በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዳን

መዳን

ፍቺ:- ከጥፋት ወይም ከአደጋ መትረፍ ወይም መላቀቅ ማለት ነው። ሰዎቹ የሚላቀቁት ከጨቋኞች ወይም ከአሳዳጆች እጅ ሊሆን ይችላል። ይሖዋ እውነተኛ ክርስቲያኖችን በሙሉ በልጁ አማካኝነት ከአሁኑ የነገሮች ሥርዓት ያላቅቃቸዋል፤ እንዲሁም ከኃጢአትና ከሞት ያድናቸዋል። በዚህ “በመጨረሻው ቀን” የሚኖሩና የታመኑ የይሖዋ አገልጋዮች የሆኑ እጅግ ብዙ ሰዎች የሚያገኙት መዳን ከታላቁ መከራ መትረፍን ይጨምራል።

አምላክ በታላቅ ምሕረቱ ውሎ አድሮ የሰው ልጆችን በሙሉ ያድናልን?

2 ጴጥሮስ 3:9 አጠቃላይ የሆነ መዳን እንደሚኖር ያመለክታልን? ጥቅሱ እንዲህ ይላል:- “ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፣ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።” የአዳም ልጆች በሙሉ ንስሐ እንዲገቡ የመሐሪው አምላክ ፈቃድ ከመሆኑም በላይ ንስሐ የገቡ ሁሉ የኃጢአት ሥርየት የሚያገኙበትን መንገድ በልግስና አዘጋጅቷል። ይሁን እንጂ አምላክ ይህንን ዝግጅት እንዲቀበል ማንንም ሰው አያስገድድም። (ከ⁠ዘዳግም 30:15–20 ጋር አወዳድር።) ብዙዎች ይህንን ዝግጅት አይቀበሉም። ወንዝ ውስጥ ሊሰምጥ ተቃርቦ ሳለ ሊረዳው የፈለገው ሰው ሕይወቱን ሊያድንለት የሚችል መንሳፈፊያ ሲጥልለት አልፈልግም ብሎ እንደሚወረውር ሰው ሆነዋል። ይሁን እንጂ ንስሐ ካልገቡ የሚቀረው ሌላው አማራጭ የሲኦል እሳት አለመሆኑ መታወቅ አለበት። 2 ጴጥሮስ 3:9 እንደሚያመለክተው ንስሐ ያልገቡ ሁሉ ‘ይጠፋሉ።’ ቁጥር 7ም ‘እግዚአብሔርን የማያመልኩት ሰዎች እንደሚጠፉ ’ ይገልጻል። እዚህ ላይ አጠቃላይ ስለሆነ መዳን የተገለጸ ነገር የለም።—በተጨማሪም “ሲኦል” የሚለውን ዋና ርዕስ ተመልከት።

1 ቆሮንቶስ 15:22 የሰው ልጆች በሙሉ በመጨረሻው እንደሚድኑ ያረጋግጣልን? ጥቅሱ እንዲህ ይላል:- “ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና።” በዚህ ጥቅስ ዙሪያ ያሉት ሐሳቦች እንደሚያመለክቱት እዚህ ላይ እየተብራራ ያለው ጉዳይ ትንሣኤ ነው። ትንሣኤ የሚያገኙት እነማን ናቸው? በአዳማዊ ኃጢአት ምክንያት የሞቱና (ቁጥር 21⁠ን ተመልከት) ሆን ብለው በ⁠ዕብራውያን 10:26–29 ላይ የተገለጸውን በደል ያልፈጸሙ ሰዎች ናቸው። ኢየሱስ ከሲኦል እንደተነሣ ሁሉ (ሥራ 2:31) በሲኦል ውስጥ ያሉ ሌሎች ሰዎች በሙሉ በትንሣኤ አማካይነት “ሕያው” ይሆናሉ። (ራእይ 1:18፤ 20:13) እነዚህ ሁሉ የዘላለም መዳን ያገኛሉን? የዘላለም ሕይወት የማግኘት አጋጣሚ ለሁሉም ክፍት ይሆናል። ይሁን እንጂ ዮሐንስ 5:28, 29 ላይ እንደተገለጸው አንዳንዶች የቅጣት “ፍርድ” ስለሚፈረድባቸው ሰዎች ሁሉ የዚህ አጋጣሚ ተጠቃሚዎች አይሆኑም።

ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ፀጋ ስለሚሉ እንደ ቲቶ 2:11 ያሉ ጥቅሶችስ ምን ሊባል ይቻላል? እንደ ዮሐንስ 12:32፤ ሮሜ 5:18⁠ና 1 ጢሞቴዎስ 2:3, 4 ያሉ ጥቅሶችም በሪስ፣ ኪጄ፣ ኒኢ፣ ቱኢቨ፣ በ1954 ትርጉም እንዲሁም በሌሎች ትርጉሞች ውስጥ ተመሳሳይ ሐሳብ ያስተላልፋሉ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ “ሁሉ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል ፓስ ከተባለው ቃል የተወሰደ ነው። በቫይን ኤክስፖዚተሪ ዲክሽነሪ ኦቭ ኒው ቴስታመንት ወርድስ (ለንደን፣ 1962፣ ጥራዝ 1፣ ገጽ 46) ላይ እንደተመለከተው ፓስ “ሁሉም ዓይነት ወይም የተለያየ ዓይነት” የሚል ትርጉም ሊኖረው ይችላል። ስለዚህ ከላይ በተጠቀሱት ቁጥሮች ውስጥ “ሁሉ” ከማለት ይልቅ “እያንዳንዱን ዓይነት” ወይም አዓት እንደተረጎመው “ከሁሉም ዓይነት” ሊባል ይችላል። ትክክለኛው “ሁሉ” የሚለው ነው ወይስ “ከሁሉም ዓይነት ሰዎች” የሚለው? ከሌሎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ጋር የሚስማማው የትኛው አተረጓጎም ነው? የኋለኛው ነው። ሥራ 10:34, 35፤ ራእይ 7:9, 10፤ 2 ተሰሎንቄ 1:9⁠ን ተመልከት። (ሌሎች ተርጓሚዎችም ይህን የግሪክኛ ቃል ትርጉም ተረድተዋል። ይህንንም ማቴዎስ 5:11⁠ን በሚተረጉሙበት ጊዜ አሳይተዋል። “ሁሉንም ዓይነት” ሪስ፣ ቱኢቨ፤ “እያንዳንዱን ዓይነት” ኒኢ፣ “በሁሉ መንገድ” ኪጄ )

አንዳንዶች ፈጽመው እንደማይድኑ የሚያመለክቱ ጥቅሶች አሉን?

2 ተሰ. 1:9:- “ከጌታ ፊት ከኃይሉም ክብር ርቀው በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ።” (ፊደላቱን ጋደል አድርገን የጻፍናቸው እኛ ነን።)

ራእይ 21:8:- “የሚፈሩና የማያምኑ የርኩሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትን የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”

ማቴ. 7:13, 14:- “በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፣ መንገዱም ትልቅ ነውና፣ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤ ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፣ መንገዱም የቀጠነ ነውና፣ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።”

አንድ ሰው አንዴ ከዳነ ለሁልጊዜ ይድናልን?

ይሁዳ 5:- “ዳሩ ግን ሁሉን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ምንም የተማራችሁ ብትሆኑ ጌታ ከግብፅ አገር ሕዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ።” (ፊደላቱን ጋደል አድርገን የጻፍናቸው እኛ ነን።)

ማቴ. 24:13:- “እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።” (የአንድ ሰው የመጨረሻ መዳን የሚወሰነው በኢየሱስ ማመን በጀመረበት ጊዜ አይደለም።)

ፊልጵ. 2:12:- “ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፣ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ፣ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ።” (ይህ ጥቅስ በ⁠ፊልጵስዩስ 1:1 ላይ እንደተገለጸው የተጻፈው በፊልጵስዩስ ለነበሩ “ቅዱሳን” ነበር። ጳውሎስ በራሳቸው እንዳይተማመኑና የመጨረሻ መዳናቸው ገና ያልተረጋገጠ እንደሆነ አሳሰባቸው።)

ዕብ. 10:26, 27:- “የእውነትን እውቀት ከተቀበለን በኋላ ወደን ኃጢአት ብናደርግ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት አይቀርልንምና፣ የሚያስፈራ ግን የፍርድ መጠበቅ ተቃዋሚዎችንም ሊበላ ያለው የእሳት ብርታት አለ።” (ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ሰው “ከዳነ” በኋላ ምንም ዓይነት ኃጢአት ቢሠራም መዳኑ አይቀርም የሚለውን ሐሳብ አይደግፍም። የታመኑ ሆኖ መገኘትን ያበረታታል። በተጨማሪም አንድ በመንፈስ የተቀባ ሰው እንኳ የመዳን ተስፋውን ሊያጣ እንደሚችል የሚገልጸውን ዕብራውያን 6:4–6⁠ን ተመልከት።)

ለመዳን ከእምነት በተጨማሪ ሌላ ነገር ያስፈልጋልን?

ኤፌ. 2:8, 9:- “ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ [“ይገባናል የማንለው ደግነት” አዓት ] ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።” (መላው የመዳን ዝግጅት ይገባናል የማንለው የአምላክ ደግነት መግለጫ ነው። ማንም የአዳም ተወላጅ ምንም ያህል ታላላቅ ሥራዎችን ቢሠራ በራሱ ጥረት ሊድን የሚችልበት መንገድ የለም። መዳን ኃጢአት የማስተስረይ ችሎታ ባለው በኢየሱስ መሥዋዕት ለሚያምኑ የሚሰጥ የአምላክ ስጦታ ነው።)

ዕብ. 5:9:- “[ኢየሱስ] ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው።” (ፊደላቱን ጋደል አድርገን የጻፍናቸው እኛ ነን።) (ታዲያ ይህ ክርስቲያኖች ‘በእምነት እንደሚድኑ’ ከሚናገሩት ጥቅሶች ጋር ይጋጫልን? በፍጹም አይጋጭም። መታዘዛቸው የሚያሳየው እምነታቸው እውነተኛ መሆኑን ብቻ ነው።)

ያዕ. 2:14, 26:- “ወንድሞቼ ሆይ፣ እምነት አለኝ የሚል ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን? ከነፍስ [“ከመንፈስ” አዓት ] የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ፣ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።” (አንድ ሰው መዳንን እንደ ድካሙ ዋጋ አድርጎ ሊቀበል ይችልም። ይሁን እንጂ እውነተኛ እምነት ያለው ሰው ከእምነት ጋር የሚስማማ ሥራ ይሠራል። አምላክና ክርስቶስ የሰጡትን ትእዛዝ ይፈጽማል። ለእምነቱና ለፍቅሩ ማስረጃ የሚሆኑ ሥራዎችን ይሠራል። እንደነዚህ ያሉ ሥራዎችን ካልሠራ እምነቱ በድን ነው።)

ሥራ 16:30, 31:- “ጌቶች ሆይ፣ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል? አላቸው። እነርሱም [ጳውሎስና ሲላስ]:- በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን፣ አንተና ቤተ ሰዎችህም ትድናላችሁ አሉት።” (ይህ ሰውና ቤተሰቦቹ እውነተኛ እምነት ከኖራቸው ከእምነታቸው ጋር የሚስማማ ሥራ አይሠሩምን? እንደሚሠሩ የተረጋገጠ ነው።)

አንድ ሰው እንዲህ ቢልስ:-

‘ድኛለሁ’

እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘ይህን በማወቄ በጣም ደስ ይለኛል፤ ምክንያቱም ይህ በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምኑ ሰው መሆንዎን ያሳየኛል። እኔም የምሠራው ሥራ ኢየሱስ ተከታዮቹ እንዲሠሩ የሰጣቸው ሥራ ነው። ይህም ሥራ ስለ ተቋቋመችው የአምላክ መንግሥት ለሰዎች መናገር ነው። (ማቴ. 24:14)’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- (1) ‘ይህች መንግሥት ምንድን ናት? የዚህች መንግሥት መምጣትስ ለዓለም ምን ትርጉም ይኖረዋል? (ዳን. 2:44)’ (2) ‘በዚህ ሰማያዊ መስተዳድር ዘመን በምድር ላይ ምን ዓይነት ሁኔታ ይኖራል? (መዝ. 37:11፤ ራእይ 21:3, 4)’

ወይም እንዲህ ማለት ትችላለህ:- ‘እንግዲያው ሐዋርያው ጴጥሮስ በ⁠ሥራ 4:12 ላይ የተናገረውን ያውቃሉ ማለት ነው። . . . የኢየሱስን ስም እንድናምንበት የሰጠን ማን እንደሆነ አስበው ያውቃሉ?’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- (1) ‘ኢየሱስ ራሱ ነግሮናል። (ዮሐ. 17:3)’ (2) ‘ኢየሱስ የአባቱን ስም እንዳሳወቀ መናገሩን ልብ ይበሉ። (ዮሐ. 17:6) የግል ስሙ ማን ነው? ይህስ ምን ነገሮችን ያስታውስዎታል? (ዘጸ. 3:15 አዓት ወይም ዘጸ. 6:3 የ1879 ትርጉም፤ 34:5–7)’

‘ድነሃል?’

እንዲህ በማለት ለመመለስ ትችላለህ:- ‘እስከ አሁን ድረስ አዎ። ይህን የምለው በአቋማችን ከሚገባ በላይ መኩራራት እንደማይገባ የሚናገረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ምክር ስለማስታውስ ነው። ይህን ጥቅስ ያውቁታል? (1 ቆሮ. 10:12)’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- ‘ይህ የሆነበት ምክንያቱ ምንድን ነው? ሐዋርያው ጳውሎስ እንደገና ለተወለዱና ሰማያዊ ተስፋ ላላቸው ሰዎች (ዕብ. 3:1) እንዲህ ሲል ጽፏል:- . . . (ዕብ. 3:12–14) እምነታችንን ልናጠነክር የምንችለው በአምላክ ቃል ላይ ያለንን እውቀት እያሳደግን ስንሄድ ነው።’

ወይም እንዲህ ማለት ትችላለህ:- ‘ይህን ጥያቄ በቀላሉ ለመመለስ ያህል አዎ ለማለት እችላለሁ። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ስለ አንድ ዓይነት መዳን ብቻ እንዳልሆነ ያውቁ ነበርን? ለምሳሌ ያህል የ⁠ራእይ 7:9, 10, 14⁠ን ትርጉም አስበውበት ያውቃሉ? . . . ስለዚህ ከሚመጣው ታላቅ መከራ ድነው በዚህ ምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች ይኖራሉ። (ማቴ. 5:5)’

‘ኢየሱስን እንደ ግል አዳኝህ አድርገህ ተቀብለኸዋል?’

በገጽ 220, 221 ላይ “ኢየሱስ ክርስቶስ” በሚለው ርዕስ ሥር ተመልከት።

‘የሚድኑት 144,000 ብቻ ናቸው ትላላችሁ’

እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘እኛ በትክክል ምን ብለን እንደምናምን ለመናገር ስለሚያስችለኝ ይህንን ጉዳይ በማንሣትዎ በጣም ደስ ብሎኛል። መዳን አምላክ በኢየሱስ በኩል ባዘጋጀው መንገድ ለሚያምኑ ሁሉ ክፍት ነው። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ከክርስቶስ ጋር በሰማይ ለመኖር የሚሄዱት 144,000 ብቻ እንደሆኑ ይናገራል። ይህን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አይተው ያውቃሉ? . . . በ⁠ራእይ 14:1, 3 ላይ ይገኛል።’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- (1) ‘እነዚህ ሰዎች በሰማይ ምን ያደርጋሉ? (ራእይ 20:6)’ (2) ‘እነሱ የበላይ ሆነው የሚገዟቸው ሰዎች እንደሚኖሩ ግልጽ ነው። እነዚህ ሰዎች እነማን ናቸው? . . . (ማቴ. 5:5፤ 6:10)’