በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አጋንንት ነፍሰ ገዳዮች ናቸው!

አጋንንት ነፍሰ ገዳዮች ናቸው!

ሰይጣንና አጋንንቱ ምንጊዜም ጨካኞችና አደገኞች ናቸው። በቀድሞ ዘመን ሰይጣን የታማኙን የኢዮብን ባሪያዎችና ከብቶች ገድሎበታል። ከዚያም “ኃይለኛ ነፋስ” አስነስቶ የነበሩበትን ቤት እንዲወድቅ በማድረግ አሥሩን ልጆቹን ገድሎበታል። ከዚያም በመቀጠል ኢዮብን “ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ፀጉሩ ድረስ ክፉኛ በሚያሠቃይ እባጭ” መቶታል።—ኢዮብ 1:7-19፤ 2:7

በኢየሱስም ዘመን አጋንንት አንዳንድ ሰዎችን ዱዳዎችና ዓይነ ስውራን አድርገዋቸው ነበር። (ማቴዎስ 9:32, 33፤ 12:22) አንድን ሰው ራሱን በድንጋይ እንዲተለትል በማድረግ አሠቃይተውት ነበር። (ማርቆስ 5:5) አንድን ልጅም እንዲጮህ፣ መሬት ላይ እንዲወድቅና በኃይል ‘እንዲንፈራገጥ’ አድርገዋል።—ሉቃስ 9:42

በቀድሞ ዘመን አጋንንት አንዳንድ ሰዎችን እንዲታመሙ ሌሎችን ደግሞ ራሳቸውን ስተው እንዲወድቁና እንዲንፈራገጡ ያደርጓቸው ነበር

በዛሬው ጊዜ ሰይጣንና አጋንንቱ ከምንጊዜውም የበለጠ ነፍስ ለማጥፋት ታጥቀዋል። እንዲያውም ከሰማይ ተወርውረው ከተጣሉበት ጊዜ ወዲህ ክፉ ተግባራቸው ጨምሯል። ከዓለም ዙሪያ የሚመጡ ዘገባዎች የሰይጣንና የአጋንንቱን ጭካኔ ይመሠክራሉ። አንዳንዶቹን ሰዎች በበሽታ ያሠቃዩአቸዋል። ሌሎችን ደግሞ እንቅልፍ በመንሳት ወይም አስፈሪ ሕልም እንዲያልሙ በማድረግ በሌሊት ያሸብሯቸዋል። ሌሎችን ደግሞ በፆታ ያስነውሯቸዋል። ሌሎችን ደግሞ ያሳብዷቸዋል፣ ሰዎችን ወይም ራሳቸውን እንዲገድሉ ይገፋፏቸዋል።

በዛሬው ጊዜ አጋንንት አንዳንድ ሰዎችን ወንጀለኞች ያደርጓቸዋል፤ ሌሎችን ደግሞ በሌሊት አስፈሪ ሕልም እንዲያልሙ በማድረግ ያስጨንቋቸዋል

በሱሪናም የምትኖረው ሊንቲና አንድ ጋኔን ወይም መጥፎ መንፈስ ከቤተሰቧ ውስጥ 16ቱን እንደገደለባትና እሷንም ለ18 ዓመታት በአካልና በአእምሮ እንዳሠቃያት ትናገራለች። ከራሷ ተሞክሮ በመነሣት አጋንንት “እሺ የማይሏቸውን ሰዎች እስከሞት ድረስ በማሠቃየት እንደሚደሰቱ” ትናገራለች።

ይሁን እንጂ ይሖዋ አገልጋዮቹን ከሰይጣን ጥቃቶች ሊጠብቃቸው ይችላል።—ምሳሌ 18:10