በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክፍል 1

‘የሚያስደምም ኃይል ያለው’

‘የሚያስደምም ኃይል ያለው’

በዚህ ክፍል ውስጥ ይሖዋ ኃይሉን ለመፍጠር፣ ለማጥፋት፣ አገልጋዮቹን ለመጠበቅና አንድን ነገር ለማደስ እንደሚጠቀምበት የሚገልጹ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን እንመረምራለን። ‘የሚያስደምም ኃይል’ ያለው ይሖዋ ‘ገደብ የሌለው ብርቱ ጉልበቱን’ እንዴት እንደሚጠቀምበት መረዳታችን፣ ልባችን በድፍረትና በተስፋ እንዲሞላ ያደርጋል።—ኢሳይያስ 40:26

በዚህ ክፍል ውስጥ

ምዕራፍ 4

‘ይሖዋ ኃይሉ ታላቅ ነው’

አምላክ ያለው ኃይል እንድንፈራው ሊያደርገን ይገባል? ትክክለኛው መልስ ይገባልም፣ አይገባምም የሚል ነው።

ምዕራፍ 5

‘የሰማይና የምድር ፈጣሪ’—ለመፍጠር የሚጠቀምበት ኃይል

ግዙፍ ከሆነችው ፀሐይ አንስቶ ኢምንት እስከሆነችው ሃሚንግበርድ የተባለችው ወፍ፣ የአምላክ ፍጥረታት ስለ አምላክ አስፈላጊ ትምህርት ያስተምሩናል።

ምዕራፍ 6

‘ኃያል ተዋጊ የሆነው ይሖዋ’—ለማጥፋት የሚጠቀምበት ኃይል

“የሰላም አምላክ” መለኮታዊ ጦርነት የሚያካሂደው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 7

‘መጠጊያችን የሆነው አምላክ’—ለመጠበቅ የሚጠቀምበት ኃይል

አምላክ ሕዝቡን የሚጠብቀው በሁለት መንገዶች ነው፤ አንደኛው ግን ከሁሉ በላይ አስፈላጊ ነው።

ምዕራፍ 8

‘ሁሉንም ነገር አዲስ የሚያደርገው’ ይሖዋ—ለማደስ የሚጠቀምበት ኃይል

ይሖዋ በአሁኑ ጊዜ ንጹሑን አምልኮ መልሶ አቋቁሟል። ወደፊትስ ምን ነገር ያድሳል?

ምዕራፍ 9

‘ክርስቶስ የአምላክ ኃይል ነው’

ኢየሱስ ክርስቶስ የፈጸማቸው ተአምራት እንዲሁም ያስተማራቸው ትምህርቶች ስለ ይሖዋ ምን ይነግሩናል?

ምዕራፍ 10

በኃይል አጠቃቀም ረገድ “አምላክን የምትመስሉ ሁኑ”

አለኝ ብለህ ከምታስበው በላይ ኃይል ወይም ሥልጣን ይኖርህ ይሆናል፤ ይሁንና ይህን ኃይልህን በአግባቡ መጠቀም የምትችለው እንዴት ነው?