በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክፍል 2

እውነተኛው አምላክ ማን ነው?

እውነተኛው አምላክ ማን ነው?

እውነተኛው አምላክ አንድ ብቻ ነው፤ ስሙም ይሖዋ ነው። (መዝሙር 83:18) እሱ መንፈስ ስለሆነ ልናየው አንችልም። እኛን ይወደናል፤ በምላሹም እሱን እንድንወደው ይፈልጋል። ለሌሎች ሰዎችም ፍቅር እንድናሳይ ይፈልጋል። (ማቴዎስ 22:35-40) እሱ የሁሉ የበላይና የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው።

ከአምላክ ፍጥረታት መካከል የመጀመሪያው፣ ኃያል የሆነ መንፈሳዊ ፍጡር ሲሆን እሱም ከጊዜ በኋላ ኢየሱስ ክርስቶስ ተብሎ ተጠርቷል። ይሖዋ መላእክትንም ፈጥሯል።

ይሖዋ በሰማይና . . . በምድር ያለውን ነገር ሁሉ ፈጥሯል። ራእይ 4:11

ይሖዋ አምላክ ከዋክብትን እንዲሁም ምድርንና በላይዋ ላይ ያለውን ነገር ሁሉ ፈጥሯል።—ዘፍጥረት 1:1

የመጀመሪያውን ሰው ይኸውም አዳምን ከምድር አፈር ሠራው።—ዘፍጥረት 2:7