በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አስደናቂ የወደፊት ተስፋ

አስደናቂ የወደፊት ተስፋ

በቅርቡ ሰይጣንና አጋንንት ከሥራ ይታገዳሉ

ሰይጣንና አጋንንቱ ከአሁን ወዲያ ሰዎችን የሚያሳስቱበት ረጅም ጊዜ የላቸውም። ቀደም ብሎም ይሖዋ ከሰማይ አውጥቶ ጥሏቸዋል። (ራእይ 12:9) በቅርቡ ደግሞ አምላክ በሰይጣንና በአጋንንቱ ላይ እርምጃ ይወስዳል። ሐዋርያው ዮሐንስ ከአምላክ በተሰጠው ራእይ እንደሚከተለው ብሏል፦ “እኔም የጥልቁን ቁልፍና ታላቅ ሰንሰለት በእጁ የያዘ አንድ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ። እሱም ዘንዶውን ያዘውና ለ1,000 ዓመት አሰረው፤ ይህም ዘንዶ ዲያብሎስና ሰይጣን የሆነው የጥንቱ እባብ ነው። ደግሞም ይህ 1,000 ዓመት እስኪያበቃ ድረስ ከእንግዲህ ሕዝቦችን እንዳያሳስት ወደ ጥልቁ ወረወረውና ዘጋበት፤ በማኅተምም አሸገው።” (ራእይ 20:1-3) በኋላም ዲያብሎስና አጋንንቱ ለዘላለም ይጠፋሉ።—ራእይ 20:10

በምድር ላይ ያሉት መጥፎ ሰዎችም ይጠፋሉ።—መዝሙር 37:9, 10፤ ሉቃስ 13:5

ሙታን እንደገና በሕይወት ይኖራሉ!

ሙታን ወደ ሕይወት ተመልሰው በምድር ላይ ይኖራሉ

ሰይጣንና አጋንንቱ ከተወገዱ በኋላ ይሖዋ ለሰው ልጆች ብዙ በረከቶች ያመጣላቸዋል። ሙታን አሁን ሕይወት እንደሌላቸውና በሕይወት እንደማይኖሩ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተማርከውን ታስታውሳለህ። ኢየሱስ ሞትን ከእንቅልፍ ማለትም ሕልም ከሌለበት ከከባድ እንቅልፍ ጋር አመሳስሏል። (ዮሐንስ 11:11-14) እንዲህ ያደረገው በሞት ያንቀላፉት ተቀስቅሰው ወደ ሕይወት እንደሚመለሱ ያውቅ ስለነበረ ነው። “በመታሰቢያ መቃብር ያሉ ሁሉ . . . ይወጣሉ” ብሏል።—ዮሐንስ 5:28, 29፤ ከሐዋርያት ሥራ 24:15 ጋር አወዳድር።

ሙታን ወደ ሕይወት ተመልሰው የሚኖሩት እዚችው ምድር ላይ ነው። የሞቱ ሰዎችን ስም ዝርዝር በሚገልጹ የመርዶ ማስታወቂያዎች ፈንታ ወደ ሕይወት ስለተመለሱት ሰዎች የሚናገሩ አስደሳች ሪፖርቶች ይሰማሉ! የሚወዱትን ሰው ከመቃብር ሲወጣ ተቀብሎ ማስተናገድ ምን ያህል ያስደስት ይሆን!