በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክፍል 8

የኢየሱስ ሞት ለአንተ ምን ትርጉም አለው?

የኢየሱስ ሞት ለአንተ ምን ትርጉም አለው?

ኢየሱስ እኛ ሕይወት እንድናገኝ ሲል ሞቶልናል። ዮሐንስ 3:16

ኢየሱስ ከሞተ ከሦስት ቀናት በኋላ አንዳንድ ሴቶች መቃብሩን ለማየት በሄዱ ጊዜ ባዶ ሆኖ አገኙት። ይሖዋ ኢየሱስን ከሞት አስነስቶት ነበር።

በኋላም ኢየሱስ ለሐዋርያቱ ተገለጠላቸው።

አዎ፣ ይሖዋ ኢየሱስን ኃያልና የማይሞት መንፈሳዊ ፍጡር አድርጎ ከሞት አስነስቶታል። የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ወደ ሰማይ ሲያርግ ተመልክተውታል።

አምላክ ኢየሱስን ከሞት አስነስቶ የአምላክ መንግሥት ንጉሥ አደረገው። ዳንኤል 7:13, 14

ኢየሱስ ለሰው ልጆች ቤዛ ለመክፈል ሲል ሕይወቱን መሥዋዕት አድርጎ ሰጥቷል። (ማቴዎስ 20:28) አምላክ በቤዛው አማካኝነት ለዘላለም መኖር የምንችልበትን አጋጣሚ ከፍቶልናል።

ይሖዋ ኢየሱስን በምድር ላይ እንዲገዛ ንጉሥ አድርጎ ሾሞታል። ከሞት ተነስተው በሰማይ የሚኖሩ 144,000 ታማኝ ሰዎች ከእሱ ጋር ይነግሣሉ። ኢየሱስና 144,000ዎቹ ጽድቅ የሰፈነበትን ሰማያዊ መስተዳድር ይኸውም የአምላክን መንግሥት ይመሠርታሉ።—ራእይ 14:1-3

የአምላክ መንግሥት ምድርን ገነት ያደርጋታል። ጦርነት፣ ወንጀል፣ ድህነትና ረሃብ ይወገዳሉ። ሰዎች እውነተኛ ደስታ ያገኛሉ።—መዝሙር 145:16