በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች​—ያዕቆብ

አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች​—ያዕቆብ

አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች​—ያዕቆብ

ያዕቆብ እና ወንድሙ ዔሳው ከተነጋገሩ ዓመታት አልፈዋል። እንዲያውም ዔሳው ያዕቆብን አጥብቆ ይጠላዋል። ያዕቆብ ግን ያጠፋው ነገር ባይኖርም በመካከላቸው ያለውን ችግር ለመቅረፍ ቅድሚያውን ወሰደ። ያዕቆብ እርቅ ለማውረድ ሲል ስምምነት ለመፍጠር ፈቃደኛ ነበር። ዓላማው ወንድሙ እንዲወደው ማድረግ እንጂ በተፈጠረው አለመግባባት አሸናፊ መሆን አልነበረም። በእርግጥ ያዕቆብ ከሚያምንባቸው ነገሮች ጋር የሚጋጭ እርምጃ አልወሰደም፤ በሌላ በኩል ግን ‘ይቅርታ ካልተጠየቅኩ ሰላም መፍጠር አልፈልግም’ አላለም።—ዘፍጥረት 25:27-34፤ 27:30-41፤ 32:3-22፤ 33:1-9

አንተስ ከቤተሰብህ አባላት ጋር አለመግባባት ሲፈጠር የምትፈታው እንዴት ነው? አንዳንድ ጊዜ፣ አንተ ትክክል እንደሆንክና ጥፋተኞቹ ወንድሞችህና እህቶችህ ወይም ወላጆችህ እንደሆኑ ይሰማህ ይሆናል። እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ሲያጋጥምህ እነሱ ቅድሚያውን ወስደው እስኪያናግሩህ ትጠብቃለህ? ወይስ እንደ ያዕቆብ ዓይነት እርምጃ ትወስዳለህ? የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች እስካልተጣሱ ድረስ ሰላም ለመፍጠር ስትል ሐሳብህን ለመለወጥ ፈቃደኛ ነህ? (1 ጴጥሮስ 3:8, 9) ያዕቆብ ኩሩ በመሆን ቤተሰቡ እንዲከፋፈል ከመፍቀድ ይልቅ ትሕትና በማሳየት ከወንድሙ ጋር እርቅ ፈጥሯል። አንተስ ከቤተሰብህ ጋር ባለህ ግንኙነት እንዲህ ታደርጋለህ?