በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሰማይ

ሰማይ

ፍቺ:- ይሖዋ አምላክና ታማኝ መንፈሳዊ ፍጥረታት የሚኖሩበት ስፍራ። ከሰው እይታ የተሰወረ ስፍራ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ “ሰማይ” ወይም “ሰማያት” የሚለውን ቃል በተለያዩ ትርጉሞች ይጠቀምበታል። ለምሳሌ አምላክን ራሱን፣ የእርሱን ታማኝ መንፈሳዊ ፍጥረታት ድርጅት፣ መለኮታዊ ሞገስ ማግኘትን፣ መሬትን ሳይጨምር ግዑዙን አጽናፈ ዓለም፣ ምድርን የከበባትን ጠፈር፣ በሰይጣን የሚገዙትን ሰብዓዊ መንግሥታት፣ ኢየሱስ ክርስቶስና ተባባሪ ወራሾቹ የሚገዙበትን ጻድቅና አዲስ ሰማያዊ መንግሥት ለማመልከት ተሠርቶበታል።

ሁላችንም ሰው ሆነን ከመወለዳችን በፊት በመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ እንኖር ነበርን?

ዮሐ. 8:23:- “[ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ አለ:-] እናንተ ከታች ናችሁ፣ እኔ ከላይ ነኝ። እናንተ ከዚህ ዓለም ናችሁ፣ እኔ ከዚህ ዓለም አይደለሁም።” (ኢየሱስ ከመንፈሣዊው ዓለም የመጣ ሲሆን ሌሎች ሰዎች ግን ኢየሱስ እንደተናገረው ከመንፈሣዊው ዓለም የመጡ አይደሉም።)

ሮሜ 9:10–12:- “ርብቃ ደግሞ . . . በፀነሰች ጊዜ፣ ልጆቹ ገና ሳይወለዱ፣ በጎ ወይም ክፉ ምንም ሳያደርጉ፣ ከጠሪው እንጂ ከሥራ ሳይሆን በምርጫ የሚሆን የእግዚአብሔር አሳብ ይጸና ዘንድ፣ ለእርስዋ:- ታላቁ ለታናሹ ይገዛል ተባለላት።” (መንትዮቹ ያዕቆብና ዔሣው አስቀድሞ በመንፈሳዊ ዓለም ይኖሩ ከነበሩ ስለ ጠባያቸው የሚገልጽ የተመዘገበ ነገር አይኖራቸውም ነበርን? ሰዎች ሆነው ከመወለዳቸው በፊት ስላደረጉት ነገር የሚገልጽ ምንም ዓይነት ታሪክ አልነበራቸውም።)

ጥሩ ሰዎች ሁሉ ወደ ሰማይ ይሄዳሉን?

ሥራ 2:34:- “ዳዊት [መጽሐፍ ቅዱስ ‘ለይሖዋ ልብ የተስማማ’ ብሎ የሚጠራው ሰው] ወደ ሰማይ አልወጣም።”

ማቴ. 11:11:- “እውነት እላችኋለሁ፣ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፤ በመንግሥተ ሰማያት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።” (ስለዚህ ዮሐንስ በሞተ ጊዜ ወደ ሰማይ አልሄደም።)

መዝ. 37:9, 11, 29:- “ክፉ አድራጊዎች ይጠፋሉና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን እነርሱ ምድርን ይወርሳሉ። . . . ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፣ በብዙም ሰላም ደስ ይላቸዋል። ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፣ በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ።”

አዳም ኃጢአት ባይሠራ ኖሮ በመጨረሻ ወደ ሰማይ ይሄድ ነበርን?

ዘፍ. 1:26:- “እግዚአብሔርም አለ:- ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፣ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፣ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።” (አምላክ ለአዳም የነበረው ዓላማ ምድርንና እንስሳትን እንዲንከባከብ ነበር። ወደ ሰማይ እንደሚሄድ የተነገረ አንድም ነገር የለም።)

ዘፍ. 2:16, 17:- “እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው:- ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።” (ሰው አንድ ቀን እንዲሞት የይሖዋ አምላክ ዓላማ አልነበረም። እዚህ ላይ የተጠቀሰው የአምላክ ትእዛዝ የሰው ልጅ ወደሞት የሚመራውን መንገድ እንዳይከተል ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ያመለክታል። ሞት ላለመታዘዝ የሚሰጥ ቅጣት እንጂ ወደተሻለ የሰማይ ሕይወት የሚያስገባ በር አይደለም። ታዛዥ መሆን አምላክ ለሰው ልጆች በሰጣት ገነት ላይ ለዘላለም የመኖርን ሽልማት ያስገኝ ነበር። በተጨማሪ ኢሳይያስ 45:18⁠ን ተመልከት።)

አንድ ሰው እውነተኛ ደስታ ያለበት ሕይወት እንዲያገኝ ወደ ሰማይ መሄድ ይኖርበታልን?

መዝ. 37:11:- “ገሮች . . . ምድርን ይወርሳሉ፣ በብዙም ሰላም ደስ ይላቸዋል።”

ራእይ 21:1–4:- “አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ፣ . . . ታላቅም ድምፅ ከሰማይ:- እነሆ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው ከእነርሱም ጋር ያድራል፣ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤ እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፣ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፣ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፣ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።”— ፊደላቱን ጋደል አድርገን የጻፍናቸው እኛ ነን።

ሚክ. 4:3, 4:- “ሕዝብ በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም ከእንግ ዲህም ወዲህ ሰልፍ አይማሩም። የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር አፍም ተናግሮአልና ሰው እያንዳንዱ ከወይኑና ከበለሱ በታች ይቀመጣል፣ የሚያስፈራውም የለም።”

ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት ለሞቱት ሰዎች ወደ ሰማይ የሚሄዱበትን መንገድ ከፍቶላቸዋልን?

1 ጴጥሮስ 3:19, 20 ምን ማለት ነው? “በእርሱም [ከትንሣኤው በኋላ መንፈስ ሆኖ] ደግሞ [ኢየሱስ] ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት [“መናፍስት” አዓት ] ሰበከላቸው። ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ [“ነፍሳት” ኪጄ፣ ዱዌይ፤ “ሰዎች” ቱኢቨ፣ ጀባ፣ ሪስ ] በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፣ የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቆየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም።” (እነዚህ ‘በወኅኒ የነበሩ መናፍስት’ ከጥፋት ውኃ በፊት የኖኅን ስብከት ያልተቀበሉት ሰዎች ነፍሳት ናቸውን? ወደ ሰማይስ የሚሄዱበት መንገድ ተከፍቶላቸዋልን? 2 ጴጥሮስ 2:4⁠ንና ይሁዳ 6⁠ን ከ⁠ዘፍጥረት 6:2–4 ጋር ማወዳደር እነዚህ መናፍስት በኖኅ ዘመን ሥጋ ለብሰው ጋብቻ የፈጸሙ የአምላክ መላእክታዊ ልጆች መሆናቸውን ያሳያል። በ⁠1 ጴጥሮስ 3:19, 20 ላይ “መናፍስት” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል ፕነማሲን ሲሆን “ነፍሳት” የሚለው የግሪክኛ ቃል ግን ፕሲሀይ ነው። እነዚህ “መናፍስት” ከሥጋቸው የተለዩ ነፍሳት ሳይሆኑ ያልታዘዙ መላእክት ናቸው። “ነፍስ” የተባሉት ግን ሰዎች ናቸው። እነርሱም ኖኅና ቤተሰቡ ነበሩ። እንግዲያው “በወኅኒ ለነበሩ መናፍስት” የተሰበከላቸው የፍርድ መልእክት መሆን አለበት።)

የ⁠1 ጴጥሮስ 4:6 ትርጉም ምንድን ነው? “እንደ ሰዎች በሥጋ እንዲፈረድባቸው በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር እንዲኖሩ ስለዚህ ምክንያት ወንጌል ለሙታን ደግሞ ተሰብኮላቸው ነበርና።” (እነዚህ “ሙታን” ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት የሞቱ ሰዎች ነበሩን? ቀደም ብሎ እንደተገለጸው እነዚህ ሙታን “በወኅኒ ያሉት መናፍስት” አይደሉም። እነዚህ መናፍስት ታዛዥ ያልሆኑ መላእክት ናቸው። ስብከት በሥጋ የሞቱትን ሰዎች ሊጠቅም አይችልም፤ ምክንያቱም መክብብ 9:5 እንደሚናገረው “ሙታን . . . አንዳች አያውቁም።” መዝሙር 146:4​ም [አዓት ] ሰው በሚሞትበት ጊዜ “ሐሳቡ ሁሉ ይጠፋል” ይላል። ነገር ግን ኤፌሶን 2:1–7, 17 በመንፈሳዊ ሞተው ስለነበሩና ምሥራቹን በመቀበላቸው ምክንያት መንፈሳዊ ሕይወት ስላገኙ ሰዎች ይናገራል።)

የሁሉም ክርስቲያኖች ተስፋ ሰማያዊ እንደሚሆን በ“አዲስ ኪዳን” ውስጥ ተገልጿልን?

ዮሐ. 14:2, 3:- “በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፣ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ።” (ኢየሱስ እዚህ ላይ የተናገረው ያዳምጡት የነበሩት ታማኝ ሐዋርያት ከጊዜ በኋላ ከእርሱ ጋር በሰማይ በአባቱ “ቤት” እንደሚሆኑ ነበር። ይሁን እንጂ ምን ያህል ሌሎች ሰዎች ወደ ሰማይ እንደሚሄዱ እዚህ ላይ አልተናገረም።)

ዮሐ. 1:12, 13:- “[ኢየሱስን] ለተቀበሉት ሁሉ ግን፣ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።” (ይህ ጥቅስ የሚናገረው የኢየሱስ “የገዛ ወገኖች” ስለነበሩት ስለአይሁዳውያን እንደሆነ ዮሐ 1 ቁጥር 11 ያመለክታል። ኢየሱስ በመጣበት በአንደኛው መቶ ዘመን የተቀበሉት አይሁዶች ሁሉ የሰማያዊ ሕይወት ተስፋ ያላቸው የአምላክ ልጆች ሆነዋል። በጥቅሱ ውስጥ ያሉት ግሦች አላፊ ጊዜን የሚያመለክቱ ስለሆነ ይህ ጥቅስ ከዚያ በኋላ ክርስቲያኖች የሆኑትን ሰዎች አይመለክትም።)

ሮሜ 8:14, 16, 17:- “በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና። የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል። ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፣ አብረንም ደግሞ እንድንከብር አብረን መከራን ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።” (ይህ በተጻፈበት ጊዜ በአምላክ መንፈስ ይመሩ የነበሩ ሁሉ የአምላክ ልጆች ሲሆኑ ከክርስቶስ ጋር ክብር የማግኘት ተስፋ ነበራቸው። ይሁን እንጂ ይህ ሁኔታ እስከ መጨረሻ አልቀጠለም። አጥማቂው ዮሐንስ በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ እንደነበረ ሉቃስ 1:15 ይናገራል። ይሁን እንጂ ማቴዎስ 11:11 ከሰማያዊው መንግሥት ክብር ተካፋይ እንደማይሆን በግልጽ ያመለክታል። ስለዚህ የሰማያዊው መንግሥት ወራሾች ከተሰበሰቡ በኋላ የልጁ ተከታዮች በመሆን አምላክን የሚያገለግሉና የሰማያዊ ክብር ተካፋዮች የማይሆኑ ሌሎች ሰዎች ይኖራሉ ማለት ነው።)

ክርስቲያኖች ዘላለማዊ ሕይወት አግኝተው በምድር ላይ እንደሚኖሩ የሚገልጹ ማስረጃዎች በ“አዲስ ኪዳን” ውስጥ ይገኛሉን?

ማቴ. 5:5:- “የዋሆች ብፁዓን ናቸው፣ ምድርን ይወርሳሉና።”

ማቴ. 6:9, 10:- “በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን። ” (ፊደላቱን ጋደል አድርገን የጻፍናቸው እኛ ነን።) (አምላክ ለምድር ያለው ፈቃድ ምንድን ነው? ዘፍጥረት 1:28 እና ኢሳይያስ 45:18 ምን ያመለክታሉ?)

ማቴ. 25:31–33, 40, 46:- “የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፣ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፣ በጎቹን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል። . . . ንጉሡም መልሶ [በጎቹን] እንዲህ ይላቸዋል:- እውነት እላችኋለሁ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል። እነዚያም [ፍየሎቹ] ወደ ዘላለም ቅጣት፣ ጻድቃን ግን [በጎቹ] ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።” (እነዚህ “በጎች” ‘የሰማያዊ ጥሪ ተካፋዮች’ ከሆኑት ከንጉሡ ወንድሞች ጋር አንድ አለመሆናቸውን ልብ በል። [ዕብ. 2:10–3:1] እነዚህ በግ መሰል የሆኑ ሰዎች ንጉሡ በዙፋኑ ላይ በሚቀመጥበትና ከ“ወንድሞቹ” መካከል አንዳንዶቹ በምድር ላይ ችግር በሚያጋጥማቸው ጊዜ በሕይወት የሚገኙ ናቸው።)

ዮሐ. 10:16:- “ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም ይሰማሉ፣ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ።” (እነዚህ “ሌሎች በጎች” እነማን ናቸው? በ“አዲሱ ቃል ኪዳን” የበጎች በረት ውስጥ ገብተው ሰማያዊ ሕይወት ለማግኘት ተስፋ የማያደርጉ የመልካሙ እረኛ የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች ናቸው። እነርሱም በአዲሱ ቃል ኪዳን በረት ውስጥ ካሉት ጋር አብረው ይሠራሉ።)

2 ጴጥ. 3:13:- “ጽድቅ የሚኖርባትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንደ ተስፋ ቃሉ እንጠብቃለን።” (ፊደላቱን ጋደል አድርገን የጻፍናቸው እኛ ነን።) (እንዲሁም ራእይ 21:1–4)

ራእይ 7:9, 10:- “ከዚህ በኋላ [ሐዋርያው ዮሐንስ ‘ከምድር ተዋጅተው የታተሙትንና’ በሰማያዊት የጽዮን ተራራ ከክርስቶስ ጋር የሚሆኑትን ሰዎች ሙሉ ቁጥር ካየ በኋላ፣ ራእይ 7:3, 4፤ 14:1–3⁠ን ተመልከት] አየሁ፣ እነሆም፣ አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤ በታላቅም ድምፅ እየጮኹ:- በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለአምላካችንና ለበጉ ማዳን ነው አሉ።”

መጽሐፍ ቅዱስ ስንት ሰዎች የሰማያዊ ሕይወት ተስፋ እንዳላቸው ያሳያል?

ሉቃስ 12:32:- “አንተ ታናሽ መንጋ ፣ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ።”— ፊደላቱን ጋደል አድርገን የጻፍናቸው እኛ ነን።

ራእይ 14:1–3:- “አየሁም፣ እነሆም፣ በጉ [ኢየሱስ ክርስቶስ] በጽዮን ተራራ [በሰማይ፣ ዕብራውያን 12:22–24⁠ን ተመልከት] ቆሞ ነበር፣ ከእርሱም ጋር ስሙና የአባቱ ስም በግምባራቸው የተጻፈላቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ። . . . አዲስ ቅኔ ዘመሩ፤ ከምድርም ከተዋጁት ከመቶ አርባ አራት ሺህ በቀር ያን ቅኔ ሊማር ለማንም አልተቻለውም።”— ፊደላቱን ጋደል አድርገን የጻፍናቸው እኛ ነን።

144,000ዎቹ ከሥጋዊ አይሁዳውያን ብቻ የተውጣጡ ናቸውን?

ራእይ 7:4–8:- “የታተሙትንም ቁጥር ሰማሁ፤ ከእስራኤል ልጆች ነገድ ሁሉ የታተሙት መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ። . . . ከይሁዳ . . . ከሮቤል . . . ከጋድ . . . ከአሴር . . . ከንፍታሌም . . . ከምናሴ . . . ከስምዖን . . . ከሌዊ . . . ከይሳኮር . . . ከዛብሎን . . . ከዮሴፍ . . . ከብንያም . . . ታተሙ።” (እነዚህ የሥጋዊ እስራኤል ነገድ አባቶች ሊሆኑ አይችሉም፤ ምክንያቱም የዮሴፍ ነገድ የሚባል ነገር አልነበረም። የኤፍሬምና የዳን ነገዶች በዝርዝሩ ውስጥ አልገቡም። እንዲሁም ሌዋውያን ከቤተ መቅደሱ ጋር ለተያያዘ አገልግሎት ተለይተው ስለነበር ከአሥራ ሁለቱ ነገዶች እንደ አንዱ ሆነው አይቆጠሩም ነበር። ዘኁልቁ 1:4–16⁠ን ተመልከት።)

ሮሜ 2:28, 29:- “በግልጥ አይሁዳዊ የሆነ አይሁዳዊ አይደለምና፣ በግልጥ በሥጋ የሚደረግ መገረዝም መገረዝ አይደለምና፤ ዳሩ ግን በስውር አይሁዳዊ የሆነ አይሁዳዊ ነው፣ መገረዝም በመንፈስ የሚደረግ የልብ መገረዝ ነው እንጂ በመጽሐፍ አይደለም።”

ገላ. 3:26–29:- “በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፤ . . . አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፣ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፣ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና። እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ።”

144,000 የሚለው ቁጥር እንዲሁ ምሳሌያዊ ቁጥር ነውን?

144,000 በማለት የተወሰነ ቁጥር ከጠቀሰ በኋላ ራእይ 7:9 ማንም ሊቆጥራቸው ስለማይችል “እጅግ ብዙ ሰዎች” መናገሩ ቁጥሩ ምሳሌያዊ አለመሆኑን ይጠቁማል። 144,000 የሚለው ቁጥር ቃል በቃል የሚወሰድ ካልሆነ “እጅግ ብዙ ሰዎች” ከሚለው ጋር ሲነፃፀር ትርጉም ያጣል። ይህን ቁጥር እንዳለ ቃል በቃል መውሰዱ ኢየሱስ በ⁠ማቴዎስ 22:14 ላይ ስለ መንግሥተ ሰማያት “የተጠሩ ብዙዎች፣ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና” በማለት ከተናገረው ጋር ይስማማል።— ፊደላቱን ጋደል አድርገን የጻፍናቸው እኛ ነን።

በራእይ 7:9, 10 ላይ “እጅግ ብዙ ሰዎች” ተብለው የተጠሩትም ወደ ሰማይ ይሄዳሉን?

የራእይ መጽሐፍ ስለ 144,000ዎቹ በሰማያዊት የጽዮን ተራራ ከክርስቶስ ጋር እንዲሆኑ ‘ከምድር የተዋጁ’ ናቸው በማለት ይናገርላቸዋል። ስለ እነዚህ ሰዎች ግን እንደዚያ ብሎ አይናገርም።—ራእይ 14:1-3

“በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ” የሚለው አገላለጽ ተቀባይነት የማግኘትን ሁኔታ እንጂ የግድ የሚኖሩበትን ቦታ አያመለክትም። (ከ⁠ራእይ 6:17⁠ና ከ⁠ሉቃስ 21:36 ጋር አወዳድር።) “በዙፋኑ ፊት” የሚለው አገላለጽ (በግሪክኛ ኢኖፒየን ቶው ትሮናው ቀጥተኛ ትርጉሙ “ከዙፋኑ ትይዩ መሆን”) የእነርሱን በሰማይ መሆን አያመለክትም። የቆሙበት ቦታ ከሰማይ ሆኖ የሰው ልጆችን እንደሚያይ ከሚነግረን ከአምላክ “ትይዩ” ነው።—መዝ. 11:4፤ ከ⁠ማቴዎስ 25:31–33፤ ሉቃስ 1:74, 75፤ ሥራ 10:33 ጋር አወዳድር።

በ⁠ራእይ 19:1, 6 ላይ “በሰማይ . . . ብዙ ሕዝብ” የተባለው በ⁠ራእይ 7:9 ላይ ከተጠቀሱት “እጅግ ብዙ ሰዎች” ጋር አንድ አይደለም። በሰማይ ያሉት ከተለያዩ ሕዝቦች እንደተውጣጡ ወይም ያዳናቸው በጉ መሆኑን እንደተናገሩ አልተገለጸም። እዚህ ላይ የተጠቀሱት መላእክት ናቸው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “እጅግ ብዙ ሰዎች” የሚለው አነጋገር በተለያዩ አገባቦች ሊያገለግል ይችላል።—ማር. 5:24፤ 6:34፤ 12:37

ወደ ሰማይ የሚሄዱት በዚያ ምን ያደርጋሉ?

ራእይ 20:6:- “የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ ከእርሱም ጋር ይህን ሺህ ዓመት ይነግሣሉ።” (እንዲሁም ዳንኤል 7:27)

1 ቆሮ. 6:2:- “ቅዱሳን በዓለም እንዲፈርዱ አታውቁምን?”

ራእይ 5:10:- “ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፣ በምድርም ላይ [“በምድር ላይ” ሪስ፣ ኪጄ፣ ዱዌይ፤ “በምድር ላይ ሆነው” አት፣ ዴር፣ ኖክስ፣ ኮክ ] ይነግሣሉ።” (ከዚህ ጋር ተመሳሳይ የሆነ የግሪክኛ ቃልና ሰዋስዋዊ አገባብ በ⁠ራእይ 11:6 ላይ ይገኛል። ሪስ፣ ኪጄ፣ ዱዌይ ወዘተ ሁሉም “በምድር ላይ” በማለት ተርጉመውታል።)

ወደ ሰማይ የሚሄዱትን የሚመርጣቸው ማን ነው?

2 ተሰ. 2:13, 14:- “እኛ ግን፣ በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ፣ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ልናመሰግን ግድ አለብን፣ እግዚአብሔር በመንፈስ መቀደስ እውነትንም በማመን ለመዳን እንደ በኩራት መርጦአችኋልና ፤ ለዚህም የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር ለማግኘት በወንጌላችን ጠራችሁ።”— ፊደላቱን ጋደል አድርገን የጻፍናቸው እኛ ነን።

ሮሜ 9:6, 16:- “እነዚህ ከእስራኤል የሚወለዱ ሁሉ እስራኤል አይደሉምና። . . . እንግዲህ ምሕረት ለወደደ ወይም ለሮጠ አይደለም፣ ከሚምር ከእግዚአብሔር ነው እንጂ።”