በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች​—ዮሴፍ

አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች​—ዮሴፍ

አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች​—ዮሴፍ

ዮሴፍ አስቸጋሪ ሁኔታ አጋጥሞታል። የጌታው ሚስት ከእሷ ጋር የፆታ ግንኙነት እንዲፈጽም ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ጊዜ ጠይቃው ነበር። አሁንም አልለቀቀችውም! ይሁንና ዮሴፍ በጥያቄዋ አልተሸነፈም። እንዲያውም የሰጠው ምላሽ ቁርጥ ያለ ነበር። “ይህን ክፉ ድርጊት ፈጽሜ እንዴት በእግዚአብሔር ፊት ኀጢአት እሠራለሁ?” አላት። የጌታው ሚስት ግን የዮሴፍ እንቢታ አልተዋጠላትም፤ ይባስ ብላም ልብሱን ጨምድዳ ያዘችው። በዚህ ጊዜ ዮሴፍ ጥሏት ለመሄድ ምንም አላመነታም፤ እንዲያውም ሸሽቶ ከቤት ወጣ! ዮሴፍ ጠንካራ የሥነ ምግባር አቋም ያለው ሰው መሆኑን አሳይቷል።​—ዘፍጥረት 39:7-12

አንቺም እንደ ዮሴፍ ዓይነት ሁኔታ ሊያጋጥምሽ ይችላል፤ ለምሳሌ፣ አንድ ሰው ለፆታ ፍላጎትሽ እንድትሸነፊ ይገፋፋሽ ይሆናል። እንዲህ ያለውን ፈተና ለመቋቋም ቆራጥ አቋም መያዝ ብቻውን የሚፈይደው ነገር የለም። ፈጣሪሽ የሆነውን ይሖዋ አምላክን የማስደሰት ፍላጎት በውስጥሽ ሊኖር ይገባል። ዮሴፍም እንደ አንቺ የፆታ ፍላጎት እንደነበረው አስታውሺ። ይሁንና ዮሴፍ የፆታ ፍላጎቱን ለማርካት ሲል ፈጣሪውን የሚያሳዝን ነገር መፈጸም በጭራሽ የማያስበው ነገር ነበር። አንቺም በተመሳሳይ የሥነ ምግባር ብልግና መፈጸም አምላክን የሚያሳዝንና ጣጣ ውስጥ የሚያስገባሽ ድርጊት መሆኑን ከልብ ልታምኚበት ይገባል። እንግዲያው ዮሴፍ ያሳየው ዓይነት ጠንካራ የሥነ ምግባር አቋም ለማዳበርና ይህንን አቋምሽን ጠብቀሽ ለመቀጠል ጥረት አድርጊ።