በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች​—ጳውሎስ

አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች​—ጳውሎስ

አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች​—ጳውሎስ

ሐዋርያው ጳውሎስ በውስጡ ከሚፈጠሩ አንዳንድ ስሜቶች ጋር በተያያዘ ሚዛናዊ አመለካከት አዳብሯል። “ትክክል የሆነውን ነገር ማድረግ ስፈልግ ከእኔ ጋር ያለው ግን መጥፎ ነገር ነው” በማለት በግልጽ ተናግሯል። ጳውሎስ ጥሩ ሰው ነው። “በውስጤ በአምላክ ሕግ እጅግ ደስ ይለኛል” ሲል ጽፏል። ታዲያ የጳውሎስ ችግር ምንድን ነው? “ከአእምሮዬ ሕግ ጋር የሚዋጋና በአካሌ ክፍሎች ውስጥ ላለው የኃጢአት ሕግ ምርኮኛ አድርጎ የሚሰጠኝን ሌላ ሕግ አያለሁ” ብሏል። ጳውሎስ ስህተት የሚሠራ መሆኑ እንዲያዝን አድርጎታል። “እኔ ምንኛ ጎስቋላ ሰው ነኝ!” በማለት ተናግሯል።​—ሮም 7:21-24

አንተስ ስህተት መሥራትህ ጎስቋላ ሰው እንደሆንክ እንዲሰማህ ወይም ደስታህን እንድታጣ ያደርግሃል? ከሆነ ጳውሎስም እንኳ አንዳንድ ጊዜ እንደዚህ ይሰማው እንደነበር አስታውስ። ጳውሎስ፣ ክርስቶስ የሞተው እንደ እሱ ላሉ ሰዎች መሆኑን ያውቅ ስለነበር “በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የሚታደገኝ አምላክ የተመሰገነ ይሁን!” በማለት መናገር ችሏል። (ሮም 7:25) ጳውሎስ የቤዛውን ዝግጅት በግሉ እንደተሰጠው ስጦታ አድርጎ ተመልክቶታል። ‘የአምላክ ልጅ እንደወደደውና ለእሱ ሲል ራሱን አሳልፎ እንደሰጠ’ ጽፏል። (ገላትያ 2:20) አንተም ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ሲሰማህ በቤዛው ዝግጅት ላይ አሰላስል። ስህተት በመሥራትህ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ካደረብህ ክርስቶስ የሞተው ለፍጹማን ሳይሆን ለኃጢአተኞች መሆኑን አትዘንጋ።