በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ተቃራኒ ፆታ

ተቃራኒ ፆታ

ክፍል 1

ተቃራኒ ፆታ

ትምህርት ቤት ውስጥ አንድ ወንድና አንዲት ሴት እጅ ለእጅ ተያይዘው ኮሪደር ላይ ሲሄዱ ተመለከትክ እንበል። ምን ይሰማሃል?

□ ግድ አይሰጠኝም

□ ትንሽ እቀናለሁ

□ በጣም እቀናለሁ

ከጓደኞችህ ጋር ፊልም ቤት ሄደህ ሳለ ከአንተ በስተቀር ሁሉም ጥንድ ጥንድ መሆናቸውን አስተዋልክ እንበል። ምን ይሰማሃል?

□ ግድ አይሰጠኝም

□ ያሸማቅቀኛል

□ በጣም እቀናለሁ

በጣም የምትወደው ጓደኛህ ሰሞኑን አንዲት ወጣት ወድዶ ከእሷ ጋር የፍቅር ጓደኝነት ጀምሯል እንበል። ምን ይሰማሃል?

□ ደስ ይለኛል

□ ትንሽ እቀናለሁ

□ በቅናት እብከነከናለሁ

በትምህርት ቤት፣ በመንገድ ላይ፣ በገበያ ቦታም ሆነ በማንኛውም ስፍራ ወጣቶች ወንድ ሴት፣ ወንድ ሴት ሆነው ሲሄዱ ትመለከታለህ። ባየሃቸው ቁጥር አንተም የሴት ጓደኛ እንድትኖርህ በጣም ትመኛለህ። ይሁንና የፍቅር ጓደኝነት ለመጀመር ደርሰሃል? ‘ደርሻለሁ’ የምትል ከሆነ ለአንተ የምትሆንህ የፍቅር ጓደኛ ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው? የምትስማማህ ጓደኛ ካገኘህ ደግሞ በምትጠናኑበት ወቅት የሥነ ምግባር ንጽሕናችሁን መጠበቅ የምትችሉት እንዴት ነው? ከ1 እስከ 5 ባሉት ምዕራፎች ላይ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት ትችላለህ።

[በገጽ 12 እና 13 ላይ የሚገኝ ባለ ሙሉ ገጽ ሥዕል]