜ ሦስቱ ዕብራውያን በይሖዋ እንደሚተማመኑ ያሳዩት እንዴት ነው?

  4. ናቡከደነፆር አብረውት የነበሩትን ሰዎች ጠርቶ ሲድራቅን፣ ሚሳቅንና አብደናጎን ምን እንዲያደርጓቸው አዘዘ?

  5. ናቡከደነፆር ወደ እሳቱ ሲመለከት ምን አየ?

  6. ንጉሡ የሲድራቅ፣ የሚሳቅና የአብደናጎን አምላክ ያመሰገነው ለምንድን ነው? እነርሱስ ለእኛ ምን ምሳሌ ትተውልናል?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዳንኤል 3:1-30ን አንብብ።

    1. (ሀ) የአምላክ አገልጋዮች የታማኝነት ፈተና ሲደርስባቸው ሦስቱ ዕብራውያን ያሳዩትን የትኛውን አመለካከት መኮረጅ ይኖርባቸዋል? (ዳን. 3:17, 18፤ ማቴ. 10:28፤ ሮሜ 14:7, 8)

    2. (ለ) ይሖዋ ለናቡከደነፆር ምን ጠቃሚ ትምህርት ሰጥቶታል? (ዳን. 3:28, 29፤ 4:34, 35)

ታሪክ 78

በግድግዳ ላይ በእጅ የተጻፈ ጽሑፍ

  1. የባቢሎን ንጉሥ ትልቅ ድግስ አዘጋጅቶ በኢየሩሳሌም ከነበረው የይሖዋ ቤተ መቅደስ በተወሰዱ መጠጫዎችና ሳህኖች ሲጠቀም ምን ተከሰተ?

  2. ብልጣሶር ለጠቢባኑ ምን አላቸው? ይሁን እንጂ እነሱ ምን ሊያደርጉ አልቻሉም?

  3. የንጉሡ እናት ምን እንዲያደርግ ነገረችው?

  4. ዳንኤል ለንጉሡ በነገረው መሠረት አምላክ በግድግዳው ላይ የጻፈውን እጅ የላከው ለምንድን ነው?

  5. ዳንኤል በግድግዳው ላይ የተጻፉትን ቃላት ትርጉም የገለጸው እንዴት ነው?

  6. ዳንኤል ገና እየተናገረ ሳለ ምን ሆነ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዳንኤል 5:1-31ን አንብብ።

    1. (ሀ) ብልጣሶር በግድግዳ ላይ የነበረውን ጽሑፍ ሲያይ የተሰማውን ፍርሃት ከአምላካዊ ፍርሃት ጋር አነጻጽር። (ዳን. 5:6, 7፤ መዝ. 19:9፤ ሮሜ 8:35-39)

    2. (ለ) ዳንኤል ለብልጣሶርና ለመኳንንቱ ሲናገር ትልቅ ድፍረት እንደነበረው ያሳየው እንዴት ነው? (ዳን. 5:17, 18, 22, 26-28፤ ሥራ 4:29)

    3. (ሐ) ዳንኤል ምዕራፍ 5 የይሖዋን ጽንፈ ዓለማዊ ሉዓላዊነት ጎላ አድርጎ የሚገልጸው እንዴት ነው? (ዳን. 4:17, 25፤ 5:21)

ታሪክ 79

ዳንኤል በአንበሶች ጉድጓድ ውስጥ

  1. ዳርዮስ ማን ነው? ዳንኤልንስ የሚመለከተው እንዴት ነው?

  2. አንዳንድ ምቀኛ ሰዎች ዳርዮስን ምን እንዲያደርግ ገፋፉት?

  3. ዳንኤል ስለ አዲሱ ሕግ ሲሰማ ምን አደረገ?

  4. ዳርዮስ መተኛት እስኪያቅተው ድረስ የተረበሸው ለምንድን ነው? በማግስቱ ጠዋትስ ምን አደረገ?

  5. ዳንኤል ለዳርዮስ ጥያቄ ምን መልስ ሰጠ?

  6. ዳንኤልን ለማስገደል የሞከሩት ክፉ ሰዎች ምን ደረሰባቸው? ዳርዮስስ በግዛቱ ላሉ ሕዝቦች ሁሉ ምን ብሎ ጻፈ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዳንኤል 6:1-28ን አንብብ።

    1. (ሀ) በዳንኤል ላይ የተጠነሰሰው ሴራ በዘመናችን ተቃዋሚዎች የይሖዋ ምሥክሮችን ሥራ ለማስቆም ያደረጉትን ሙከራ የሚያስታውሰን እንዴት ነው? (ዳን. 6:7፤ መዝ. 94:20፤ ኢሳ. 10:1፤ ሮሜ 8:31)

    2. (ለ) በዛሬው ጊዜ ያሉት የአምላክ አገልጋዮች “በሥልጣን ላሉት ሹማም[ን]ት” በመገዛት ረገድ ዳንኤልን ሊመስሉ የሚችሉት እንዴት ነው? (ዳን. 6:5, 10፤ ሮሜ 13:1፤ ሥራ 5:29)

    3. (ሐ) ይሖዋን “ሁልጊዜ” በማገልገል ረገድ የዳንኤልን ምሳሌ ልንኮርጅ የምንችለው እንዴት ነው? (ዳን. 6:16, 20፤ ፊልጵ. 3:16፤ ራእይ 7:15)

ታሪክ 80

የአምላክ ሕዝቦች ከባቢሎን ወጡ

  1. በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው እስራኤላውያን ምን እያደረጉ ነው?

  2. ይሖዋ በኢሳይያስ በኩል የተናገረውን ትንቢት ቂሮስ የፈጸመው እንዴት ነው?

  3. ቂሮስ ወደ ኢየሩሳሌም መመለስ ያልቻሉትን እስራኤላውያን ምን አላቸው?

  4. እስራኤላውያን ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሱ ይዘውት እንዲሄዱ ቂሮስ የሰጣቸው ምንድን ነው?

  5. እስራኤላውያን ኢየሩሳሌም ለመድረስ ምን ያህል ጊዜ ፈጀባቸው?

  6. ምድሪቱ ሰው አልባ ሆና የቆየችው ለስንት ዓመት ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ኢሳይያስ 44:28 እና 45:1-4ን አንብብ።

    1. (ሀ) ቂሮስን አስመልክቶ የተነገረው ትንቢት ያለጥርጥር መፈጸሙ እንደማይቀር ይሖዋ ጠበቅ አድርጎ የገለጸው እንዴት ነው? (ኢሳ. 55:10, 11፤ ሮሜ 4:17)

    2. (ለ) ኢሳይያስ ቂሮስን በተመለከተ የተናገረው ትንቢት ይሖዋ ስለወደፊቱ ጊዜ አስቀድሞ የመናገር ችሎታ ያለው መሆኑን የሚያሳየው እንዴት ነው? (ኢሳ. 42:9፤ 45:21፤ 46:10, 11፤ 2 ጴጥ. 1:20)

  2. ዕዝራ 1:1-11ን አንብብ።

    ወደ ኢየሩሳሌም መመለስ ያልቻሉትን እስራኤላውያን ምሳሌ በመከተል እኛ ወደ ሙሉ ጊዜ አገልግሎት የገቡትን ወንድሞችና እህቶች ‘ልንረዳቸው’ የምንችለው እንዴት ነው? (ዕዝራ 1:4, 6፤ ሮሜ 12:13፤ ቈላ. 4:12)

ታሪክ 81

በአምላክ እርዳታ መተማመን

  1. ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም የሚወስደውን ረዥም ጉዞ የተጓዙት ስንት ሰዎች ነበሩ? ይሁን እንጂ ኢየሩሳሌም ሲደርሱ የገጠማቸው ምን ነበር?

  2. እስራኤላውያን ኢየሩሳሌም ከደረሱ በኋላ ምን መገንባት ጀመሩ? ይሁን እንጂ ጠላቶቻቸው ምን አደረጉ?

  3. ሐጌና ዘካርያስ እነማን ናቸው? እነርሱስ ለሕዝቡ ምን ተናገሩ?

  4. ተንትናይ ወደ ባቢሎን ምን ደብዳቤ ላከ? ከዚያስ ምን መልስ መጣለት?

  5. ዕዝራ የአምላክ ቤተ መቅደስ ጥገና እንደሚያስፈልገው በተገነዘበ ጊዜ ምን አደረገ?

  6. በሥዕሉ ላይ ዕዝራ ስለ ምን ጉዳይ ሲጸልይ ይታያል? ለጸሎቱ መልስ ያገኘው እንዴት ነው? ይህስ ለእኛ ምን ያስተምረናል?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዕዝራ 3:1-13ን አንብብ።

    ጉባኤ በሌለበት አካባቢ የምንኖርበት ሁኔታ ቢያጋጥመን እንኳ ምን ማድረጋችንን መቀጠል አለብን? (ዕዝራ 3:3, 6፤ ሥራ 17:16, 17፤ ዕብ. 13:15)

  2. ዕዝራ 4:1-7ን አንብብ።

    ሃይማኖት መቀላቀልን በሚመለከት ዘሩባቤል ለይሖዋ ሕዝቦች የተወው ምሳሌ ምንድን ነው? (ዘፀ. 34:12፤ 1 ቆሮ. 15:33፤ 2 ቆሮ. 6:14-17)

  3. ዕዝራ 5:1-5, 17 እና 6:1-22ን አንብብ።

    1. (ሀ) ተቃዋሚዎች የቤተ መቅደሱን ግንባታ ማስቆም ያልቻሉት ለምንድን ነው? (ዕዝራ 5:5፤ ኢሳ. 54:17)

    2. (ለ) ክርስቲያን ሽማግሌዎች ተቃዋሚ በሚያጋጥማቸው ጊዜ የይሖዋን አመራር በመፈለግ ረገድ የአይሁድ መሪዎች የወሰዱት እርምጃ ማበረታቻ የሚሆናቸው እንዴት ነው? (ዕዝራ 6:14፤ መዝ. 32:8፤ ሮሜ 8:31፤ ያዕ. 1:5)

  4. ዕዝራ 8:21-23, 28-36ን አንብብ።

    አንድ ዓይነት ሥራ ከመጀመራችን በፊት የትኛውን የዕዝራን ምሳሌ ብንከተል ጥሩ ይሆናል? (ዕዝራ 8:23፤ መዝ. 127:1፤ ምሳሌ 10:22፤ ያዕ. 4:13-15)

ታሪክ 82

መርዶክዮስና አስቴር

  1. መርዶክዮስና አስቴር እነማን ናቸው?

  2. ንጉሥ አሐሽዌሮሽ አዲስ ሚስት ለማግባት የፈለገው ለምንድን ነው? ሚስቱ እንድትሆን የመረጠውስ ማንን ነው?

  3. ሐማ ማን ነው? በጣም የተቆጣውስ ለምንድን ነው?

  4. ምን አዋጅ ወጣ? አስቴር ከመርዶክዮስ የተላከ መልእክት ከደረሳት በኋላ ምን አደረገች?

  5. ሐማ ምን ደረሰበት? መርዶክዮስስ ምን ሆነ?

  6. እስራኤላውያን ከጠላቶቻቸው የዳኑት እንዴት ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. አስቴር 2:12-18ን አንብብ።

    አስቴር “ገርና ጭምት መንፈስ” የማዳበርን ጠቀሜታ በተግባር ያሳየችው እንዴት ነው? (አስ. 2:15፤ 1 ጴጥ. 3:1-5)

  2. አስቴር 4:1-17ን አንብብ።

    አስቴር ለእውነተኛው አምልኮ ያደረች መሆኗን ለማሳየት የሚያስችል አጋጣሚ እንደተሰጣት ሁሉ በዛሬው ጊዜ ለአምላክ ያደርን መሆናችንንና ለይሖዋ ያለንን ታማኝነት የምንገልጽበት ምን አጋጣሚ ተሰጥቶናል? (አስ. 4:13, 14፤ ማቴ. 5:14-16፤ 24:14)

  3. አስቴር 7:1-6ን አንብብ።

    በዛሬው ጊዜ ያሉ በርካታ የአምላክ ሕዝቦች ከአስቴር ጋር በሚመሳሰል መንገድ ለስደት የተጋለጡት እንዴት ነው? (አስ. 7:4፤ ማቴ. 10:16-22፤ 1 ጴጥ. 2:12)

ታሪክ 83

የኢየሩሳሌም ግንብ

  1. እስራኤላውያን በኢየሩሳሌም ከተማ ዙሪያ ቅጥር ባለመኖሩ ምን ይሰማቸው ነበር?

  2. ነህምያ ማን ነው?

  3. የነህምያ ሥራ ምንድን ነው? ሥራው ይህን ያህል አስፈላጊ የሆነውስ ለምንድን ነው?

  4. ነህምያን በጣም ያሳዘነው ዜና ምን ነበር? ከዚያስ ምን አደረገ?

  5. ንጉሥ አርጤክስስ ለነህምያ ደግነት ያሳየው እንዴት ነው?

  6. የእስራኤላውያን ጠላቶች የግንባታ ሥራውን እንዳያስቆሙት ሲል ነህምያ ምን ዝግጅት አደረገ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ነህምያ 1:4-6 እና 2:1-20ን አንብብ።

    ነህምያ የይሖዋን አመራር የፈለገው እንዴት ነበር? (ነህ. 2:4, 5፤ ሮሜ 12:12፤ 1 ጴጥ. 4:7)

  2. ነህምያ 3:3-5ን አንብብ።

    በቴቁሐ ሰዎችና ‘በመኳንንቶቻቸው’ መካከል የነበረውን ልዩነት በማነጻጸር ሽማግሌዎችና የጉባኤ አገልጋዮች ምን ሊማሩ ይችላሉ? (ነህ. 3:5, 27፤ 2 ተሰ. 3:7-10፤ 1 ጴጥ. 5:5)

  3. ነህምያ 4:1-23ን አንብብ።

    1. (ሀ) እስራኤላውያን የከረረ ተቃውሞ ቢያጋጥማቸውም ግንባታውን እንዲቀጥሉ ያነሳሳቸው ምንድን ነው? (ነህ. 4:6, 8, 9፤ መዝ. 50:15፤ ኢሳ. 65:13, 14)

    2. (ለ) የእስራኤላውያን ተሞክሮ በዛሬው ጊዜ እኛን የሚያበረታታን በምን መንገድ ነው?

  4. ነህምያ 6:15ን አንብብ።

    የኢየሩሳሌም ቅጥር በሁለት ወር ውስጥ ተሠርቶ መጠናቀቁ የእምነትን ኃይል በሚመለከት ምን ያሳያል? (መዝ. 56:3, 4፤ ማቴ. 17:20፤ 19:26)

ታሪክ 84

አንድ መልአክ ማርያምን አነጋገራት

  1. በሥዕሉ ላይ የምትታየው ሴት ማን ናት?

  2. ገብርኤል ለማርያም ምን ነገራት?

  3. ማርያም ከወንድ ጋር ኖራ የማታውቅ ብትሆንም ልጅ እንደምትወልድ ገብርኤል ያስረዳት እንዴት ነው?

  4. ማርያም ዘመዷን ኤልሳቤጥን ልትጠይቃት ሄዳ ሳለ ምን ተከሰተ?

  5. ዮሴፍ ማርያም መጸነሷን ባወቀ ጊዜ ምን ለማድረግ አሰበ? ይሁን እንጂ ሐሳቡን የለወጠው ለምንድን ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ሉቃስ 1:26-56ን አንብብ።

    1. (ሀ) የአምላክ ልጅ ሕይወት ከመንፈሳዊው ዓለም ወደ ማርያም ማኅፀን ሲዛወር በማርያም ሴቴ ዘር ዕንቁላል በኩል አዳማዊ አለፍጽምና እንዳይተላለፍበት ስለመደረጉ ሉቃስ 1:35 ምን ይጠቁማል? (ሐጌ 2:11-13፤ ዮሐ. 6:69፤ ዕብ. 7:26፤ 10:5)

    2. (ለ) ኢየሱስ ከመወለዱ በፊትም እንኳን ክብር ያገኘው እንዴት ነው? (ሉቃስ 1:41-43)

    3. (ሐ) በዛሬው ጊዜ ልዩ የአገልግሎት መብት ለሚያገኙ ክርስቲያኖች ማርያም ጥሩ ምሳሌ የምትሆናቸው በምን መንገድ ነው? (ሉቃስ 1:38, 46-49፤ 17:10፤ ምሳሌ 11:2)

  2. ማቴዎስ 1:18-25ን አንብብ።

    ኢየሱስ አማኑኤል የሚል መጠሪያ ስም ባይሰጠውም እንኳ ሰው ሆኖ ያከናወነው ተግባር የዚህን ስም ትርጉም መፈጸሙን የሚያሳየው እንዴት ነው? (ማቴ. 1:22, 23፤ ዮሐ. 14:8-10፤ ዕብ. 1:1-3)

ታሪክ 85

ኢየሱስ ጋጣ ውስጥ ተወለደ

  1. በሥዕሉ ላይ የሚታየው ሕፃን ማን ነው? ማርያም ሕፃኑን ያስተኛችው የት ነው?

  2. ኢየሱስ በከብቶች ግርግም ውስጥ የተወለደው ለምንድን ነው?

  3. በሥዕሉ ላይ ወደ ግርግሙ ሲገቡ የሚታዩት ሰዎች እነማን ናቸው? አንድ መልአክ ለሰዎቹ ምን ነገራቸው?

  4. ኢየሱስን በጣም ለየት ያደረገው ነገር ምንድን ነው?

  5. ኢየሱስ የአምላክ ልጅ ተብሎ ሊጠራ የሚችለው ለምንድን ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ሉቃስ 2:1-20ን አንብብ።

    1. (ሀ) አውግስጦስ ቄሣር የኢየሱስን ልደት አስመልክቶ የተነገረው ትንቢት እንዲፈጸም ምን ሚና ተጫውቷል? (ሉቃስ 2:1-4፤ ሚክ. 5:2)

    2. (ለ) አንድ ግለሰብ ‘አምላክ የሚወዳቸው ሰዎች’ ተብለው ከተጠቀሱት መካከል ሊቆጠር የሚችለው እንዴት ነው? (ሉቃስ 2:14፤ ማቴ. 16:24፤ ዮሐ. 17:3፤ ሥራ 3:19፤ ዕብ. 11:6)

    3. (ሐ) እነዚያ ትሑት የይሁዳ እረኞች አዳኝ የሆነው መሲሕ በመወለዱ ከተደሰቱ በዛሬው ጊዜ ያሉ የአምላክ አገልጋዮችስ ለመደሰት የሚያበቃ ምን የላቀ ምክንያት አላቸው? (ሉቃስ 2:10, 11፤ ኤፌ. 3:8, 9፤ ራእይ 11:15፤ 14:6)

ታሪክ 86

በኮከብ እየተመሩ የመጡ ሰዎች

  1. በሥዕሉ ላይ የሚታዩት ሰዎች እነማን ናቸው? ከመካከላቸው አንዱ ወደ አንድ ደማቅ ኮከብ በእጁ የሚጠቁመው ለምንድን ነው?

  2. ንጉሥ ሄሮድስ በጣም የተቆጣው ለምንድን ነው? ከዚያስ ምን አደረገ?

  3. ደማቁ ኮከብ ሰዎቹን እየመራ የወሰዳቸው ወዴት ነበር? ይሁን እንጂ በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው የተመለሱት ለምንድን ነው?

  4. ሄሮድስ ምን ትእዛዝ አስተላለፈ? ለምንስ?

  5. ይሖዋ ዮሴፍን ምን እንዲያደርግ ነገረው?

  6. ይህን አዲስ ኮከብ እንዲያበራ ያደረገው ማን ነው? ለምንስ?

ተጨማሪ ጥያቄ:-

  1. ማቴዎስ 2:1-23ን አንብብ።

    ኢየሱስ ኮከብ ቆጣሪዎቹ ሊያዩት ሲመጡ ዕድሜው ስንት ነበር? የሚኖረውስ የት ነበር? (ማቴ. 2:1, 11, 16)

ታሪክ 87

ወጣቱ ኢየሱስ በቤተ መቅደስ ውስጥ

  1. በዚህ ሥዕል ላይ እንደምናየው ኢየሱስ ስንት ዓመቱ ነው? ያለውስ የት ነው?

  2. ዮሴፍ በየዓመቱ ከቤተሰቡ ጋር ምን ያደርግ ነበር?

  3. ዮሴፍና ማርያም ወደ ቤታቸው ለመመለስ አንድ ቀን ያህል ከተጓዙ በኋላ እንደገና ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሱት ለምንድን ነው?

  4. ዮሴፍና ማርያም ኢየሱስን የት አገኙት? በቤተ መቅደሱ የነበሩት ሰዎች በጣም የተገረሙት ለምንድን ነው?

  5. ኢየሱስ ለእናቱ ለማርያም ምን አላት?

  6. ስለ አምላክ በመማር ረገድ እንደ ኢየሱስ ልንሆን የምንችለው እንዴት ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ሉቃስ 2:41-52ን አንብብ።

    1. (ሀ) በሕጉ መሠረት በዓመታዊ በዓላት ላይ እንዲገኙ የታዘዙት ወንዶች ብቻ ቢሆኑም ዮሴፍና ማርያም በዛሬው ጊዜ ላሉ ወላጆች ምን ጥሩ ምሳሌ ትተውላቸዋል? (ሉቃስ 2:41፤ ዘዳ. 16:16፤ 31:12፤ ምሳሌ 22:6)

    2. (ለ) ለወላጆች መታዘዝን በተመለከተ ኢየሱስ በዛሬው ጊዜ ላሉ ልጆች ጥሩ ምሳሌ የተወላቸው እንዴት ነው? (ሉቃስ 2:51፤ ዘዳ. 5:16፤ ምሳሌ 23:22፤ ቈላ. 3:20)

  2. ማቴዎስ 13:53-56ን አንብብ።

    በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱት አራቱ የኢየሱስ የሥጋ ወንድሞች እነማን ናቸው? ከእነርሱ መካከል ሁለቱ ከጊዜ በኋላ በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ ያገለገሉት እንዴት ነበር? (ማቴ. 13:55፤ ሥራ 12:17፤ 15:6, 13፤ 21:18፤ ገላ. 1:19፤ ያዕ. 1:1፤ ይሁዳ 1)

ታሪክ 88

ዮሐንስ ኢየሱስን አጠመቀው

  1. በሥዕሉ ላይ የሚታዩት ሁለት ሰዎች እነማን ናቸው?

  2. አንድ ሰው የሚጠመቀው እንዴት ነው?

  3. ዮሐንስ ከዚህ ቀደም የሚያጠምቀው እነማንን ነበር?

  4. ኢየሱስ ዮሐንስን እንዲያጠምቀው የጠየቀበት ከሌሎቹ ተጠማቂዎች የተለየ ምክንያት ምንድን ነው?

  5. አምላክ፣ ኢየሱስ ሲጠመቅ መደሰቱን ያሳየው እንዴት ነው?

  6. ኢየሱስ ሰው ወደሌለበት አካባቢ ሄዶ ለ40 ቀናት በቆየ ጊዜ ምን ተከሰተ?

  7. ከመጀመሪያዎቹ የኢየሱስ ተከታዮች ወይም ደቀ መዛሙርት መካከል አንዳንዶቹ እነማን ናቸው? ኢየሱስ የፈጸመው የመጀመሪያው ተአምር ምን ነበር?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ማቴዎስ 3:13-17ን አንብብ።

    ኢየሱስ ጥምቀትን በተመለከተ ደቀ መዛሙርቱ ሊከተሉት የሚገባ ምን ምሳሌ ትቷል? (መዝ. 40:7, 8፤ ማቴ. 28:19, 20፤ ሉቃስ 3:21, 22)

  2. ማቴዎስ 4:1-11ን አንብብ።

    ኢየሱስ ቅዱሳን መጻሕፍትን በመጠቀም የተካነ መሆኑ መጽሐፍ ቅዱስን አዘውትረን እንድናጠና የሚያበረታታን እንዴት ነው? (ማቴ. 4:5-7፤ 2 ጴጥ. 3:17, 18፤ 1 ዮሐ. 4:1)

  3. ዮሐንስ 1:29-51ን አንብብ።

    መጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን የመራቸው ወደ ማን ነበር? በዛሬው ጊዜስ እርሱን ልንኮርጅ የምንችለው እንዴት ነው? (ዮሐ. 1:29, 35, 36፤ 3:30፤ ማቴ. 23:10)

  4. ዮሐንስ 2:1-12ን አንብብ።

    ይሖዋ ለአገልጋዮቹ የሚነፍገው አንዳች መልካም ነገር እንደሌለ የኢየሱስ የመጀመሪያ ተአምር ያሳየው እንዴት ነው? (ዮሐ. 2:9, 10፤ መዝ. 84:11፤ ያዕ. 1:17)

ታሪክ 89

ኢየሱስ ቤተ መቅደሱን አጸዳ

  1. እንስሳቱ በቤተ መቅደሱ ውስጥ እየተሸጡ ያሉት ለምንድን ነው?

  2. ኢየሱስን ያናደደው ምንድን ነው?

  3. በሥዕሉ ላይ እንደምታየው ኢየሱስ ምን እያደረገ ነው? ርግብ ሻጮቹንስ ምን እንዲያደርጉ አዘዛቸው?

  4. የኢየሱስ ተከታዮች ኢየሱስ ያደረገውን ሲመለከቱ ምን ትዝ አላቸው?

  5. ኢየሱስ ወደ ገሊላ ሲመለስ እግረ መንገዱን ጎራ ያለው ወደ የትኛው አውራጃ ነው?

ተጨማሪ ጥያቄ:-

  1. ዮሐንስ 2:13-25ን አንብብ።

    ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ግቢ ውስጥ ገንዘብ መንዛሪዎችን ባገኘ ጊዜ መቆጣቱን ስንመለከት በመንግሥት አዳራሽ ውስጥ የንግድ እንቅስቃሴ ማካሄድን በተመለከተ ሊኖረን የሚገባው ተገቢ አመለካከት ምንድን ነው? (ዮሐ. 2:15, 16፤ 1 ቆሮ. 10:24, 31-33)

ታሪክ 90

ከአንዲት ሴት ጋር በውኃው ጉድጓድ አጠገብ

  1. ኢየሱስ በሰማርያ በሚገኝ በአንድ የውኃ ጉድጓድ አጠገብ ያረፈው ለምን ነበር? እዚያ ላገኛት ሴትስ ምን እያላት ነው?

  2. ሴትየዋ የተደነቀችው ለምንድን ነው? ኢየሱስ ምን ብሎ ነገራት? ለምንስ?

  3. ሴትየዋ ኢየሱስ እየተናገረ ያለው ስለ የትኛው ውኃ መስሏት ነበር? ይሁን እንጂ ኢየሱስ ምን ማለቱ ነበር?

  4. ኢየሱስ ስለ እርሷ ማወቁ ሴትየዋን ያስደነቃት ለምንድን ነው? ይህን ሊያውቅ የቻለውስ እንዴት ነው?

  5. በውኃው ጉድጓድ አጠገብ ከኢየሱስ ጋር ስለተወያየችው ሴት ከሚገልጸው ታሪክ ምን ትምህርት እናገኛለን?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዮሐንስ 4:5-43ን አንብብ።

    1. (ሀ) ኢየሱስ የተወውን ምሳሌ በመከተል የተለያየ ዘር ወይም አስተዳደግ ላላቸው ሰዎች ምን ዓይነት አመለካከት ሊኖረን ይገባል? (ዮሐ. 4:9፤ 1 ቆሮ. 9:22፤ 1 ጢሞ. 2:3, 4፤ ቲቶ 2:11)

    2. (ለ) የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የሚሆን ሰው ምን ዓይነት መንፈሳዊ ጥቅሞች ያገኛል? (ዮሐ. 4:14፤ ኢሳ. 58:11፤ 2 ቆሮ. 4:16)

    3. (ሐ) ያወቀችውን ነገር ለሌሎች ለማካፈል ከፍተኛ ጉጉት እንደነበራት እንደ ሳምራዊቷ ሴት እኛም አድናቆታችንን እንዴት ማሳየት እንችላለን? (ዮሐ. 4:7, 28፤ ማቴ. 6:33፤ ሉቃስ 10:40-42)

ታሪክ 91

ኢየሱስ በአንድ ተራራ ላይ ሲያስተምር

  1. በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው ኢየሱስ እያስተማረ ያለው የት ሆኖ ነው? አጠገቡ የተቀመጡትስ እነማን ናቸው?

  2. የ12ቱ ሐዋርያት ስም ማን ይባላል?

  3. ኢየሱስ የሚሰብከው መንግሥት ምንድን ነው?

  4. ኢየሱስ ሰዎቹን ምን ብለው እንዲጸልዩ አስተማራቸው?

  5. ኢየሱስ አንዳቸው ለሌላው ምን ዓይነት ጠባይ ማሳየት እንዳለባቸው ሲያስተምራቸው ምን አለ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ማቴዎስ 5:1-12ን አንብብ።

    ለመንፈሳዊ ፍላጎታችን ንቁ መሆናችንን ማሳየት የምንችለው በየትኞቹ መንገዶች ነው? (ማቴ. 5:3፤ ሮሜ 10:13-15፤ 1 ጢሞ. 4:13, 15, 16)

  2. ማቴዎስ 5:21-26ን አንብብ።

    ከወንድሞቻችን ጋር ያለን ግንኙነት ከይሖዋ ጋር የመሠረትነውን ዝምድና እንደሚነካብን ማቴዎስ 5:23, 24 ጠበቅ አድርጎ የሚገልጸው እንዴት ነው? (ማቴ. 6:14, 15፤ መዝ. 133:1፤ ቈላ. 3:13፤ 1 ዮሐ. 4:20)

  3. ማቴዎስ 6:1-8ን አንብብ።

    ክርስቲያኖች ሊርቋቸው የሚገቡ አንዳንድ ራስን የማመጻደቅ ድርጊቶች ምንድን ናቸው? (ሉቃስ 18:11, 12፤ 1 ቆሮ. 4:6, 7፤ 2 ቆሮ. 9:7)

  4. ማቴዎስ 6:25-34ን አንብብ።

    ኢየሱስ የሚያስፈልጉንን ቁሳዊ ነገሮች በተመለከተ በይሖዋ መታመን እንዳለብን ሲያስተምር ምን ብሏል? (ዘፀ. 16:4፤ መዝ. 37:25፤ ፊልጵ. 4:6)

  5. ማቴዎስ 7:1-11ን አንብብ።

    በማቴዎስ 7:5 ላይ የሚገኘው ግልጽ ምሳሌ ምን ያስተምረናል? (ምሳሌ 26:12፤ ሮሜ 2:1፤ 14:10፤ ያዕ. 4:11, 12)

ታሪክ 92

ኢየሱስ የሞቱ ሰዎችን አስነሳ

  1. በሥዕሉ ላይ የምትታየው ልጅ አባት ማን ነው? እርሱና ሚስቱ በጣም የተጨነቁትስ ለምንድን ነው?

  2. ኢያኢሮስ ኢየሱስን ሲያገኘው ምን አደረገ?

  3. ኢየሱስ ወደ ኢያኢሮስ ቤት በመጓዝ ላይ ሳለ ምን አጋጠመው? ኢያኢሮስ በመንገድ ላይ ሳለ ምን መልእክት ደረሰው?

  4. በኢያኢሮስ ቤት የነበሩት ሰዎች በኢየሱስ ላይ የሳቁት ለምንድን ነው?

  5. ኢየሱስ ሦስቱን ሐዋርያቱን ጨምሮ የልጅቷን አባትና እናት፣ ልጅቷ ወዳለችበት ክፍል ካስገባቸው በኋላ ምን አደረገ?

  6. ኢየሱስ ከኢያኢሮስ ልጅ ሌላ እነማንን ከሞት አስነስቷል? ይህስ ምን ያሳያል?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ሉቃስ 8:40-56ን አንብብ።

    ኢየሱስ ደም ይፈሳት ለነበረችው ሴት ርኅራኄና ምክንያታዊነት ያሳየው እንዴት ነው? በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ከዚህ ምን ሊማሩ ይችላሉ? (ሉቃስ 8:43, 44, 47, 48፤ ዘሌ. 15:25-27፤ ማቴ. 9:12, 13፤ ቈላ. 3:12-14)

  2. ሉቃስ 7:11-17ን አንብብ።

    የሚወዱትን ሰው በሞት ያጡ ሁሉ ኢየሱስ በናይን ላገኛት መበለት ከሰጠው መልስ ታላቅ መጽናኛ ሊያገኙ የሚችሉት ለምንድን ነው? (ሉቃስ 7:13፤ 2 ቆሮ. 1:3, 4፤ ዕብ. 4:15)

  3. ዮሐንስ 11:17-44ን አንብብ።

    የሚወዱት ሰው ሲሞት ማዘን ያለ ነገር መሆኑን ኢየሱስ በተግባር የገለጸው እንዴት ነው? (ዮሐ. 11:33-36, 38፤ 2 ሳሙ. 18:33፤ 19:1-4)

ታሪክ 93

ኢየሱስ ብዙ ሰዎችን መገበ

  1. መጥምቁ ዮሐንስ ምን አሰቃቂ ነገር ደረሰበት? ኢየሱስ ጉዳዩን ሲሰማ ምን ተሰማው?

  2. ኢየሱስ የተከተሉትን ብዙ ሕዝብ የመገበው እንዴት ነው? ምን ያህልስ ምግብ ተረፈ?

  3. ሌሊት ላይ ደቀ መዛሙርቱ የፈሩት ለምን ነበር? ጴጥሮስ ምን ሆነ?

  4. ኢየሱስ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ለሁለተኛ ጊዜ የመገበው እንዴት ነው?

  5. ኢየሱስ በአምላክ የተሾመ ንጉሥ ሆኖ ምድርን የሚገዛበት ጊዜ በጣም አስደሳች የሚሆነው ለምንድን ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ማቴዎስ 14:1-32ን አንብብ።

    1. (ሀ) በ⁠ማቴዎስ 14:23-32 ላይ ያለው ታሪክ ስለ ጴጥሮስ ባሕርይ ምን ያስገነዝበናል?

    2. (ለ) ጴጥሮስ መጎልመስና የችኩልነት ባሕሪውን ማሸነፍ እንደቻለ የቅዱሳን መጻሕፍት ዘገባዎች የሚያሳዩት እንዴት ነው? (ማቴ. 14:27-30፤ ዮሐ. 18:10፤ 21:7፤ ሥራ 2:14, 37-40፤ 1 ጴጥ. 5:6, 10)

  2. ማቴዎስ 15:29-38ን አንብብ።

    ኢየሱስ አባቱ ላደረገው ቁሳዊ ዝግጅት አክብሮት እንዳለው ያሳየው እንዴት ነው? (ማቴ. 15:37፤ ዮሐ. 6:12፤ ቈላ. 3:15)

  3. ዮሐንስ 6:1-21ን አንብብ።

    በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያኖች ከሥልጣን ጋር በተያያዘ የኢየሱስን ምሳሌ ሊከተሉ የሚችሉት እንዴት ነው? (ዮሐ. 6:15፤ ማቴ. 22:21፤ ሮሜ 12:2፤ 13:1-4)

ታሪክ 94

ኢየሱስ ትንንሽ ልጆችን ይወዳል

  1. ደቀ መዛሙርቱ ከሄዱበት ረዥም ጉዞ በመመለስ ላይ ሳሉ ስለ ምን ጉዳይ ይከራከሩ ነበር?

  2. ኢየሱስ አንድ ትንሽ ልጅ አምጥቶ በሐዋርያቱ መካከል ያቆመው ለምንድን ነው?

  3. ሐዋርያቱ እንደ ሕፃናት መሆንን መማር ያለባቸው በምን ረገድ ነው?

  4. ከጥቂት ወራት በኋላ፣ ኢየሱስ ልጆችን እንደሚወድ ያሳየው እንዴት ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ማቴዎስ 18:1-4ን አንብብ።

    ኢየሱስ ሌሎችን ለማስተማር በምሳሌዎች ይጠቀም የነበረው ለምንድን ነው? (ማቴ. 13:34, 36፤ ማር. 4:33, 34)

  2. ማቴዎስ 19:13-15ን አንብብ።

    ከመንግሥቱ በረከቶች ተካፋይ ለመሆን ከፈለግን ትንንሽ ልጆች ያሏቸውን የትኞቹን ባሕርያት መኮርጅ ይገባናል? (መዝ. 25:9፤ 138:6፤ 1 ቆሮ. 14:20)

  3. ማርቆስ 9:33-37ን አንብብ።

    ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ የክብር ቦታን ስለ መፈለግ ምን ትምህርት ሰጥቷቸዋል? (ማር. 9:35፤ ማቴ. 20:25, 26፤ ገላ. 6:3፤ ፊልጵ. 2:5-8)

  4. ማርቆስ 10:13-16ን አንብብ።

    ኢየሱስ ምን ያህል በቀላሉ የሚቀረብ ሰው ነበር? ክርስቲያን ሽማግሌዎች ከእርሱ ምሳሌ ምን ይማራሉ? (ማር. 6:30-34፤ ፊልጵ. 2:1-4፤ 1 ጢሞ. 4:12)

ታሪክ 95

ኢየሱስ ያስተማረበት መንገድ

  1. አንድ ሰው ኢየሱስን ምን ጥያቄ ጠየቀው? ለምንስ?

  2. ኢየሱስ ሲያስተምር አንዳንድ ጊዜ ምን ይጠቀማል? ቀደም ሲል ስለ አይሁዳውያንና ስለ ሳምራውያን ምን ተምረናል?

  3. ኢየሱስ በተናገረው ታሪክ ላይ ወደ ኢያሪኮ ሲጓዝ የነበረው አይሁዳዊ ምን ደረሰበት?

  4. አንድ ካህንና አንድ ሌዋዊ አይሁዳዊው ተደብድቦ የወደቀበት ቦታ ላይ ሲደርሱ ምን አደረጉ?

  5. ጉዳት የደረሰበትን አይሁዳዊ በመርዳት ላይ የሚገኘው በሥዕሉ ላይ ያለው ሰው ማን ነው?

  6. ኢየሱስ ታሪኩን ተናግሮ ሲጨርስ ሰውየውን ምን ብሎ ጠየቀው? እርሱስ ምን ብሎ መለሰለት?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ሉቃስ 10:25-37ን አንብብ።

    1. (ሀ) ኢየሱስ ለሕግ አዋቂው ቀጥተኛ መልስ በመስጠት ፈንታ ጉዳዩን እርሱ ራሱ እንዲያመዛዝን የረዳው እንዴት ነው? (ሉቃስ 10:26፤ ማቴ. 16:13-16)

    2. (ለ) ኢየሱስ ምሳሌዎችን ተጠቅሞ አድማጮቹ የነበራቸውን መሠረተ ቢስ ጥላቻ እንዲያሸንፉ የረዳቸው እንዴት ነው? (ሉቃስ 10:36, 37፤ 18:9-14፤ ቲቶ 1:9)

ታሪክ 96

ኢየሱስ የታመሙ ሰዎችን ፈወሰ

  1. ኢየሱስ በመላው የአገሪቱ ክፍል ሲዘዋወር ምን ያደርግ ነበር?

  2. ኢየሱስ ከተጠመቀ ከሦስት ዓመት በኋላ ለሐዋርያቱ ምን ብሎ ነገራቸው?

  3. በሥዕሉ ላይ የሚታዩት ሰዎች እነማን ናቸው? ኢየሱስ ለሴትየዋ ምን አደረገላት?

  4. ኢየሱስ የሃይማኖት መሪዎቹ ለሰነዘሩት የተቃውሞ ሐሳብ የሰጣቸው መልስ ያሳፈራቸው ለምንድን ነው?

  5. ኢየሱስና ሐዋርያቱ ኢያሪኮ አጠገብ ሲደርሱ ኢየሱስ ማየት ለተሳናቸው ሁለት ለማኞች ምን አደረገላቸው?

  6. ኢየሱስ ተአምራት ይፈጽም የነበረው ለምንድን ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ማቴዎስ 15:30, 31ን አንብብ።

    በኢየሱስ በኩል የታየው አስደናቂ የይሖዋ ኃይል መግለጫ ምንድን ነው? ይህስ ይሖዋ ቃል በገባው አዲስ ዓለም ውስጥ ስለሚያደርገው ነገር ያለንን ግንዛቤ የሚነካው እንዴት ነው? (መዝ. 37:29፤ ኢሳ. 33:24)

  2. ሉቃስ 13:10-17ን አንብብ።

    ኢየሱስ አብዛኞቹን አስደናቂ ተአምራት የፈጸመው በሰንበት መሆኑ በሺህ ዓመት ግዛቱ ወቅት ለሰው ልጆች የሚያመጣላቸው እፎይታ ምን እንደሚመስል የሚያሳየው እንዴት ነው? (ሉቃስ 13:10-13፤ መዝ. 46:9፤ ማቴ. 12:8፤ ቈላ. 2:16, 17፤ ራእይ 21:1-4)

  3. ማቴዎስ 20:29-34ን አንብብ።

    ይህ ታሪክ ኢየሱስ ሰዎችን ለመርዳት ጊዜ የለኝም ብሎ እንደማያውቅ የሚያሳየው እንዴት ነው? እኛስ ከዚህ ምን እንማራለን? (ዘዳ. 15:7፤ ያዕ. 2:15, 16፤ 1 ዮሐ. 3:17)

ታሪክ 97

ኢየሱስ ንጉሥ ሆኖ መጣ

  1. ኢየሱስ በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ወዳለች አንዲት አነስተኛ መንደር ሲደርስ ደቀ መዛሙርቱ ምን እንዲያደርጉ ነገራቸው?

  2. በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ሲቃረብ የሆነው ነገር ምንድን ነው?

  3. ኢየሱስ ማየት የተሳናቸውንና ሽባዎችን ሲፈውስ የተመለከቱ ትንንሽ ልጆች ምን አደረጉ?

  4. ኢየሱስ ለተቆጡት ካህናት ምን አላቸው?

  5. ኢየሱስን ያወደሱትን ሕፃናት መምሰል የምንችለው እንዴት ነው?

  6. ደቀ መዛሙርቱ ማወቅ የፈለጉት ምንድን ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ማቴዎስ 21:1-17ን አንብብ።

    1. (ሀ) ኢየሱስ ንጉሥ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም የገባበት ሁኔታ ሮማውያን የጦር አዝማቾች ድል አድርገው ወደ ከተማ ሲገቡ ይታይ ከነበረው ሁኔታ የሚለየው እንዴት ነው? (ማቴ. 21:4, 5፤ ዘካ. 9:9፤ ፊልጵ. 2:5-8፤ ቈላ. 2:15)

    2. (ለ) በዛሬው ጊዜ ያሉ ወጣቶች ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደሱ ሲገባ መዝሙር 118⁠ን ጠቅሰው ካወደሱት ልጆች ምን ትምህርት ሊያገኙ ይችላሉ? (ማቴ. 21:9, 15፤ መዝ. 118:25, 26፤ 2 ጢሞ. 3:15፤ 2 ጴጥ. 3:18)

  2. ዮሐንስ 12:12-16ን አንብብ።

    ኢየሱስን በምስጋና የተቀበሉት ሰዎች የዘንባባ ዝንጣፊ መያዛቸው ምን ያመለክታል? (ዮሐ. 12:13፤ ፊልጵ. 2:10፤ ራእይ 7:9, 10)

ታሪክ 98

በደብረ ዘይት ተራራ ላይ

  1. በሥዕሉ ላይ ካሉት ሰዎች መካከል ኢየሱስ የትኛው ነው? ከእርሱ ጋር ያሉትስ እነማን ናቸው?

  2. በቤተ መቅደስ ውስጥ ካህናቱ ኢየሱስን ምን ሊያደርጉት ሞክረው ነበር? እርሱስ ምን አላቸው?

  3. ሐዋርያቱ ኢየሱስን ምን ብለው ጠየቁት?

  4. ኢየሱስ በሰማይ ንጉሥ ሆኖ በሚገዛበት ጊዜ በምድር ላይ የሚፈጸሙትን አንዳንድ ነገሮች ለሐዋርያቱ የነገራቸው ለምንድን ነው?

  5. ኢየሱስ በምድር ላይ ያለውን ክፋት በሙሉ ጠራርጎ ከማጥፋቱ በፊት ምን እንደሚሆን ተናገረ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ማቴዎስ 23:1-39ን አንብብ።

    1. (ሀ) ቅዱሳን መጻሕፍት ዓለማዊ የማዕረግ መጠሪያዎችን መጠቀም እንደሚቻል የሚጠቁሙ ቢሆንም በ⁠ማቴዎስ 23:8-11 ላይ የሚገኙት የኢየሱስ ቃላት በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ ለሽንገላ ተብሎ የሚሰጡ የማዕረግ ስሞችን ስለመጠቀም ምን ያመለክታሉ? (ሥራ 26:25፤ ሮሜ 13:7፤ 1 ጴጥ. 2:13, 14)

    2. (ለ) ፈሪሳውያኑ፣ ሰዎች ክርስቲያኖች እንዳይሆኑ ለመከልከል የሞከሩት በምን መንገድ ነበር? በዘመናችን ያሉት የሃይማኖት መሪዎችስ ከዚህ ጋር የሚመሳሳል ዘዴ የተጠቀሙት እንዴት ነው? (ማቴ. 23:13፤ ሉቃስ 11:52፤ ዮሐ. 9:22፤ 12:42፤ 1 ተሰ. 2:16)

  2. ማቴዎስ 24:1-14ን አንብብ።

    1. (ሀ) በ⁠ማቴዎስ 24:13 ላይ የመጽናት አስፈላጊነት ጠበቅ ተደርጎ የተገለጸው እንዴት ነው?

    2. (ለ) በ⁠ማቴዎስ 24:13 ላይ “መጨረሻ” የሚለው አባባል ትርጉም ምንድን ነው? (ማቴ. 16:27፤ ሮሜ 14:10-12፤ 2 ቆሮ. 5:10)

  3. ማርቆስ 13:3-10ን አንብብ።

    ምሥራቹን የመስበኩን አጣዳፊነት የሚያሳየው የትኛው የ⁠ማርቆስ 13:10 አገላለጽ ነው? የኢየሱስ ቃላት እኛንስ እንዴት ሊነኩን ይገባል? (ሮሜ 13:11, 12፤ 1 ቆሮ. 7:29-31፤ 2 ጢሞ. 4:2)

ታሪክ 99

ፎቅ ላይ በሚገኝ አንድ ክፍል ውስጥ

  1. በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው ኢየሱስና 12 ሐዋርያቱ በፎቅ ላይ በሚገኝ አንድ ትልቅ ክፍል ውስጥ የተሰበሰቡት ለምን ነበር?

  2. ወደ ውጪ እየወጣ ያለው ሰው ማን ነው? የሚሄደውስ ለምንድን ነው?

  3. የማለፍ በዓልን ለማክበር የተዘጋጀውን ማዕድ ተመግበው ከጨረሱ በኋላ ኢየሱስ ምን ሌላ ልዩ እራት አዘጋጀ?

  4. የማለፍ በዓል እስራኤላውያንን ስለ ምን ነገር ያስታውሳቸዋል? ይሄኛው ልዩ እራት ደግሞ የኢየሱስን ተከታዮች ምን ያስታውሳቸዋል?

  5. ከጌታ እራት በኋላ ኢየሱስ ለሐዋርያቱ ምን ነገራቸው? እነርሱስ ምን አደረጉ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ማቴዎስ 26:14-30ን አንብብ።

    1. (ሀ) ይሁዳ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠው አስቦበትና ሆነ ብሎ እንደነበር ማቴዎስ 26:15 የሚያሳየው እንዴት ነው?

    2. (ለ) የፈሰሰው የኢየሱስ ደም ምን ጥምር ዓላማ ያከናውናል? (ማቴ. 26:27, 28፤ ኤር. 31:31-33፤ ኤፌ. 1:7፤ ዕብ. 9:19, 20)

  2. ሉቃስ 22:1-39ን አንብብ።

    በይሁዳ ውስጥ ሰይጣን ገባበት ሲባል ምን ማለት ነው? (ሉቃስ 22:3፤ ዮሐ. 13:2፤ ሥራ 1:24, 25)

  3. ዮሐንስ 13:1-20ን አንብብ።

    1. (ሀ) በዮሐንስ 13:2 ላይ ከሰፈረው ዘገባ አንጻር ሲታይ ይሁዳ ላደረገው ነገር በጥፋተኝነት ሊጠየቅ ይችላል? የአምላክ አገልጋዮች ከዚህ ምን ትምህርት ያገኛሉ? (ዘፍ. 4:7፤ 2 ቆሮ. 2:11፤ ገላ. 6:1፤ ያዕ. 1:13, 14)

    2. (ለ) ኢየሱስ በተግባር የተደገፈ ምን ዓይነት ኃይለኛ ትምህርት ሰጠ? (ዮሐ. 13:15፤ ማቴ. 23:11፤ 1 ጴጥ. 2:21)

  4. ዮሐንስ 17:1-26ን አንብብ።

    ኢየሱስ ተከታዮቹ “አንድ” እንዲሆኑ የጸለየው ከምን አንጻር ነው? (ዮሐ. 17:11, 21-23፤ ሮሜ 13:8፤ 14:19፤ ቈላ. 3:14)

ታሪክ 100

ኢየሱስ በአንድ የአትክልት ቦታ

  1. ኢየሱስና ሐዋርያቱ በፎቅ ላይ ከነበረው ክፍል ወጥተው ወዴት ሄዱ? ኢየሱስ ለሐዋርያቱ ምን እንዲያደርጉ ነገራቸው?

  2. ኢየሱስ ሐዋርያቱ ወዳሉበት ቦታ ሲመጣ ምን ሆነው አገኛቸው? ኢየሱስ ሐዋርያቱን ተኝተው ያገኛቸው ስንት ጊዜ ነው?

  3. ወደ አትክልቱ ቦታ እነማን ገቡ? በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው የአስቆሮቱ ይሁዳ ምን አደረገ?

  4. ይሁዳ ኢየሱስን የሳመው ለምን ነበር? ጴጥሮስስ ምን አደረገ?

  5. ኢየሱስ ለጴጥሮስ ምን አለው? ታዲያ ኢየሱስ አባቱ መላእክት እንዲልክለት ያልጠየቀው ለምንድን ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ማቴዎስ 26:36-56ን አንብብ።

    1. (ሀ) ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን የመከረበት መንገድ በዛሬው ጊዜ ላሉ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው እንዴት ነው? (ማቴ. 20:25-28፤ 26:40, 41፤ ገላ. 5:17፤ ኤፌ. 4:29, 31, 32)

    2. (ለ) ኢየሱስ የጦር መሣሪያ ተጠቅሞ ስለማጥቃት የነበረው አመለካከት ምንድን ነው? (ማቴ. 26:52፤ ሉቃስ 6:27, 28፤ ዮሐ. 18:36)

  2. ሉቃስ 22:39-53ን አንብብ።

    ኢየሱስ በጌቴሴማኒ የአትክልት ቦታ የሚያበረታታው መልአክ ያየ መሆኑ እምነቱ ላልቶ እንደነበር ያመለክታል? አብራራ። (ሉቃስ 22:41-43፤ ኢሳ. 49:8፤ ማቴ. 4:10, 11፤ ዕብ. 5:7)

  3. ዮሐንስ 18:1-12ን አንብብ።

    ኢየሱስ ተቃዋሚዎቹ ከሚሰነዝሩት ጥቃት ደቀ መዛሙርቱን የተከላከለላቸው እንዴት ነው? እኛስ ከዚህ ምሳሌ ምን እንማራለን? (ዮሐ. 10:11, 12፤ 18:1, 6-9፤ ዕብ. 13:6፤ ያዕ. 2:25)

ታሪክ 101

ኢየሱስ ተገደለ

  1. ለኢየሱስ ሞት በዋነኝነት ተጠያቂው ማን ነው?

  2. ኢየሱስ በሃይማኖት መሪዎቹ ተይዞ ሲወሰድ ሐዋርያቱ ምን አደረጉ?

  3. በሊቀ ካህኑ በቀያፋ ቤት ምን ተደረገ?

  4. ጴጥሮስ ወደ ውጪ ወጥቶ ያለቀሰው ለምንድን ነው?

  5. ኢየሱስ ወደ ጲላጦስ ከተወሰደ በኋላ የካህናት አለቆቹ ምን ብለው ጮኹ?

  6. ኢየሱስ ዓርብ ረፋዱ ላይ ምን ተደረገ? ኢየሱስ ከጎኑ ለተሰቀለው ወንጀለኛ ምን ቃል ገባለት?

  7. ኢየሱስ የተናገረለት ገነት የሚቋቋመው የት ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ማቴዎስ 26:57-75ን አንብብ።

    የአይሁድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አባላት ልባቸው ክፉ መሆኑን ያሳዩት እንዴት ነው? (ማቴ. 26:59, 67, 68)

  2. ማቴዎስ 27:1-50ን አንብብ።

    ይሁዳ የተሰማው ጸጸት እውነተኛ አለመሆኑን እንዴት እናውቃለን? (ማቴ. 27:3, 4፤ ማር. 3:29፤ 14:21፤ 2 ቆሮ. 7:10, 11)

  3. ሉቃስ 22:54-71ን አንብብ።

    ኢየሱስ አልፎ በተሰጠበትና በተያዘበት ሌሊት ጴጥሮስ ይህን ሰው አላውቀውም ብሎ መካዱ ለእኛ ምን ያስተምረናል? (ሉቃስ 22:60-62፤ ማቴ. 26:31-35፤ 1 ቆሮ. 10:12)

  4. ሉቃስ 23:1-49ን አንብብ።

    ኢየሱስ ፍትሕ ቢጓደልበትም ምን ምላሽ ሰጠ? እኛስ ከዚህ ምን እንማራለን? (ሉቃስ 23:33, 34፤ ሮሜ 12:17-19፤ 1 ጴጥ. 2:23)

  5. ዮሐንስ 18:12-40ን አንብብ።

    ጴጥሮስ ለጊዜው በሰው ፍርሃት ተሽመድምዶ የነበረ ቢሆንም ከዚያ አገግሞ የታወቀ ሐዋርያ ለመሆን መቻሉ ምን ያሳያል? (ዮሐ. 18:25-27፤ 1 ቆሮ. 4:2፤ 1 ጴጥ. 3:14, 15፤ 5:8, 9)

  6. ዮሐንስ 19:1-30ን አንብብ።

    1. (ሀ) ኢየሱስ ለቁሳዊ ነገሮች ምን ዓይነት ሚዛናዊ አመለካከት ነበረው? (ዮሐ. 2:1, 2, 9, 10፤ 19:23, 24፤ ማቴ. 6:31, 32፤ 8:20)

    2. (ለ) ኢየሱስ ሲሞት የተናገራቸው ቃላት የይሖዋን ሉዓላዊነት ደግፎ በመቆሙ የተሰማውን የድል አድራጊነት ስሜት የሚያንጸባርቁት እንዴት ነው? (ዮሐ. 16:33፤ 19:30፤ 2 ጴጥ. 3:14፤ 1 ዮሐ. 5:4)

ታሪክ 102

ኢየሱስ ተነሳ

  1. በሥዕሉ ላይ የምትታየው ሴት ማን ነች? ሁለቱ ሰዎች እነማን ናቸው? ያሉትስ የት ነው?

  2. ጲላጦስ ካህናቱን የኢየሱስን መቃብር የሚጠብቁ ወታደሮች እንዲልኩ የነገራቸው ለምንድን ነው?

  3. ኢየሱስ በሞተ በሦስተኛው ቀን ማለዳ አንድ መልአክ ምን አደረገ? ካህናቱስ ምን አደረጉ?

  4. የኢየሱስን መቃብር ለማየት የሄዱ አንዳንድ ሴቶች መቃብሩን ሲያዩ የተገረሙት ለምንድን ነው?

  5. ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ ኢየሱስ መቃብር ሮጠው የሄዱት ለምንድን ነው? በስፍራው ሲደርሱስ ምን አገኙ?

  6. የኢየሱስ አካል ምን ሆነ? ኢየሱስ ከሞት መነሳቱን ለደቀ መዛሙርቱ ለማሳየት ሲል ምን አደረገ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ማቴዎስ 27:62-66 እና 28:1-15ን አንብብ።

    ኢየሱስ ከሞት በተነሳ ጊዜ የካህናት አለቆች፣ ፈሪሳውያንና ሽማግሌዎች በመንፈስ ቅዱስ ላይ ኃጢአት የሠሩት እንዴት ነው? (ማቴ. 12:24, 31, 32፤ 28:11-15)

  2. ሉቃስ 24:1-12ን አንብብ።

    ስለ ኢየሱስ ትንሣኤ የሚገልጸው ዘገባ ይሖዋ ሴቶችን እምነት የሚጣልባቸው ምሥክሮች አድርጎ እንደሚቆጥራቸው የሚያሳየው እንዴት ነው? (ሉቃስ 24:4, 9, 10፤ ማቴ. 28:1-7)

  3. ዮሐንስ 20:1-12ን አንብብ።

    ዮሐንስ 20:8, 9 የአንድን የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት አፈጻጸም ሙሉ በሙሉ መረዳት ቢያዳግተን ነገሩን በትዕግሥት የመጠባበቅን አስፈላጊነት እንድንገነዘብ የሚረዳን እንዴት ነው? (ምሳሌ 4:18፤ ማቴ. 17:22, 23፤ ሉቃስ 24:5-8፤ ዮሐ. 16:12)

ታሪክ 103

በተዘጋ ክፍል ውስጥ

  1. ማርያም አትክልተኛ ነው ብላ ላሰበችው ሰው ምን አለችው? ይሁን እንጂ ይህ ሰው ኢየሱስ መሆኑን ለመገንዘብ ያስቻላት ምንድን ነው?

  2. ኤማሁስ ወደሚባል መንደር ይጓዙ የነበሩት ሁለት ደቀ መዛሙርት ምን ገጠማቸው?

  3. ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ኢየሱስን እንዳዩት ለሐዋርያቱ በተናገሩ ጊዜ ምን አስደናቂ ነገር ተፈጸመ?

  4. ኢየሱስ ለተከታዮቹ የተገለጠላቸው ስንት ጊዜ ነው?

  5. ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን እንዳዩት ቶማስ ሲሰማ ምን አለ? ከስምንት ቀናት በኋላስ ምን ተከሰተ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዮሐንስ 20:11-29ን አንብብ።

    ኢየሱስ በ⁠ዮሐንስ 20:23 ላይ ሰዎች ኃጢአትን ይቅር የማለት ሥልጣን እንዳላቸው መናገሩ ነበር? አብራራ። (መዝ. 49:2, 7፤ ኢሳ. 55:7፤ 1 ጢሞ. 2:5, 6፤ 1 ዮሐ. 2:1, 2)

  2. ሉቃስ 24:13-43ን አንብብ።

    የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን እንዲቀበል ልባችንን ልናዘጋጅ የምንችለው እንዴት ነው? (ሉቃስ 24:32, 33፤ ዕዝራ 7:10፤ ማቴ. 5:3፤ ሥራ 16:14፤ ዕብ. 5:11-14)

ታሪክ 104

ኢየሱስ ወደ ሰማይ ተመለሰ

  1. በአንድ ወቅት ኢየሱስን ስንት ደቀ መዛሙርት አዩት? በዚያን ጊዜስ ስለ የትኛው ጉዳይ ነገራቸው?

  2. የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? ኢየሱስ ንጉሥ ሆኖ ለሺህ ዓመት በሚገዛበት ጊዜ በምድር ላይ ምን ዓይነት ሁኔታ ይኖራል?

  3. ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እየተገለጠላቸው የቆየው ለስንት ቀናት ነበር? ከዚያስ ምን የሚያደርግበት ጊዜ ደረሰ?

  4. ከደቀ መዛሙርቱ ተለይቶ ከመሄዱ በፊት ምን እንዲያደርጉ ነገራቸው?

  5. በሥዕሉ ላይ ምን ይታይሃል? ኢየሱስ ከዓይን የተሰወረው እንዴት ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. አንደኛ ቆሮንቶስ 15:3-8ን አንብብ።

    ሐዋርያው ጳውሎስ የኢየሱስን ትንሣኤ በተመለከተ በእርግጠኝነት ሊናገር የቻለው እንዴት ነው? በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያኖችም ስለ የትኞቹ ጉዳዮች በእርግጠኝነት መናገር ይችላሉ? (1 ቆሮ. 15:4, 7, 8፤ ኢሳ. 2:2, 3፤ ማቴ. 24:14፤ 2 ጢሞ. 3:1-5)

  2. የሐዋርያት ሥራ 1:1-11ን አንብብ።

    በሐዋርያት ሥራ 1:8 ላይ እንደተተነበየው የስብከቱ ሥራ ምን ያህል ተሰራጭቷል? (ሥራ 6:7፤ 9:31፤ 11:19-21፤ ቈላ. 1:23)

ታሪክ 105

በኢየሩሳሌም ሆኖ መጠባበቅ

  1. በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው በኢየሩሳሌም ሲጠባበቁ የነበሩት የኢየሱስ ተከታዮች ምን አጋጠማቸው?

  2. ወደ ኢየሩሳሌም የመጡ ጎብኚዎች ምን አስገራሚ ነገር አጋጠማቸው?

  3. ጴጥሮስ ለሕዝቡ ምን ማብራሪያ ሰጠ?

  4. ሕዝቡ ጴጥሮስን ካዳመጡት በኋላ ምን ተሰማቸው? እርሱስ ምን እንዲያደርጉ ነገራቸው?

  5. በ33 ከክርስቶስ ልደት በኋላ በዋለው የጰንጠቆስጤ ዕለት ስንት ሰዎች ተጠመቁ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. የሐዋርያት ሥራ 2:1-47ን አንብብ።

    1. (ሀ) በሐዋርያት ሥራ 2:23, 36 ላይ የሚገኙት የጴጥሮስ ቃላት ለኢየሱስ ሞት ተጠያቂ የሚሆነው መላው የአይሁድ ብሔር መሆኑን የሚያመለክቱት እንዴት ነው? (1 ተሰ. 2:14, 15)

    2. (ለ) ጴጥሮስ ከቅዱሳን መጻሕፍት እየጠቀሰ በማስረዳት ረገድ ጥሩ ምሳሌ የተወው እንዴት ነው? (ሥራ 2:16, 17, 29, 31, 36, 39፤ ቈላ. 4:6)

    3. (ሐ) ጴጥሮስ ኢየሱስ ለእርሱ እንደሚሰጠው ቃል ከገባለት ‘የመንግሥተ ሰማይ መክፈቻዎች’ የመጀመሪያውን የተጠቀመው እንዴት ነው? (ሥራ 2:14, 22-24, 37, 38፤ ማቴ. 16:19)

ታሪክ 106

ከእስር ቤት መውጣት

  1. ጴጥሮስና ዮሐንስ አንድ ቀን ከሰዓት በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ሲገቡ ምን አጋጠማቸው?

  2. ጴጥሮስ የአካል ጉዳተኛ ለነበረው ሰው ምን አለው? ጴጥሮስ ለዚህ ሰው ከገንዘብ የበለጠ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሰጠው?

  3. የሃይማኖት መሪዎቹ የተናደዱት ለምንድን ነው? ጴጥሮስንና ዮሐንስን ምን አደረጓቸው?

  4. ጴጥሮስ ለሃይማኖት መሪዎቹ ምን አላቸው? ሐዋርያቱ ምን ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው?

  5. የሃይማኖት መሪዎቹ የቀኑት ለምን ነበር? ያም ሆኖ ሐዋርያቱ ለሁለተኛ ጊዜ ሲታሰሩ ምን አጋጠማቸው?

  6. ሐዋርያቱ በሳንሄድሪን ሸንጎ ፊት በቀረቡ ጊዜ ምን መልስ ሰጡ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. የሐዋርያት ሥራ 3:1-10ን አንብብ።

    በዛሬው ጊዜ ተአምራት የመሥራት ኃይል ባይሰጠንም እንኳ በሐዋርያት ሥራ 3:6 ላይ ያሉት የጴጥሮስ ቃላት የመንግሥቱን መልእክት ዋጋማነት እንድናደንቅ የሚረዱን እንዴት ነው? (ዮሐ. 17:3፤ 2 ቆሮ. 5:18-20፤ ፊልጵ. 3:8)

  2. የሐዋርያት ሥራ 4:1-31ን አንብብ።

    በአገልግሎታችን ወቅት ተቃውሞ ሲያጋጥመን በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩትን ክርስቲያን ወንድሞቻችንን መኮረጅ የሚገባን በምን መንገድ ነው? (ሥራ 4:29, 31፤ ኤፌ. 6:18-20፤ 1 ተሰ. 2:2)

  3. የሐዋርያት ሥራ 5:17-42ን አንብብ።

    ጥንትም ሆነ ዛሬ አንዳንድ የይሖዋ ምሥክር ያልሆኑ ሰዎች የስብከቱን ሥራ በሚመለከት ምክንያታዊነት ያሳዩት እንዴት ነው? (ሥራ 5:34-39)

ታሪክ 107

እስጢፋኖስ በድንጋይ ተወገረ

  1. እስጢፋኖስ ማን ነው? አምላክ እስጢፋኖስን ምን እንዲፈጽም ረድቶታል?

  2. እስጢፋኖስ የሃይማኖት መሪዎቹ በጣም የተናደዱበትን ምን ነገር ተናገረ?

  3. ሰዎቹ እስጢፋኖስን ከከተማው ውጪ እየጎተቱ ከወሰዱት በኋላ ምን አደረጉት?

  4. በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው፣ እስጢፋኖስን የገደሉት ሰዎች ልብሳቸውን ካስቀመጡበት ቦታ አጠገብ የቆመው ማን ነው?

  5. እስጢፋኖስ ከመሞቱ በፊት ምን ብሎ ወደ ይሖዋ ጸለየ?

  6. አንድ ሰው መጥፎ ነገር ሲፈጽምብን እኛም እንደ እስጢፋኖስ ምን ማድረግ ይኖርብናል?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. የሐዋርያት ሥራ 6:8-15ን አንብብ።

    የሃይማኖት መሪዎች የይሖዋ ምሥክሮችን የስብከት ሥራ ለማስቆም ምን ዓይነት ማታለያዎችን ተጠቅመዋል? (ሥራ 6:9, 11, 13)

  2. የሐዋርያት ሥራ 7:1-60ን አንብብ።

    1. (ሀ) እስጢፋኖስ በሳንሄድሪን ሸንጎ ፊት ቀርቦ ለወንጌሉ በሚከራከርበት ጊዜ ውጤታማ እንዲሆን የረዳው ምንድን ነው? እኛስ ከእርሱ ምሳሌ ምን ልንማር እንችላለን? (ሥራ 7:51-53፤ ሮሜ 15:4፤ 2 ጢሞ. 3:14-17፤ 1 ጴጥ. 3:15)

    2. (ለ) ሥራችንን የሚቃወሙ ሰዎችን በተመለከተ ምን ዓይነት አስተሳሰብ ለማዳበር መጣር ይኖርብናል? (ሥራ 7:58-60፤ ማቴ. 5:44፤ ሉቃስ 23:33, 34)

ታሪክ 108

ወደ ደማስቆ በሚወስደው መንገድ ላይ

  1. እስጢፋኖስ ከተገደለ በኋላ ሳውል ምን አደረገ?

  2. ሳውል ወደ ደማስቆ በመሄድ ላይ ሳለ ምን የሚያስገርም ነገር አጋጠመው?

  3. ኢየሱስ ሳውልን ምን እንዲያደርግ ነገረው?

  4. ኢየሱስ ለሐናንያ ምን ትእዛዝ ሰጠው? ሳውል እንደገና ማየት የቻለው እንዴት ነው?

  5. ሳውል የሚታወቀው በየትኛው ስሙ ነው? ምንስ አከናውኗል?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. የሐዋርያት ሥራ 8:1-4ን አንብብ።

    አዲስ የተቋቋመውን የክርስቲያን ጉባኤ የመታው የስደት ማዕበል የክርስትናን እምነት ለማስፋፋት ያገለገለው እንዴት ነው? በዘመናችንስ ምን ተመሳሳይ የሆነ ድርጊት ተፈጽሟል? (ሥራ 8:4፤ ኢሳ. 54:17)

  2. የሐዋርያት ሥራ 9:1-20ን አንብብ።

    ኢየሱስ፣ ጳውሎስ እንዲያከናውነው ሊሰጠው ያሰበው ሦስት ዘርፎች ያሉት ተልእኮ ምን ነበር? (ሥራ 9:15፤ 13:5፤ 26:1፤ 27:24፤ ሮሜ 11:13)

  3. የሐዋርያት ሥራ 22:6-16ን አንብብ።

    ሐናንያን መምሰል የምንችለው እንዴት ነው? ይህስ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (ሥራ 22:12፤ 1 ጢሞ. 3:7፤ 1 ጴጥ. 1:14-16፤ 2:12)

  4. የሐዋርያት ሥራ 26:8-20ን አንብብ።

    ሳውል ወደ ክርስትና መለወጡ፣ በዛሬው ጊዜ የማያምኑ የትዳር ጓደኞች ያሏቸው ክርስቲያኖችን የሚያበረታታቸው እንዴት ነው? (ሥራ 26:11፤ 1 ጢሞ. 1:14-16፤ 2 ጢሞ. 4:2፤ 1 ጴጥ. 3:1-3)

ታሪክ 109

ጴጥሮስ ወደ ቆርኔሌዎስ ቤት ሄደ

  1. በሥዕሉ ላይ ተንበርክኮ የሚታየው ይህ ሰው ማን ነው?

  2. አንድ መልአክ ለቆርኔሌዎስ ምን አለው?

  3. ጴጥሮስ በኢዮጴ በሚገኘው በስምዖን ቤት ሰገነት ላይ ሳለ አምላክ ምን አሳየው?

  4. ጴጥሮስ ቆርኔሌዎስን ተንበርክኮ ሊሰግድለትና ሊያመልከው እንደማይገባ የነገረው ለምንድን ነው?

  5. ከጴጥሮስ ጋር የነበሩት አይሁዳውያን ደቀ መዛሙርት የተገረሙት ለምንድን ነው?

  6. የጴጥሮስ ወደ ቆርኔሌዎስ ቤት መሄድ ምን ጠቃሚ ትምህርቶችን ይሰጠናል?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. የሐዋርያት ሥራ 10:1-48ን አንብብ።

    በሐዋርያት ሥራ 10:42 ላይ የሚገኙት የጴጥሮስ ቃላት የመንግሥቱን ምሥራች ስለ መስበኩ ሥራ ምን ያመለክታሉ? (ማቴ. 28:19፤ ማር. 13:10፤ ሥራ 1:8)

  2. የሐዋርያት ሥራ 11:1-18ን አንብብ።

    ጴጥሮስ፣ ይሖዋ አሕዛብን በተመለከተ የሰጠው መመሪያ ግልጽ በሆነለት ጊዜ ምን ዓይነት ዝንባሌ አሳይቷል? እኛስ የእርሱን ምሳሌ ልንኮርጅ የምንችለው እንዴት ነው? (ሥራ 11:17, 18፤ 2 ቆሮ. 10:5፤ ኤፌ. 5:17)

ታሪክ 110

የጳውሎስ አዲስ ረዳት የሆነው ጢሞቴዎስ

  1. በሥዕሉ ላይ የሚታየው ወጣት ማን ነው? የሚኖረው የት ነው? የእናቱና የአያቱ ስምስ ማን ይባላል?

  2. ጳውሎስና ሲላስ ራቅ ብለው በሚገኙ ቦታዎች ለሚኖሩ ሰዎች ለመስበክ በሚሄዱበት ጊዜ ጢሞቴዎስ አብሯቸው መሄድ ይፈልግ እንደሆነ ጳውሎስ ሲጠይቀው ምላሹ ምን ነበር?

  3. የኢየሱስ ተከታዮች ለመጀመሪያ ጊዜ ክርስቲያን ተብለው የተጠሩበት ቦታ የት ነው?

  4. ጳውሎስ፣ ሲላስና ጢሞቴዎስ ከልስጥራን ከሄዱ በኋላ የጎበኟቸው አንዳንድ ከተሞች የትኞቹ ናቸው?

  5. ጢሞቴዎስ ጳውሎስን የረዳው እንዴት ነው? በዛሬው ጊዜ ያሉ ወጣቶችስ ራሳቸውን ምን ብለው መጠየቅ ይኖርባቸዋል?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. የሐዋርያት ሥራ 9:19-30ን አንብብ።

    ሐዋርያው ጳውሎስ ምሥራቹን የሚቃወሙ ሰዎች ባጋጠሙት ጊዜ ብልህነቱን ያሳየው እንዴት ነው? (ሥራ 9:22-25, 29, 30፤ ማቴ. 10:16)

  2. የሐዋርያት ሥራ 11:19-26ን አንብብ።

    በሐዋርያት ሥራ 11:19-21, 26 ላይ የተመዘገበው ታሪክ የስብከቱን ሥራ የሚመራው የይሖዋ መንፈስ እንደነበር የሚያሳየው እንዴት ነው?

  3. የሐዋርያት ሥራ 13:13-16, 42-52ን አንብብ።

    ደቀ መዛሙርቱ የሚደርስባቸው ተቃውሞ ተስፋ እንዲያስቆርጣቸው እንዳልፈቀዱለት የሐዋርያት ሥራ 13:51, 52 የሚያሳየው እንዴት ነው? (ማቴ. 10:14፤ ሥራ 18:6፤ 1 ጴጥ. 4:14)

  4. የሐዋርያት ሥራ 14:1-6, 19-28ን አንብብ።

    “ላመኑበት ጌታ ዐደራ ሰጧቸው” የሚለው አባባል አዳዲሶችን በምንረዳበት ጊዜ ከመጠን በላይ መጨነቅ እንደሌለብን እንድንገነዘብ የሚያስችለን እንዴት ነው? (ሥራ 14:21-23፤ 20:32፤ ዮሐ. 6:44)

  5. የሐዋርያት ሥራ 16:1-5ን አንብብ።

    ጢሞቴዎስ ለመገረዝ ፈቃደኛ መሆኑ ‘ስለ ወንጌል ሲባል ሁሉን የማድረግን’ አስፈላጊነት ጎላ አድርጎ የሚገልጸው እንዴት ነው? (ሥራ 16:3፤ 1 ቆሮ. 9:23፤ 1 ተሰ. 2:8)

  6. የሐዋርያት ሥራ 18:1-11, 18-22ን አንብብ።

    ለስብከቱ ሥራ አመራር ለመስጠት ኢየሱስ ጣልቃ መግባቱን በሚመለከት የሐዋርያት ሥራ 18:9, 10 ምን ይላል? ይህስ በዛሬው ጊዜ ስለምን ነገር እርግጠኞች እንድንሆን ያደርገናል? (ማቴ. 28:20)

ታሪክ 111

ያንቀላፋው ልጅ

  1. በሥዕሉ ላይ መሬት ላይ ተኝቶ የሚታየው ልጅ ማን ነው? ምን ሆኗል?

  2. ጳውሎስ ልጁ መሞቱን ባየ ጊዜ ምን አደረገ?

  3. ጳውሎስ፣ ጢሞቴዎስና ከእነርሱ ጋር የሚጓዙት ሰዎች የሚሄዱት ወዴት ነው? የተሳፈሩባት ጀልባ በሚሊጢን በቆመች ጊዜ ጳውሎስ ምን አደረገ?

  4. ነቢዩ አጋቦስ ለጳውሎስ ምን ማስጠንቀቂያ ሰጠው? ልክ ነቢዩ እንደተናገረው ሁሉ ምን ተፈጸመ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. የሐዋርያት ሥራ 20:7-38ን አንብብ።

    1. (ሀ) በሐዋርያት ሥራ 20:26, 27 ላይ ተመዝግበው በሚገኙት የጳውሎስ ቃላት መሠረት “ከሰው ሁሉ ደም ንጹሕ” መሆን የምንችለው እንዴት ነው? (ሕዝ. 33:8፤ ሥራ 18:6, 7)

    2. (ለ) ሽማግሌዎች በሚያስተምሩበት ጊዜ ‘በታመነው ቃል መጽናት’ የሚኖርባቸው ለምንድን ነው? (ሥራ 20:17, 29, 30፤ ቲቶ 1:7-9፤ 2 ጢሞ. 1:13)

  2. የሐዋርያት ሥራ 26:24-32ን አንብብ።

    ጳውሎስ ሮማዊ ዜግነቱን ከኢየሱስ የተቀበለውን የስብከት ተልእኮ ለመፈጸም የተጠቀመበት እንዴት ነው? (ሥራ 9:15፤ 16:37, 38፤ 25:11, 12፤ 26:32፤ ሉቃስ 21:12, 13)

ታሪክ 112

አንዲት መርከብ በአንድ ደሴት አጠገብ ተሰበረች

  1. ጳውሎስ የተሳፈረባት ጀልባ በቀርጤስ ደሴት አጠገብ ስታልፍ ምን ሆነች?

  2. ጳውሎስ በመርከቧ ውስጥ ለነበሩት ሰዎች ምን አላቸው?

  3. መርከቧ የተሰባበረችው እንዴት ነው?

  4. ኃላፊ የነበረው የመቶ አለቃ ምን ትእዛዝ ሰጠ? ወደ ባሕሩ ዳርቻ በደህና የደረሱት ሰዎች ምን ያህል ነበሩ?

  5. ያረፉባት ደሴት ስሟ ማን ነው? የአየሩ ጠባይ ሲስተካከል ጳውሎስ ምን ተደረገ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. የሐዋርያት ሥራ 27:1-44ን አንብብ።

    ጳውሎስ ወደ ሮም ያደረገውን ጉዞ ስናነብ መጽሐፍ ቅዱስ ትክክለኛ ስለመሆኑ ያለን እምነት ይበልጥ የሚጠናከረው እንዴት ነው? (ሥራ 27:16-19, 27-32፤ ሉቃስ 1:3፤ 2 ጢሞ. 3:16, 17)

  2. የሐዋርያት ሥራ 28:1-14ን አንብብ።

    አማኝ ያልነበሩት የመላጥያ ደሴት ነዋሪዎች ለጳውሎስና በተሰበረችው መርከብ ላይ አብረውት ይጓዙ ለነበሩት ሰዎች “የሚያስገርም ደግነት” ካሳዩአቸው፣ ክርስቲያኖችስ ምን ለማድረግ መገፋፋት ይኖርባቸዋል? በተለይም በምን መንገድ እንዲህ ማድረግ ይችላሉ? (ሥራ 28:1, 2፤ ዕብ. 13:1, 2፤ 1 ጴጥ. 4:9)

ታሪክ 113

ጳውሎስ በሮም

  1. ጳውሎስ በሮም ታስሮ ሳለ ለእነማን ሰብኳል?

  2. በሥዕሉ ላይ ጠረጴዛ ላይ አስደግፎ ሲጽፍ የሚታየው ጳውሎስን ሊጠይቅ የመጣ ሰው ማን ነው? እርሱስ ለጳውሎስ ምን እያደረገለት ነው?

  3. አፍሮዲጡ ማን ነበር? ወደ ፊልጵስዩስ ሲመለስ ምን ይዞ ሄደ?

  4. ጳውሎስ የቅርብ ጓደኛው ለነበረው ለፊልሞና ደብዳቤ የጻፈው ለምን ነበር?

  5. ጳውሎስ ከእስር ቤት ሲፈታ ምን አደረገ? ቆየት ብሎስ ምን ደረሰበት?

  6. ይሖዋ የመጨረሻዎቹን የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት ለማጻፍ የተጠቀመው በማን ነው? የራእይ መጽሐፍ ስለምን ነገር ይነግረናል?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. የሐዋርያት ሥራ 28:16-31 እና ፊልጵስዩስ 1:13ን አንብብ።

    ጳውሎስ በሮም ታስሮ ሳለ ጊዜውን የተጠቀመበት እንዴት ነው? የማይናወጥ እምነት ማሳየቱ በክርስቲያን ጉባኤ ላይ ምን ውጤት ነበረው? (ሥራ 28:23, 30፤ ፊልጵ. 1:14)

  2. ፊልጵስዩስ 2:19-30ን አንብብ።

    ጳውሎስ፣ ስለ ጢሞቴዎስና ስለ አፍሮዲጡ አድናቆቱን የገለጸው እንዴት ነው? እኛስ የጳውሎስን ምሳሌ መኮረጅ የምንችለው እንዴት ነው? (ፊልጵ. 2:20, 22, 25, 29, 30፤ 1 ቆሮ. 16:18፤ 1 ተሰ. 5:12, 13)

  3. ፊልሞና 1-25ን አንብብ።

    1. (ሀ) ጳውሎስ ለፊልሞና ተገቢውን ነገር እንዲያደርግ ያሳሰበው ምንን መሠረት በማድረግ ነው? ይህስ በዛሬው ጊዜ ላሉ ሽማግሌዎች እንደ መመሪያ ሆኖ የሚያገለግለው እንዴት ነው? (ፊል. 9፤ 2 ቆሮ. 8:8፤ ገላ. 5:13)

    2. (ለ) በ⁠ፊልሞና ቁጥር 13 እና 14 ላይ የሚገኘው የጳውሎስ አነጋገር በጉባኤው ውስጥ ያሉትን የሌሎች ክርስቲያኖች ሕሊና ያከብር እንደነበር የሚያሳየው እንዴት ነው? (1 ቆሮ. 8:7, 13፤ 10:31-33)

  4. ሁለተኛ ጢሞቴዎስ 4:7-9ን አንብብ።

    እኛም ልክ እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ እስከ ፍጻሜው ድረስ በታማኝነት ከጸናን ይሖዋ ወሮታ እንደሚከፍለን እርግጠኞች መሆን የምንችለው እንዴት ነው? (ማቴ. 24:13፤ ዕብ. 6:10)

ታሪክ 114

የክፋት ሁሉ ፍጻሜ

  1. መጽሐፍ ቅዱስ በሰማይ ስላሉ ፈረሶች የሚናገረው ለምንድን ነው?

  2. አምላክ በምድር ላይ ካሉ ክፉ ሰዎች ጋር የሚያደርገው ጦርነት ምን ይባላል? የዚህ ጦርነት ዓላማስ ምንድን ነው?

  3. በሥዕሉ ላይ እንደምትመለከተው ጦርነቱን ከፊት እየመራ የሚዋጋው ማን ነው? የንጉሥ ዘውድ የጫነውስ ለምንድን ነው? በእጁ የያዘው ሰይፍ ትርጉም ምንድን ነው?

  4. በታሪክ 10፣ 15 እና 33 ላይ የተማርናቸውን ታሪኮች ስናስታውስ አምላክ ክፉ ሰዎችን የሚያጠፋ መሆኑ ሊያስደንቀን የማይገባው ለምንድን ነው?

  5. ክፉ ሰዎች አምላክን እናመልካለን ቢሉም ታሪክ 36 እና 76 ከጥፋት እንደማያመልጡ የሚያሳዩት እንዴት ነው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ራእይ 19:11-16ን አንብብ።

    1. (ሀ) የነጩ ፈረስ ጋላቢ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ቅዱሳን መጻሕፍት ግልጽ የሚያደርጉት እንዴት ነው? (ራእይ 1:5፤ 3:14፤ 19:11፤ ኢሳ. 11:4)

    2. (ለ) በኢየሱስ ልብስ ላይ ደም የተረጨ መሆኑ የሚቀዳጀው ድል ወሳኝና የተሟላ መሆኑን የሚያረጋግጠው እንዴት ነው? (ራእይ 14:18-20፤ 19:13)

    3. (ሐ) ኢየሱስ በነጩ ፈረስ ላይ ሆኖ በሚዋጋበት ጊዜ እነማን ጭምር አብረውት ይዘምታሉ? (ራእይ 12:7፤ 19:14፤ ማቴ. 25:31, 32)

ታሪክ 115

በምድር ላይ የምትቋቋም አዲስ ገነት

  1. መጽሐፍ ቅዱስ ገነት በምትሆነው ምድር ላይ ምን ዓይነት አስደሳች ሕይወት እንደምናገኝ ያመለክታል?

  2. መጽሐፍ ቅዱስ በገነት ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ምን ተስፋ ይዞላቸዋል?

  3. ኢየሱስ ይህን አስደናቂ ለውጥ የሚያመጣው መቼ ነው?

  4. ኢየሱስ የአምላክ መንግሥት ንጉሥ በሚሆንበት ጊዜ ምን እንደሚያከናውን ለማሳየት በምድር ሳለ ምን አድርጎ ነበር?

  5. ኢየሱስና ተባባሪ ገዥዎቹ ከሰማይ ሆነው ምድርን በሚያስተዳድሩበት ጊዜ ምን ያደርጋሉ?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ራእይ 5:9, 10ን አንብብ።

    በሺህ ዓመቱ ግዛት ወቅት በምድር ላይ የሚገዙት ነገሥታትና ካህናት ርኅሩኅና መሐሪ እንደሚሆኑ እርግጠኞች መሆን የምንችለው ለምንድን ነው? (ኤፌ. 4:20-24፤ 1 ጴጥ. 1:7፤ 3:8፤ 5:6-10)

  2. ራእይ 14:1-3ን አንብብ።

    በ144,000ዎቹ ግንባር ላይ የበጉና የአባቱ ስም መጻፉ ምን ያመለክታል? (1 ቆሮ. 3:23፤ 2 ጢሞ. 2:19፤ ራእይ 3:12)

ታሪክ 116

ለዘላለም መኖር የምንችለው እንዴት ነው?

  1. ለዘላለም ለመኖር እንድንችል ምን ማወቅ ይኖርብናል?

  2. በሥዕሉ ላይ የምናያቸው ትንሿ ልጅና ጓደኞቿ እንደሚያደርጉት ስለ ይሖዋ አምላክና ስለ ኢየሱስ መማር የምንችለው እንዴት ነው?

  3. በሥዕሉ ላይ ምን ሌላ መጽሐፍ ታያለህ? አዘውትረን ልናነበው የሚገባንስ ለምንድን ነው?

  4. የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ስለ ይሖዋና ስለ ኢየሱስ ከመማር በተጨማሪ ምን ያስፈልጋል?

  5. ከታሪክ 69 ምን ትምህርት እናገኛለን?

  6. በታሪክ 55 ላይ ትንሹ ሳሙኤል የተወልን ምሳሌ ምን ያሳየናል?

  7. የኢየሱስ ክርስቶስን ምሳሌ ልንከተል የምንችለው እንዴት ነው? የእርሱን ምሳሌ ከተከተልን ለወደፊቱ ምን ማድረግ እንችላለን?

ተጨማሪ ጥያቄዎች:-

  1. ዮሐንስ 17:3ን አንብብ።

    ስለ ይሖዋ አምላክና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ማወቅ እውነትን እንዲሁ በቃል ከማጥናት ያለፈ ነገር መሆኑን ቅዱሳን መጻሕፍት የሚያሳዩት እንዴት ነው? (ማቴ. 7:21፤ ያዕ. 2:18-20፤ 1 ዮሐ. 2:17)

  2. መዝሙር 145:1-21ን አንብብ።

    1. (ሀ) ይሖዋን ከምናመሰግንባቸው ብዙ ምክንያቶች ውስጥ አንዳንዶቹ ምንድን ናቸው? (መዝ. 145:8-11፤ ራእይ 4:11)

    2. (ለ) ይሖዋ “ለሁሉ ቸር” የሆነው እንዴት ነው? ይህስ ወደ እርሱ ይበልጥ እንድንቀርብ የሚያደርገን እንዴት ነው? (መዝ. 145:9፤ ማቴ. 5:43-45)

    3. (ሐ) ይሖዋን ከልባችን የምንወደው ከሆነ ምን ለማድረግ እንገፋፋለን? (መዝ. 119:171, 172, 175፤ 145:11, 12, 21)